>
5:13 pm - Friday April 19, 7439

የኦህዴድ/ኦነግ ያነጋገር ፈልጢ አልገባ ያለህ የዋሁ ወገኔ ምን ላድርግህ? (ሸንቁጥ አየለ)

የኦህዴድ/ኦነግ ያነጋገር ፈልጢ አልገባ ያለህ የዋሁ ወገኔ ምን ላድርግህ?

ሸንቁጥ አየለ

እነ አዳነች አበቤ የኮንዶሚኒዬም ወረራ የቤት ወረራ የቦታ ወረራ በአዲስ አበባ ላይ አለ ብለዉ ሲነግሩህ የኛ ነገድ ካልሆነዉ ኢትዮጵያዊ ላይ በጉልበት የምንቀማዉ ቦታ:የምናፈርሰዉ ቤት:በወንጀል የምንነጥቀዉ ኮንዶሚኒዬም አለ ማለታቸዉ ነዉ::
አዳነች አበቤ የተባለች ኦነግ/ኦህዴድ አዲስ አበባ ላይ የመሬት ወረራ : ህገወጥ የቤት ዘረፋ እየተካሂያደ ነዉ ብላ መረጃ ብትልቅ የዋሁ ህዝባችን እየተቀባበለ የዚችን ሴትዮ መረጃ ያስተጋባዋል::
አንዳንዱም ይባስ ብሎ እስክንድር/ባልደራስ ይሄን ለማስቆም ነበር እኮ የታገለዉ እያለ ይፖስታል::
ሰዉ እንዴት በሶስት አመት ዉስጥ ከሥስትም የከፋዉን የኦህዴድ/ኦነጋዉያንን ባህሪ ማስተዋል አቃተዉ ጃል?
ኦነግ/ኦህዴድ የመሬት ወረራ አለ: የኮንዶምኒዬም ዘረፋ አለ ስልህ አብሮ ቄሮ የሚለዉንም መጋዉን የመሬት ወረራን እና የኮንዶሚኒዬም ወረራን እንቃወማለን የሚል ሰልፍ እንደጠራዉ አላስተዋልክም ማለት ነዉ?
ቄሮ/ኦነግ/ኦህዴድ የሚቃወሙት እኮ የቤት እና የኮንዶሚኒዬም ወረራ የዋሁ ህዝባችን የሚያስበዉን እዉነታ አይደለም::
አዳነች አበቤ አሁን ቄሮዎቿን/የኦህዴድ ካድሬዎቿን አሰልፋ የምትቃወመዉ እኮ የአዲስ አበባ ህዝብ የያዘዉን ርስቱን ስለመንጠቅ: ቤቱን ስለመዉሰድ ነዉ::
አልተገናኝቶም አሉ::
እነ አዳነች አበቤ የመሬት ወረራ ሲሉ እኮ ድሃዉ የአዲስ አበባ ጎጆ የቀየሰባትን ጥቃቅን ቦታ ሁሉ ስለመንጠቅ ቤት ስለማፍረስ ነዉ::
የዋሁ ወገኔ ምን ላርግህ?
ነገር አይገባህም አይባል ነገር አዋቂ ነህ::
ግን ደግሞ አንዳንዴ የዋህነትህ አስገራሚ ነዉ::
ለማንኛዉም ለድሃዉ የአዲስ አበባ ኢትዮጵያዊ ሁሉ እግዚአብሄር ይሁነዉ እንጂ እነ አዳነች አበቤ ቀጣይ ማፈናቀል:ቤት ማፍረስ እና ኮንዶሚኒየሞችን መቀማት አድርገዉ ለራሳቸዉ ካድሬዎች/ቄሮዎች የማደል ፕሮግራማቸዉን ነዉ የነገሩህ::
እነ አዳነች አበቤ የኮንዶሚኒዬም ወረራ የቤት ወረራ የቦታ ወረራ በአዲስ አበባ ላይ አለ ብለዉ ሲነግሩህ የኛ ነገድ ካልሆነዉ ኢትዮጵያዊ ላይ በጉልበት የምንቀማዉ ቦታ:የምናፈርሰዉ ቤት:በወንጀል የምንነጥቀዉ ኮንዶሚኒዬም አለ ማለታቸዉ ነዉ::
የኦህዴዳዉያንን/ኦነጋዉያንን ትርጉም በትክክል ያለመረዳት አባዜ ሶስት እና አራት አመታት ሙሉ እንዴት ሊቀጥል እንደቻለ ግን አስገራሚ ነዉ::
አቢይ በሀገሪቱ ወንጀል ተሰራ ሲልህ የኦህዴድ/ኦነግን ወንጀለኞች አያካትትም::
በራሱ አንደበትም  “ኦሮሞን ኦሮሞ ከሚገለዉ ብለን ኦነግ የሚሰራዉን ወንጀል እንዳላዬን አለፍነዉ” ብሎ በገሃድ ነግሮህ እንኳን የኦህዴዳዉያን/ኦነጋዉያን ትርጉም እንዲሁ ግራ ሆኖብህ ሶስት አራት አመት እንዴት ሊዘልቅ ቻለ?
አቢይ በሀገሪቱ ወንጀል ተሰራ ሲልህ የኦህዴድ/ኦነግን ወንጀለኞች አያካትትም:: ከሌላ ነገድ የሆኑ ሰዎች የሚሰሩት ጥቃቅን ስህተት ግን በአቢይ  የወንጀል ዲክሽነሪ ዉስጥ ይካተታል::የአዳነች አበቤም ንግግር ይሄዉ ነዉ:: ኦነጋዉያንን/ኦህዴዳዉያንን እየገለበጥክ እየተመራመርክ ነዉ ማድመጥ ያለብህ::
መቼም ኢትዮጵያ የገጠማት ድንቅ ነገር ነዉ ! እጅግ ድንቅ !
Filed in: Amharic