>

በድሉ ዋቅጂራ‘’…ካፈርሁ አይመልሰኝ አይነት ሌብነት‘’

በድሉ ዋቅጂራ

‘’…ካፈርሁ አይመልሰኝ አይነት ሌብነት‘’

 

@አዲስ ተስፋ

 

’ትልቅ ሰው ሲበላሽ ቅራሪ የለውም’’ እንዲሉ አንዳንዶች በመከበሪያቸውና ያላቸውን እውቀት በጥንቃቄ ማስተላለፍ ባለባቸው ጊዜ ድንገት የበሉበትን ወጭት ሲስብሩ ሲታይ አጄኤብ ያሰኛል

በድሉ ዋቅጂራ በሚጽፋቸው መጣጥፎቹ፣ በግጥሞቹና አልፎ አልፎም በድፍረት በሚሰጣቸው ፖለቲካዊ አስትያየቶቹ የሚታዎቅ ሰው ነበር ። ትንሽ ስጋ እነደመርፌ ትዎጋ ነውና ግጥምም ሆነ ልቦለዶች በመጻፍ ከአንባቢዎቹ ጋር ያስተዋወቀንውን የአማርኛ አባት የሆነውን ግዕዝን ለማውገዝ የሄደበት ርቀት ከዐማራ ጥላቻ የመነጨ ለመሆኑ ሌላ ዋቢ መጥቀስ አያስፈልግም።

እንደ በድሉ ያሉ ለማወቅ ከፈልጉ በደቂቃ ውስጥ በርካታ መረጃዎችን ማሰበሰብ የሚችሉ ሰዎች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የግዕዝን ቋንቋን አስፈላጊነት በመገንዘብ በርካታ ዓለማቀፍ ዩኒቨርስቲዎች ለምን ኮርሶችን መስጠት ጀመሩ ብሎ ምርምሮች ከመስራት ይልቅ ፈጥኞ የሞተ ቋንቋ ነው ይህንን የሞተ ቋንቋ ለማስተማር መወሰን ዋጋ የለውም ብሎ አስተያየት መስጠት እጅግ አስተዛዛቢ ነው።

እንደ ኤውሮውያን አቆጣጠር 2017 ዓም የግዕዝ ቋንቋ ኮርስን መስጠት የጀመረው የዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ ስለ ግእዝ አስፈላጊነት በወቅቱ ኮርሱን ይሰጡ የነበሩ ከፍተኛ ዓለማቀፋዊ ዩኒቨርሲቲዎች ሁለት ብቻ እንደነበሩ ከገለጸ በኋላ የሚከተለውን ብሏል።

“It’s an important language for the study of late ancient Christianity and early Islam. It’s the language of some of the earliest Judeo-Christian writings.  Its vocabulary can be found throughout the Quran.  Yet the classical language Ge’ez is little known beyond the Horn of Africa and taught at just two universities in the Western world.”

ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ ከምእራባውያን ዩኒቨርስቲዎች ግዕዝ ትምህርትን ሲሰጥ በወቅቱ ሶስተኛው ዩኒቨርሲቲ ነበር። ከዚያ በኋላ ግን በርካታ ዩኒቨርሲቲዎች ማስተማር ጀምረዋል። ከላይ ዩኒቨርሲቲው የጻፈውን እንዳየነው በቁራን ውስጥ በርካታ ቃላት የግእዝ ቅላት እንደሆኑ ይናገራል። ይህ ለእኔ አዲስ ነው ምክንያቱ በኢትዮጵያ የሚሰራው ቆሻሻ ፖለቲካ ግዕዝ የክርስቲያኖችና ክርስቲያኖች ብቻ የሚጠቀሙበት ቋንቋ ነው ስለሚል።

ሌሎች ግዕዝን የሚያስተምሩ የሚያስተምሩ ከፍተኛ ተቋማት የሚያስተምሩበትን ምክንያት በተለያየ መንገድ አስቀምጠዋል። አማርኛ በብዛት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ከሚናገራቸው ሴማዊ ቋንቋወች ሁለትኛ ደረጃ ላይ ያለ ስለሆነና የዚህ ቋንቋ መነሻ ደግሞ ግዕዝ ስለሆነ ሲሉ ሌሎች ደግሞ ግዕዝ ቀደምት ቋንቋ በመሆኑ ጥንታዊ የታሪክ የባህል የሃይማኖትና የፍልስፍና ሰነዶችን ለመመርመርና ለመራዳት ይላሉ። ከቴክኖሎጂና ከህክምና ጋር የተያያዙ ገሃድ ያልዎጡ ምስጢራዊ ሰንዶችም በግዕዝ መጽፋቸውን የሚያነሱ አሉ። ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን ግዕዝ ኢትዮጵያዊ ነን ከሚሉ ከእነ በድሉ ዋቅጂራ አመለካከት በተለየ ዓለም የተረዳው አንዳች ነገር እንዳለ ግልጽ ነው።

በድሉ ቢያንስ በሃገሪቱ አብላጫ ቁጥር ያለው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አገልጋዮች የሚቀድሱትም ሆን ይህንን አገግሎት ምእምኑ የሚካፈለው በግእዝ መሆኑን እያወቀና ቤተክርስቲያኗ ቢያንስ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ካህናት፣ ዲያቆናትና በርካታ ጳጳሳት እንዳሏት እያወቀ ከ25ሺህ ሰዎች በታች ናቸው የሚናገሩት ብሎ ለመናገር መድፈር ካፈርሁ አይመልሰኝ አይነት ሌብነት ነው።

Filed in: Amharic