ፖለቲካዊ Suicide እየፈጸሙ ያሉ የህወሃት ቫይረስ ተሸካሚዎች!

ጋዜጠኛ ወንድወሰን ተክሉ

የአፋብን ላእላይ አመራር የህወሃት ቫይረስ ተሸካሚ በመሆን አይደለም ለአማራ ሕዝብ ይቅርና ለራሳቸውም እንካን የማይሆንን Political Suicide እያፈጸሙ ነው።

ለመሆኑ ውሃ እና ዘይት እኩል ፈሳሽ ቢሆኑም ማዋሃድ ይቻላልን?!

በፋኖ እና በህወሃት መካከል የትብብር ስምምነት እንፈጥራለን እያሉ በመዳከር ላይ ያሉት የአፋብን ላእላይ የፖለቲካ አመራሮች ከመላው የአማራ ሕዝብና ከመላው የአማራ ፋኖ ሰራዊት የሚነጥላቸውን የፖለቲካ ጥፋት ያለአንዳች መሳቀቅ እያፈጸሙ ነው። እነዙህ አመራሮች ስለምን የፖለቲካ ህልውናቸውን ለማክተም መጣደፍ ውስጥ ሊገቡ እንደቻሉ የአማራ አምላክ ይወቅ።

ነገር ግን እየመረራቸው የሚጋቱት አንድ እውነት አለ። ያም እውነት አንድም የአማራ ፋኖ ሰራዊት፣ አንድም የአማራ ሕዝብ የስልጣን ዘመና ካከተመውና በጸረ አማራነታ ከምታወቀው ህወሃት ጋር ሆነው አንዳች ፖለቲካ ለመስራት ቢሞክሩ የሚቀበላቸው የለም። ተራግፈው የፖለቲካ ሞትን በመሞት ከህልውና ትግሉ ገለል እንዱሉ ነው የሚደረገው እንጂ እነሱ የተሸከሙትን የህወሃት ቫይረስ ተቀብሎ የሚሸከም አማራ ፈጽሞ የለም።

እንዴት የሰው ልጅ ይህን ያህል ፖለቲካዊ ህልውናውን የሚያከስምበትን ግንኙነት የሙጢኝ ብሎ ሞቼ እገኛለሁ ይላል???

ማንም ሰው ወደ ህወሃት መሄድ ይችላል። ግላዊ መብቱ ነው።

ማንም ሰው አማራነቱንም ክዶ የህወሃት አባል ሆኖ ለህወሃት መታገል ይችላል። ግላዊ መብቱ ነው።

አንድም ሰው፣ የአፋብን ሰብሳቢ ሆነ፣ የአፋብን ወታደራዊ አዛዥ የአማራን ትግልና የአማራን ፋኖ ድርጅት ይዞ ወደ ህወሃት መሄድ ፈጽሞ አይችልም። ማንም አይፈቅድለትምም።

የአማራ ፋኖ ሰራዊት ታግሎ የሚያታግለውን አፋብንን ይዞ ወደ ህወሃት ለመግባት የሚጥርን ላእላይ አመራር በዝምታ እያየ የሚፈቅድለት አይሆንም!!!

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.