እንኳን ለቃና ዘገሊላ በዓል አደረሳችሁ!

ዶ/ር መስከረም ለቺሣ

ለወደፊት… ከመከራችንና ከውድቀታችን ትምህርት ከወሰድን፥ ብዙ ነገሮቻችን ከተለወጡ፥ አእምሮአችንና መንፈሳችን በቃል ኪዳን አገርነት ታድሶ ልብ ከገዛን፡ በዓል አከባበራችን እውነተኛው ታሪካዊና መንፈሳዊ ገጽታው (utopian aspect) ይበልጥ ጎልቶ ይወጣል።

በአሁኑ ሁኔታችን፡ የጥምቀት በዓልን ስናከብር፡ ዜናው እንዲህ ይለናል፦

“የኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል፡ በአገራችን ልዩ ልዩ አካባቢዎች በሃይማኖታዊ ሥርዓት ተከብሮ ዋለ። በዓሉ፡ ለአገሪቱ ገጽታ ግንባታና ለቱሪስት መስኅብነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለው ሲኾን፡ በዚህ ዓመት የጎብኚዎች ቁጥር መጨመሩ ተገልጧል። ይኽም ለኢኮኖሚው ከፍተኛ እመርታን እንደሚያመጣ ይጠበቃል።….”

ይኽ ዜና፡ ኹሉን ነገር በገንዘብ የመተመን አእምሮ እንዲኖረን ተደርገን በያቅጣጫው የተሠራንበት የ dystopianism መርዝ አንዱ ውጤት ነው። በውጤቱም፡ ስለዶላር ብለው ቅርስ የሚሸጡ ብዙዎችን አፍርተናል። ምክንያቱም፡ ዓላማው የውጪ ምንዛሪ ከኾነ፡ ታቦቱን ተከትሎ ከመጮህ ይልቅ፡ ታቦቱን መሸጥ ይቀላልና።

ነገር ግን… ልብ ከገዛን፥ ወደቀልባችን ከተመለስን፥ ለልቦናችን ትንሣኤ ከኾነልን፥ ኢትዮጵያዊነት (“utopianism”) ምን እንደኾነ ከገባን… ጥምቀት በዓል ስናከብር፡ ዜናችን እንዲህ ይላል፦

“የአምላካችን፥ የፈጣሪያችን፥ የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀቱ በዓል፡ በዛሬው እለት በመላው አገሪቱ በልዩ ልዩ መንፈሳዊ ሥርዓቶች ተከብሮ ውሏል። በዓሉ፡ ኢትዮጵያውያን፡ ከንጉሣችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያለንን የልጅነትና የሕዝብነት ቃል ኪዳን ያደስንበት 2031ኛ ዓመት መኾኑን በማሰብ፡ በተለያዩ ቋንቋዎችና ባሕሎች፡ በርካታ መንፈሳዊ ትእይንቶች ተከውናነዋል። በአገሪቱ ታሪክ፡ ከሰው ዘር ውድቀት በጥምቀት እስከተገኘው ዳግም ልደት ድረስ፡ አምላካችን ከሰው ልጆች ጋር ያደረጋቸው ወሳኝ የቃል ኪዳን ምዕራፎችን የሚያስታውሱ ትእይንቶችና ንግግሮችም የእለቱ ደማቅ ክስተቶች ነበሩ።…”

እግዚአብሔር አምላኩ የኾነለት ሕዝብ ብፁዕ ነው። (መዝ 143፡15)

እንዲህ ያለ ሕዝብ ብንኾን፡ ዶላር ይዘው ሳይኾን፡ ልብ ይዘው የሚመጡ ጎብኚዎችን እንስባለን። እነሱም፡ የሚያዩትን ካዩና የተባለውን ኹሉ ከሰሙ በኋላ፡  “እንዳልጠመቅ የሚከለክለኝ ምንድነው?” ይሉናል። እኛም “በፍጹም ልብህ፡ በዳግማዊው አዳም በኢየሱስ ክርስቶስ የባሕሪ አምላክነት ብታምን፥ ዘረኝነትን ከልቦናህ ብታወጣ፥ በኢትዮጵያዊነትና በሰው ዘር አንድነት ብታምን ተፈቅዶልሃል” እንለዋለን። እሱም እዚያው ተጠምቆ፡ “ገብረ ሥላሴ” ይባልና፡ ማተብ ዐሥሮ፡ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ይዞ ወደአገሩ ይኼዳል። 

የቄሱ ዮሓንስ አገር ኢትዮጵያ (Utopia) ይህቺ ናት!

“Utopian Imagination” ማለትም ይኼ ነው። 

እናንተም አስቡ። Imagine አድርጉ! 

Imagine Imagine!

አብርሃም ሊንከን “The best way to predict the future is to create it” ያለው ወዶ አይደለም። 

እንኳን ለቃና ዘገሊላ በዓል አደረሳችሁ!

https://t.me/Utopiaprintingpress

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.