እንኳን ደስ ያለህ! (ጌታቸው አበራ)

እንኳን ደስ ያለህ!

ጌታቸው አበራ

 

      (ለመቶኛው የኖቤል የሰላም ሎሬት / ዐብይ አህመድ)

 

የሰው ዘር የምንጭ ህይወትየዘመናት ታሪክ እናት፣

የነጻነት ቀንዲል ብርሃንያለም ማማ የእግዚአብሔር ቤት፤

የመለኮት ምስጢራቱቅድስት አገር ኢትዮጵያ፣                    

መከራዋን አሸንፋ –  ባለም ታየች ሃሌሉያ!

 

ከበሻሻ መደብአልጋ  – የተነሳው ብላቴና፣

  ቀጭን መንገድ በድክ ድክውጣውረድ.. አለፈና፣

  በሰንበሌጥ ተመስሎጎርፉን አልፎ ለጥ ብሎ፣

  አሳር፣ ችግር፣ ሞትን ከድቶበተዐምር ህይወት ዘርቶ፣

  ካለም ጫፍ ላይ በድል ታየየክብር አክሊል ወርቁን ደፍቶ።

 

ያገር አድባር ግዙፍ ዋርካ፣

ስኬት ተስፋው እሚለካ፣

የይቻላል ትምህርት ቤትለትውልዱ አርአያ፣

ክብር ኩራት ለናት አገር ለእምዬ ለኢትዮጵያ!

 

ጌታቸው አበራ

ህዳር 2012 /

(ዲሴምበር 2019)

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.