![](https://www.ethioreference.com/wp-content/uploads/2021/01/FB_IMG_1611773659393-300x223.jpg)
የኦህዴድ/ኦነግ ያነጋገር ፈልጢ አልገባ ያለህ የዋሁ ወገኔ ምን ላድርግህ?
![](https://www.ethioreference.com/wp-content/uploads/2021/01/FB_IMG_1611773659393-300x223.jpg)
ሸንቁጥ አየለ
እነ አዳነች አበቤ የኮንዶሚኒዬም ወረራ የቤት ወረራ የቦታ ወረራ በአዲስ አበባ ላይ አለ ብለዉ ሲነግሩህ የኛ ነገድ ካልሆነዉ ኢትዮጵያዊ ላይ በጉልበት የምንቀማዉ ቦታ:የምናፈርሰዉ ቤት:በወንጀል የምንነጥቀዉ ኮንዶሚኒዬም አለ ማለታቸዉ ነዉ::
አዳነች አበቤ የተባለች ኦነግ/ኦህዴድ አዲስ አበባ ላይ የመሬት ወረራ : ህገወጥ የቤት ዘረፋ እየተካሂያደ ነዉ ብላ መረጃ ብትልቅ የዋሁ ህዝባችን እየተቀባበለ የዚችን ሴትዮ መረጃ ያስተጋባዋል::
አንዳንዱም ይባስ ብሎ እስክንድር/ባልደራስ ይሄን ለማስቆም ነበር እኮ የታገለዉ እያለ ይፖስታል::
ሰዉ እንዴት በሶስት አመት ዉስጥ ከሥስትም የከፋዉን የኦህዴድ/ኦነጋዉያንን ባህሪ ማስተዋል አቃተዉ ጃል?
ኦነግ/ኦህዴድ የመሬት ወረራ አለ: የኮንዶምኒዬም ዘረፋ አለ ስልህ አብሮ ቄሮ የሚለዉንም መጋዉን የመሬት ወረራን እና የኮንዶሚኒዬም ወረራን እንቃወማለን የሚል ሰልፍ እንደጠራዉ አላስተዋልክም ማለት ነዉ?
ቄሮ/ኦነግ/ኦህዴድ የሚቃወሙት እኮ የቤት እና የኮንዶሚኒዬም ወረራ የዋሁ ህዝባችን የሚያስበዉን እዉነታ አይደለም::
አዳነች አበቤ አሁን ቄሮዎቿን/የኦህዴድ ካድሬዎቿን አሰልፋ የምትቃወመዉ እኮ የአዲስ አበባ ህዝብ የያዘዉን ርስቱን ስለመንጠቅ: ቤቱን ስለመዉሰድ ነዉ::
አልተገናኝቶም አሉ::
እነ አዳነች አበቤ የመሬት ወረራ ሲሉ እኮ ድሃዉ የአዲስ አበባ ጎጆ የቀየሰባትን ጥቃቅን ቦታ ሁሉ ስለመንጠቅ ቤት ስለማፍረስ ነዉ::
የዋሁ ወገኔ ምን ላርግህ?
ነገር አይገባህም አይባል ነገር አዋቂ ነህ::
ግን ደግሞ አንዳንዴ የዋህነትህ አስገራሚ ነዉ::
ለማንኛዉም ለድሃዉ የአዲስ አበባ ኢትዮጵያዊ ሁሉ እግዚአብሄር ይሁነዉ እንጂ እነ አዳነች አበቤ ቀጣይ ማፈናቀል:ቤት ማፍረስ እና ኮንዶሚኒየሞችን መቀማት አድርገዉ ለራሳቸዉ ካድሬዎች/ቄሮዎች የማደል ፕሮግራማቸዉን ነዉ የነገሩህ::
እነ አዳነች አበቤ የኮንዶሚኒዬም ወረራ የቤት ወረራ የቦታ ወረራ በአዲስ አበባ ላይ አለ ብለዉ ሲነግሩህ የኛ ነገድ ካልሆነዉ ኢትዮጵያዊ ላይ በጉልበት የምንቀማዉ ቦታ:የምናፈርሰዉ ቤት:በወንጀል የምንነጥቀዉ ኮንዶሚኒዬም አለ ማለታቸዉ ነዉ::
የኦህዴዳዉያንን/ኦነጋዉያንን ትርጉም በትክክል ያለመረዳት አባዜ ሶስት እና አራት አመታት ሙሉ እንዴት ሊቀጥል እንደቻለ ግን አስገራሚ ነዉ::
አቢይ በሀገሪቱ ወንጀል ተሰራ ሲልህ የኦህዴድ/ኦነግን ወንጀለኞች አያካትትም::
በራሱ አንደበትም “ኦሮሞን ኦሮሞ ከሚገለዉ ብለን ኦነግ የሚሰራዉን ወንጀል እንዳላዬን አለፍነዉ” ብሎ በገሃድ ነግሮህ እንኳን የኦህዴዳዉያን/ኦነጋዉያን ትርጉም እንዲሁ ግራ ሆኖብህ ሶስት አራት አመት እንዴት ሊዘልቅ ቻለ?
አቢይ በሀገሪቱ ወንጀል ተሰራ ሲልህ የኦህዴድ/ኦነግን ወንጀለኞች አያካትትም:: ከሌላ ነገድ የሆኑ ሰዎች የሚሰሩት ጥቃቅን ስህተት ግን በአቢይ የወንጀል ዲክሽነሪ ዉስጥ ይካተታል::የአዳነች አበቤም ንግግር ይሄዉ ነዉ:: ኦነጋዉያንን/ኦህዴዳዉያንን እየገለበጥክ እየተመራመርክ ነዉ ማድመጥ ያለብህ::
መቼም ኢትዮጵያ የገጠማት ድንቅ ነገር ነዉ ! እጅግ ድንቅ !