ወያኔ እጅ ሰጠች – ካባዋንም ገለበጠች!!! (አምሳሉ ገ/ ኪዳን)

ወያኔ እጅ ሰጠች – ካባዋንም ገለበጠች!!!
አምሳሉ ገ/ ኪዳን
 
 “እኛ የተመሠረትነውና የታገልነው ለዲሞክራሲያዊት አንዲት ኢትዮጵያ ነው!!!”
አቦይ ስብሐት ነጋ
ወያኔ የተመሠረተችበትና የታገለችው ትግል የተሳሳተ እንደሆነና ከባድ የፖለቲካ ኪሳራ መከናነቧን የተመሠረተችበትንና የታገለችበትን ትግል ሸምጥጣ ክዳ በአውራ ታጋይዋ በአቦይ ስብሐት በኩል ይፋ በማድረግ ነው እጅ የሰጠችው!!!
አቦይ ስብሐት ምን አሉ መሰላቹህ “እኛ የተመሠረትነውና የታገልነው ለዲሞክራሲያዊት አንዲት ኢትዮጵያ ነው፡፡ በርግጥ የትግራይ ሊብሬሽን (ነጻነት) የሚል አንድ ወረቀት ነበር እሱን ማን እንደጻፈው አይታወቅም!” ብለው እርፍ!!!
ቆይ ቆይ አቦይ ስብሓት አሁንም ድረስ ድርጅታቸው የሚጠራው የትግራይ ነጻ አውጭ ግንባር በትግርኛው ሕወሓት ተብሎ እንደሆነ ዘነጉት እንዴ??? ሰውየውን ምን ነካቸው??? ማጭበርበሩ፣ ማምታታቱ፣ ማወናበዱ ጠፋባቸው ወይስ ጃጁ???
መልካሙ ዜና ወያኔ መሳሳቷንና ከባድ ጥፋት መሥራቷን ማመኗ ሲሆን መጥፎው ዜና ደግሞ “ስሕተቱን የማረም አቅም አለንና አሁንም እኛው ነን!” ማለታቸው ነው፡፡
ልባቹህ በሳቅ ጦሽ ብላ እንዳትፈነዳ ተጠንቅቃቹህ ቃለምልልሱን አዳምጡት!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.