>

በመከላከያ እና በምስራቅ አማራ ፋኖ መካከል ሰላም ለማስፈን የኃይማኖት አባቶች እና የአገር ሽማግሌዎች እየጣሩ ናቸው! ባልደራስ

በመከላከያ እና በምስራቅ አማራ ፋኖ መካከል ሰላም ለማስፈን የኃይማኖት አባቶች እና የአገር ሽማግሌዎች እየጣሩ ናቸው!
ባልደራስ

 

# በፋኖዎች ላይ በሚደርሰው ተጽዕኖ ህዝቡ ደስተኛ አይደለም!
/
በወልዲያ አዳጎ በሚገኘው የምስራቅ አማራ ፋኖ ሎጀስቲክስ ማዕከል እና በሮቢት በሚገኘው ማሰልጠኛ ካምፑ ላይ በዙ23፣ በዲሽቃ እና በብሬን የታጀበ ተኩስ በመከላከያ በመፈፀሙ በአካባቢው ከፍተኛ ውጥረት ነግሶ ይገኛል፡፡ ችግሩ የተነሳው የምስራቅ አማራ ፋኖ መሪዎች እና ሌሎች የፋኖ መሪዎች ወደ አንድነት ለመምጣት በደሴ ስብሰባ ላይ ተቀምጠው ባሉበት ጊዜ የፋኖ አባላት ለእስር መዳረጋቸው ነበር፡፡
የአመራር አባላቱ ስብሰባቸውን ከጨረሱ በኋላ የምስራቅ አማራ ፋኖ መሪ ምሬ ወዳጆ ማዕከሉ ወደሆነችው ቆቦ እያመራ በነበረበት ጊዜ፣ ወልዲያ ላይ ሲደርስ፣ እስረኞቹን በኃይል ከእስር ለማስፈታት እየተንቀሳቀሰ ነው የሚል ክስ ቀርቦበት፣ በመከላከያ ትጥቅ እንዲፈታ ተጠይቆ ፈቃደኛ ባለመሆኑ ከፍተኛ ውጥረት ተፈጥሯል፡፡ ምሬ ተከቦ ድርድር እየተደረገ ባለበት ጊዜ፣በምስራቅ አማራ ፋኖ ሎጂስቲክስ ማዕከል እና ማሰልጠኛው ላይ መከላከያ ተኩስ ከፍቷል፡፡
ሆኖም፣ ከብዙ ድርድር በኋላ ምሬና ጠባቂዎቹ  በመጨረሻ ትጥቅ እንዳይፈቱ ተደርጎ ምሬ ወደ ቆቦ አምርቷል፡፡ በተፈጠረው ሁኔታ ግን የአካባቢው ህዝብ በከፍተኛ ሁኔታ ያዘነ እና የተቆጣ በመሆኑ ውጥረቱ ሊበርድ አልቻለም፡፡
 የምስራቅ አማራ ፋኖ ከሞላ ጎደል ባዶ እጁን ሆኖ ከህወሓት ጋር ከፍተኛ ፍልሚያ በማድረጉ በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት አለው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ከህወሓት ላይ የማረካቸውን የጦር መሳሪያዎች ታጥቆ ይገኛል፡፡ በጦር ግምባርም ከህወሓት ሰራዊት ጋር ተፋጥጦ የሚገኝና ታች ባሉት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ዘንድ ከፍተኛ አክብሮት እና መግባባት ያለው ነው፡፡ አሁን በፋኖ ላይ እየደረሰ ባለው ተጽዕኖ ህዝቡ ደስተኛ አይደለም፡፡ ከህወሓት ጋር ያለው ጦርነት ያላለቀ ከመሆኑም አኳያ፣ለአገር አደጋ ነው የሚል እምነት የብዙዎች ነው፡፡
በአሁኑ ሰዓት ከክርስትናና ከሙስሊም ማህበረሰብ የተውጣጡ የሃይማኖት አባቶች እና የአገር ሽማግሌዎች ከዚህ በኋላ በሁለቱ ኃይሎች መካከል ተኩስ እንዳይኖርና ሰላም እንዲሰፍን እየተማፀኑ ይገኛሉ፡፡
Filed in: Amharic