>
5:21 pm - Friday July 19, 2193

'ብልፅግና ማደራጃ መንገዱ ሌብነት፣ አዳሪነት፣ ተላላኪነት እና ስንፍና በመሆኑ ምክንያት ሀገሪቱ በውስብስብ ችግር ውስጥ ገብታለች...!!!' (አቶ ዮሃንስ ቧ ያለው)

‘ብልፅግና ማደራጃ መንገዱ ሌብነት፣ አዳሪነት፣ ተላላኪነት እና ስንፍና በመሆኑ ምክንያት ሀገሪቱ በውስብስብ ችግር ውስጥ ገብታለች…!!!’
አቶ ዮሃንስ ቧ ያለው

አቶ ዮሃንስ በትናንትናው ዕለት ቶቢያ ኬብል ቲቪ ከተባለ የበይነ መረብ ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቆይታ የብልፅግና የካድሬ መመልመያ መስፈርት ሌብነት፣ አጨብጫቢነት እና አለመታገል መሆኑን ተናግረዋል።
አሁን ካሉ አመራሮች ይልቅ የእነ አቶ በረከት ስምኦን ካድሬ የተሻለ ነበር ያሉት አቶ ዮሃንስ፣ አሁን ያሉት መሪዎች በተለይ የአማራዎች የአማራን ህዝብ ፖለቲካዊ ፍላጎት የማያውቁ እና ቢያውቁም የማይገዳቸው ናቸው ብለዋል።
አቶ ዮሃንስ ቧያሌው በሚኒስተር ደረጃ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የስልጠና ዋና ዳይሬክተር ናቸው። ነገርግን ግን እውነትን ከመናገር ስልጣናቸው አልገደባቸውም።
በብዛት ሹመት የተሰጣቸው የፓርቲ ገንዘብ ቀይፋ በፊርማቸው ያከፋፈሉት እና ለሌብነታቸው እውቅና ያገኙት ናቸው ብለዋል። የሰሊጥ ሌቦች የአማራን ፖለቲካ ገባሪ አድርገውታል ያሉት አቶ ዮሃንስ፣ የአማራ መሰረታዊ ጥያቄዎችም እየተዳፈኑ መሆኑን አስታውሰዋል።
አሁን መናገር የጀመሩት ከስልጣን ስለተገፉ ነው የሚል ጥያቄ የተጠየቁት አቶ ዮሃንስ “እኔ ራሴን የሆንኩ ሰው ነኝ። ስልጣን አላጣሁም። በነበረከት ካድሬ ውስጥም ትልቅ ባለስልጣን ነበርኩ። ነገርግን የዛኔም ራሴን ሆኘ ተቃውሜ ወጥቻለሁ” ብለዋል። የዛኔ በረከትን አግኝቶ ለማውራት ጉርሻ የሚከፍሉ ካድሬዎች ናቸው የዛሬ ተሿሚዎች ያሉት አቶ በረከት በኢህአዴግ መለስ ስልጣን ከለቀቀ ሀገር ትፈርሳለች የሚሉት ዛሬም አብይ ከስልጣን ተነሳ ኢትዮጵያ አትድንም እያሉ ነው። ቀጣይ ሌላ መሪ ቢመጣም አብይን ረግመው አዲሱን ያወድሳሉ ብለዋል። ይህ አይነት የቆሸሸ ጭንቅላት ከመሪነት ካልተገደበ አማራም ኢትዮጵያም ችግር ውስጥ ናቸው ብለዋል።
የሰነፍ እና የሌባ አመራር ደጋፊዎች የኛን ስም በማቆሸሽ የአማራን ትክክለኛ ጥያቄ ለመቅበር ይፈልጋሉ የሚሉት አቶ ዮሃንስ፣ ማን መሬት፣ ገንዘብ ተቀብሎ እንደሚፅፍ እና እንደሚናገር ይፋ እናደርጋለንም ብለዋል።
የብሌፅግናን ስንፍና ለመደበቅ የተቀጠሩ አክቲቪስቶች፣ ጋዜጠኞች፣ የፖለቲካ ተፎካካሪ ሀይሎች በርካታ ናቸው። አቶ ፀጋ አራጌም ከዚህ በፊት የተከፋዮችን እና የከፋዮችን ስም ዝርዝር በቅርብ ይፋ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።
አቶ ዮሃንስ የሌብነት፣ የስንፍና፣ የጭቆና ጠበቆች እንዲያመሰግኑኝ አልፈልግም። እኔ የምፈልገው ትክክለኛው የአማራ እና የኢትዮጵያ ህዝብ ድምፅ ለመሆን ነው ብለዋል።
ብልፅግና ማደራጃ መንገዱ ሌብነት፣ አዳሪነት፣ ተላላኪነት እና ስንፍና በመሆኑ ምክንያት ሀገሪቱ በውስብስብ ችግር ውስጥ ገብታለች የሚል ሀሳብም አንስተዋል።
ብልፅግና የሰነፎች እና የሆድ አደሮች ማህበር በመሆኑ ከኦህዴድ ብልፅግና እነ ለማ መገርሳ፣ ከብአዴን ብልፅግና እነ ዮሃንስ ቧያሌው፣ ፀጋ አራጌ፣ ላቀ አያሌው፣ ገዱ አንዳርጋቸው ወዘተ ተገፍተው ወጥተዋል።
በአንፃሩ በአማራ ስም እነ ዶክተር ለገሰ ቱሉ፣ ዛዲግ አብርሃ፣ ይታገሱ አስፋው የመሳሰሉ ለአማራ በጎ ምልከታ የሌላቸው ካድሬዎች ተሹመዋል። የብልፅግናን 60 ሚሊየን ብር የወሰዱ ካድሬዎችም የተሾሙ ሲሆን መሬት የቸረቸሩ፣ ሰሊጥ የነገዱ፣ በህዝብ ደም ያተረፉ ወደ ስልጣን መጥተዋል። ህወሃት ወረራ በፈፀመበት ወቅት የዘረፉ፣ ከህወሃት ጎን የሆኑ ወደ ስልጣን እየመጡ ታጋዮች ደግሞ ከስልጣን ተነስተዋል።
የመምራት ጥበብ ሲያልፍ ያልነካቸው የብልፅግና ወንጌል መሪዎች የኑሮ ውድነት ሲመጣ ነዳጅ እንዳይባክን በእግራችሁ ተንቀሳቀሱ፣ እንጀራ ከጠፋ ሙዝ በዳቦ ብሉ፣ መተከል እና ወለጋ በሰላም እጦት ሳይታረስ ከቤታችሁ ውስጥ አትክልት ትከሉ ብለው የሚመክሩ እውቀት ጠሎች ናቸው።
እነዚህ እውቀት ጠሎች ሀገሪቱን በኢኮኖሚ፣ በዲፕሎማሲ አቀጭጨዋታል። አቶ ዮሃንስም ይሄን ሀቅ በመረዳት እውነታውን እየመሰከሩ ሲሆን፣ የብልፅግና ተከፋዮች ደግሞ ታጋዮቸ አቶ ዮሃንስ የማዕከላዊ ኮሚቴ ምርጫውም በመራጭ ተመራጭ የተዋቀረ አንድ ሰው እስከ ስምንት የተመረጠበት አሳፋሪ ሂደት ነበር ብለውታል።
ሌላው አቶ ዮሃንስ ያነሱት፣ የህዝብ ቆጠራ አለመደረጉ የአማራ ህዝብ እንዲበደል አድርጓል ያሉ ሲሆን፣ ካሁን በሗላ ህዝብ ቆጠራ በገለልተኛ እና በውጭ ሀገር ዜጎች ካልሆነ ታማኒነት የለውም ብለዋል።
ከአማራ ህዝብ 1999 ዓም 2.4 ሚሊየኑ ሳይቆጠር እንደቀረ ይታወሳል።
ምንጭ:- ኢትዮጵያ ን እናድን
Filed in: Amharic