መክሸፍ እንደ ሀብታሙ አያሌው!

 

” እኔ የምሰብከውን ወያኔን ያልተቀበለ ሁሉ እርኩስ ከመአሪዮስ ነው”
ሀብታሙ አያሌው – የህወሃት ጠበቃ

Main Media Stream ወደ ባልት፣ ስድብና ነቆራ በለወጠ መልኩ ሚዲያውን መሳደቢያ ያደረገው ገልቱው ተሳዳቢ

ጋዜጠኛ ወንድወሰን ተክሉ

ለመሆኑ ህወሃት ስንት ብትከፍለው ነው ይህንን ያህል 7/24hrs ወያኔ ወይንም ሞት፣ ‘’ጽምዶ አዳኛችን ነው’’ እያለ ለሀጩን ሊያዝረበርብ የቻለው ?

ለመሆኑ አንድ የፖለቲካ ተንታኝ ነኝ የሚል ሰው በዚህ ፍጥነት ቁልቁል ተምዘግዝጎ እራሱን በአጭር ጊዜ ከቲክቶክ ላይ ከምንሰማቸው ተሳዳቢዎች እጥፍ በልጦ ከተንታኝነት ወደ ለየለት ተሳዳቢነት እራሱን መለወጥ ይቻለዋልን?!

ለመሆኑ አንድ እራሱን የእግዚአብሔርን ቃል እንደሚያውቅ አድርጎ የሚገልጽ፣ በሚሰጠው የፖለቲካ ትንታኔ ላይ የመጽሀፍ ቅዱስን ጥቅስ እያጣቀሰ ለቤተክርስቲያን ቅርብ ብቻ ሳይሆን የቤተክርስቲያን ልጅ ነኝ እያለ የሚመጻደቅ ሰው ይህንን ያህል እራሱን ቁልቁቆ ፈጥፍጦ በስድብ ፍላጻ ሰውን በሳተላይት ቲቪ ሰውን መሳደብ ይቻለዋልን?

እጅግ Disgusting የሆነ Personality ያለው ሰው ሆኖ ነው የተገኘው። በተለይ ባለፈው መስከረም 11 ቀን 2025 እራሱን ነጥሎ የንጉስ ዙፋን አስቀምጦ ብቻውን ካስወደስ እና ከዚያም ለጥቆም ከ 360 ሚዲያ እራሱን ነጥሎ ይህ አሁን የሚሳደብበትን ኢትዮ ውርደት ሚዲያውን ከከፈተ በኃላ ግለሰቡ ጭንብሉን አውልቆ እውነተኛ ማንነቱ፣ ማለትም ፍጹም ቀጣፊነቱን፣ ፍጹም መረን የለቀቀ ተሳዳቢነቱንና ብልተኝነቱን ለአደባባይ ያበቃ ሰው መሆኑን ስናይ በኢሳትና በኢትዮ 360 ሚዲያ ውስጥ ሆኖ ታፍኖና ታስሮ የነበረ ሰው መሆኑን ነው የሚያሳየን እንጂ ይህን አይነቱን መረን የለቀቀ ተሳዳቢነትን አሁን የተለማመደው ነው ብሎ መግለጽ ይቸግራል።

የታሪኩ ጭብጥ የሚያጠነጥነው ከጽምዶና ህወሃትን በአማራ ሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖራቸው ሌት ተቀን ከመዋተት ይጀምራል። እንደ ሀብታሙ አያሌው ግላዊ ገለጻ እሱ የፖለቲካ ትንታኔን የPHD ቆብ አጥልቃል። እናም በኢትዮጲያ ፖለቱካ ውስጥ ያለውንና ሊሆን የሚችለውን የኃይል አሰላለፍ ጠንቅቆ የሚያውቅ እና ይህንንም ነቢያዊ እውቀቱን ሰዎች ያለአንዳች ጥያቄና ቅዋሜ አሜን እያሉ እንዲያስተጋቡለት እጅግ ይሻል።

ወያኔ እና ጽምዶ – ( ጽምዶ ወያኔና ሻእቢያን ያጣመደ ሀሳባዊ የሁለቲዮሽ ጥማድ ነው) ለአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል ፍጹም አጋር ሆነው የቀረቡ ናቸው ብሎ ደምድማል። እንዴት የአማራ ፋኖ እና የትግራዩ ህወሃት በጋራ ሊሰሩ እንደሚችሉ ምንም ትንፍሽ ብሎ ማብራራት ሳይችል ሾላ በደፈናው ፋኖ ከወያኔም ሆነ ከጽምዶ ጋር ሆኖ አገዛዙን መታገል አለበት እያለ 7/24hurs እጅግ ሲወተውት ይደመጣል።

ሁለቱ በጋራ የሚሰሩበት የፖለቲካ ቀመር (ፎርሙላ) አሊያም ሁለቱን አቀራርቦ በጋራ ሊያሰልፍ የሚችል የመግባቢያ ሰነድ Memorandum of Understanding MOU እስቲ አምጣ ተብሎ ቢጠየቅ የሚያቀርበው ቅንጣት የመግባቢያ፣ የመቀራረቢያና የመስማሚያ ነጥቦች ሳይኖሩ ፋኖ እና ህወሃት አብረው መስራት አለባቸው እያለ ክችችች ብሎ የደረቀ ሰው ነው።

ሁለቱ አብረው መስራት አለባቸው ብሎ ክችችች ብሎ መገገሙ ችግር የለውም። መብቱ ነው። ችግር የሚኖረው እኔ ያልኩትን ያልተቀበለ እርኩስ ከመአሪዮስ ነው፣ የስርዓቱ አገልጋይ ነው ወዘተ እያለ በመፈረጅ በጽምዶና ህወሃት ላይ ብርቱ ትችት የሚያቀርቡትን ከመፈረጅ አልፎ በስድብ ናዳ ሲያጥረገርግ መገኘቱ ነው የዚህ ሰው በሽተኝነት።

ትናንት – በዚሁ በጽምዶ ጉዳይ የቀድሞ ባልደረባውን ኢየሩሳሌም ተክለጻዲቅን (ጄሪ) ሲያጥረገርግ የሚያሳይ አጭር ቪዲዮ ሲዘዋወር ተመልከቼ ይሄ ሰው ጨርቁን አልጣለም እንጂ ህሊናውን የሳተ ሰው ነው ስል ለራሴ አሰብኩ።

ሀብታሙ ጄሪ ላይ ያዥጎደጎደውን የስድብ ናዳ መልሶ መድገም እጅግ ጸያፍ ነው። ማድመጥ የሚፈልግ ሄዶ ማድመጥ ይችላል። ጄሪ ስለጽምዶ ምን ብላ እንደዘገበች ይህ ጸሀፊ ፈጽሞ የሚያውቀውና የሰማው ነገር የለም። ከሀብታሙ የስድብ ናዳ በመነሳት ጄሪ ስለጽምዶ የሆነ ነገር እንደተናገረች ግን መገመት ይቻላል።

እናም የጽምዶና የህወሃት ጠበቃ ነኝ የሚለው ሀብታሙ አያሌው ብቅ ብሎ ሲጥረገርጋት አመሸ።

ለመሆኑ ሀብታሙን የጽምዶና የህወሃት ጠበቃ ያደረገው ማን ነው?? ወዱ አፈወርቂና ደጺ ናቸውን ?? ስንት ቢከፈለውስ ነው ይህንን ያህል ህወሃትን ከኢየሱስ እኩል አዳኝ አድርጎ እንዲሰብክ ያደረገው ?

እሺ – እሱ አይደለም ጭራቃን ወያኔን ይቅራና ከፈለገ የሎሲፈርም ጠበቃና ወዳጅ መሆን ይችላል። መብቲ ነው። ስለምንድነው ይህንን ኃላቀር እና Outdated የሆነን ፊውዳላዊ አስተሳሰቡን ያልተቀበሉት ላይ መረን የለሽ ልቅ አንደበቱን ሰው ላይ የሚከፍተው?!

በህወሃትና በጽምዶ ጉዳይ ሀሳብ የሚሰጡ ሁሉ በሀብታሙ አያሌው ብልጽግን ተብለው ተፈርጀዋል። መዝለፍና መስደብ የቻለውን ሁሉ ተሳድባል። አባት አርበኛ መሳፍንት ተስፉ እንካን ሳይቀሩ እንዴት ስለጽምዶ ይናገራሉ እያለ ወርዶባቸዋል። የአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል ከሁለቱ ጸረ አማራ ኃይሎች ህወሃት እና ብልጽግና (ኦህዴድ/ብአዴን) ጥገኝነት ርቆ እና እራሱን ችሎ በተደራጀ አማራዊ ድርጅት ታግሎ አታጋይነት ግቡን የሚመታው ብለው ወጥ አቋም የሚያራምዱ የአማራ ልጆች በሙሉ በሀብታሙ አያሌው የብልጽግና ተላላኪ እየተባሉ ተፈርጀዋል፣ ከሰባተኛ ሰፈር ካለች ተሳዳቢ ኮማሪት ባስናቀ አንደበቱ ነጋ ጠባ ተሰድበዋል፣ ተብጠልጥለዋል።

ይህ ሁሉ ግብረገብነት የጎደለው ስድብ፣ ፍረጃና አሉባልታ እኔ የምሰብከውን ህወሃት ለምን ተቻቹ፣ ለምን ጽምዶ ለአማራ ፋኖ አይሆንም ትላላችሁ ነው ምክንያቱ።

ከዚህ የበለጠ ህመምተኝነት አለን???
ከዚህ የበለጠ ወርዶ መፈጥፈጥስ አለን???
ከዚህ የበለጠ የህወሃት ሽንት ጨርቅ አጣቢ መሆን አለን??

እጅግ ይቀፋል። አንድ ወንድ አንዲትን ሴት እንዲህ ሲሳደብና ሲሳለቅ ማየት እጅግ መቅፈፍ ብቻ ሳይሆን ወንድነቱን እንድንጠራጠር ያደርጋል። እጅግም ይቀፋል።

ግን ለእሱ የደስታ ምንጭ ሆኖ ነው የሚያገለግለው። አሉባልተኝነቱን፣ ተሳዳቢነቱን Enjoy የማያደርግ ቢሆን በስድብ ረግረግ ውስጥ ተዘፍቆ ሲጨማለቅ ባልታየ ነበር። አበቃሁ።

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.