>

"...ጥያቄው እስክንድርን ትፈቱታላችሁ? ወይስ በድራማችሁ ትቀጥላላችሁ? ነው...!!!" (ሀብታሙ አያሌው)

“…ጥያቄው እስክንድርን ትፈቱታላችሁ? ወይስ በድራማችሁ ትቀጥላላችሁ? ነው…!!!”

ሀብታሙ አያሌው

 

• ታከለ ኡማ አዲስ አበባን ሲቸበችባት አዳነች አቤቤ የህግ ከለላ ስትሰጠው የቆየች የአቃቤ ህግ ተቋሙ ኃላፊ ነበረች።
• እስክንድር ታከለ የሚያደርገው እየተከታተለ ሲያጋልጥ እንዲታሰር የተደረገው ሌባው ሳይሆን ለምን ያሉት እነ እስክንድር ነጋ ናቸው። የዚህ ተቋም ኃላፊ ደግሞ አዳነች ነበረች።
• አሳፋሪውና አስቂኙ ጉዳይ ደግሞ ከእስክንድር ክስ መካከል አንዱ “ከንቲባውን አላሰራው ብለሀል” የሚል ነው።አሁን ገባችሁ “አላሰራው ብለሀል” ማለት ምን ማለት እንደሆነ❗
• አዳነች አዲስ አበባ ውስጥ የሚህነው የምታውቅና የማስቆም ስልጣን የነበራት ሰው ነች።ያኔ ሽፋን ስትሰጥ ቆይታ አሁን “አጅሪት” የሚል ውታፍ ነቃይ ተደማሪ ተደጋፊ አሰማርታ እንድናመሰግናት እየጠበቀች ነው።
•እነሱ convince እና confuse የሚሏት ይቺን ኮሚካቸውን ነው።በዚህ ቀሽም ትወና ግን የሚታለልም ሆነ የሚሸወድ የለም።
•አሁን ታከለን ተጠያቂ አድርገው እስክንድርን ይፈቱታል ወይስ በዚሁ ቀሽም ትወናቸው ይቀጥላሉ የሚለውን አብረን የምናይ ይሆናል።
Filed in: Amharic