እንኳን ደስ ያለህ! (ጌታቸው አበራ)

እንኳን ደስ ያለህ!

ጌታቸው አበራ

 

      (ለመቶኛው የኖቤል የሰላም ሎሬት ለ ዶ/ር ዐብይ አህመድ)

 

የሰው ዘር የምንጭ ህይወት – የዘመናት ታሪክ እናት፣

የነጻነት ቀንዲል ብርሃን – ያለም ማማ የእግዚአብሔር ቤት፤

የመለኮት ምስጢራቱ – ቅድስት አገር ኢትዮጵያ፣                    

መከራዋን አሸንፋ –  ባለም ታየች ሃሌሉያ!

 

…ከበሻሻ መደብ–አልጋ  – የተነሳው ብላቴና፣

  ቀጭን መንገድ በድክ ድክ – ውጣ–ውረድ.. አለፈና፣

  በሰንበሌጥ ተመስሎ – ጎርፉን አልፎ ለጥ ብሎ፣

  አሳር፣ ችግር፣ ሞትን ከድቶ – በተዐምር ህይወት ዘርቶ፣

  ካለም ጫፍ ላይ በድል ታየ – የክብር አክሊል ወርቁን ደፍቶ።

 

ያገር አድባር ግዙፍ ዋርካ፣

ስኬት ተስፋው እሚለካ፣

የይቻላል ትምህርት ቤት – ለትውልዱ አርአያ፣

ክብር ኩራት ለናት አገር ለእምዬ ለኢትዮጵያ!

 

ጌታቸው አበራ

ህዳር 2012 ዓ/ም

(ዲሴምበር 2019)

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.