ሥፍራህን አትልቀቅ!

አንዱ የኔ ብጤ የዋህ አማኝ ከዕለታት አንድ ቀን ወደ ንስሃ አባቱ ይሄድና በምሬት እንዲህ ይላቸዋል ።

‘’አባቴ እኔ ዘወትር እፀልያለሁ። የእለት ውዳሴ ማርያም :መዝሙረ ዳዊትና ድርሳኑንም በየወቅቱ አዘወትሬ ብፀልይም አምላክ አልሰማኝም ብዬ እሁድ ጠዋት ወደቤተክርስቲያን እገሰግስና ኪዳኑን አድርሼ ከቅዳሴው ተካፍዬ ወንጌል ሰምቼ እመጣለሁ። ጥያቄዎች የማይመለሱት ለምን ይመስልዎታል ‘’ይላቸዋል ።

‘’አይ ልጄ አባቶቻችን ሁሉን በጥበብ ነውና የሚያስተናግዱት እግዚአብሔር ተለምኖ ብቻ ሳይሆን የሚያሻንን በቸርነቱ የሚሰጥ አምላክ ሰለሆነ ማማረር አይገባም ።
እንዴው ግን ሰንበትን እንዴት ታስቀድሳለህ ትንሽ ብትነግረኝ ‘’ ሲሉ የእሁድ ፀሎቱን አስታከው ሊመክሩት የፈለጉ የመሰለው አማኝ:-
‘’ አይ! እሁድማ ኪዳኑን በወንዶች በር በኩል :ቅዳሴውን በስተምዕራብ :ድርገት ላይ በደቡብ በኩል እንዲሁም ወንጌሉን ከቤተልሔም አጠገብ ነው የማሳለፍው’’  ይላቸዋል።
የነስሃ አባቱም ጥቂት አሰብ አደረጉና ‘’አየህ ልጄ …አንተ ፀሎቴ አልተሰማም ስተል ፀሎት አሳራጊው መልአክ ሲመጣ አንተ ቦታ ስተቀይር አሁንም ሲመጣ አንተ ቦታ ሰተቀይር መልአኩም እንዳይሰለችህ ፀሎት በጀመርክበት ቦታ ጨርስ። ሰፍራህን አትልቀቅ ።አንተ ከቆምክበት ስትለቅ ሌላው ሲፀድቅ ።አንተ ስትሸሽ ሌላው ሲቀበል ዘመን ያልፋልና ሥፍራህ ላይ ፅና!’’ አሉት ይባላል ።

በዚህ የሶስት አመት የአማራ ህልውና ትግል ውስጥ ብዙ ሰው የቆመበትን አንድ ጊዜ አይደለም ደጋግሞ እየለቀቀ በአጭር ጊዜ የታሰበው የነፃነት መንገድ እንዲወሳሰብ ተደርጓል ።ትግሉ ሲጀመር ከጫፍ እስከ ጫፍ በስሜት የተነሳው አማራ በጠራ አደረጃጀት እና ራዕይ የሚያሰባስበው ቢኖርና የዲያስፖራ አማራ ቢደራጅ በአንድ አመት ታሪክ መስራት የሚችል አቅም ቢኖረውም ተስፋ እንዳያደርግ ስፍራ በሚቀያይሩ የሰፈር አለቆች እየተማረረ ከድጋፍ እንዲርቅ ተገደደ።በጥቂት ሙሴም ነኝ እግዚአብሔርም ነኝ በሚሉ የማህበራዊ ሚዲያ ተሳዳቢዎች ተሸማቀው ከአማራ ትግል ራሳቸውን የደበቁ የትዬለሌ ናቸው ።የተወሰኑ ተሳዳቢ ግለሰቦች በሚዘውሩት የአማራ ዲያስፖራ አደረጃጀት ውስጥ ሰርገው የገቡና በማንነታቸው የማይታወቁ (AI) መሰል አጋፋሪዎችና ጥቂት ምንደኞች በፈጠሩት አሰጥ አገባ አማራው እንደማዬስማማ ተደርጎ ለጠላት የመግቢያ በር ተከፈተለት። አንዳንዶቹ የትግሉ ሞተርም ማርሽም እኛ ነን ብለው በሰፈር ተጠራርተው “እስክንድር ወይም ሞት”የምትል መፈክር ይዘው ብቅ ሲሉ እኛም አብረናቸው ዘመርን።

አርበኛ እስክንድር ስሜቱን ያዝ አድርጎ ‘’ከሁሉም በላይ የአማራ ትግል ይቀደም!’’ የሚል አቋም ሲይዝ የልብ አማካሪዎች ‘እኛ ነን’ ብለው መድረኩን ሞሉት። ካለ እነሱ ፈቃድ እስክንድርን ማግኘትም ሆነ ማነጋገር ሃጢያት እስኪመስል ድረስ ፎቶግራፍ እየለጠፋ አደባባዩን ሞሉት። ይህ ቀረርቶና ፉከራ ዛሬ በሌላ ሰው ተተክቶ “ቪቫ ስምንተኛው ንጉሳችን “የሚል T-shirt እያሳተሙ ያሉ ብዙ ሥፍራ ቀያሪዎች ተከስተዋል ።የአማራ ብሄርተኝነትን ገና በህፃንነቴ የለኮስኩት እኔ ነኝ ያሉና ሌላውን መተንፈሻ ያሳጡት መንደርተኞች 360 ዲግሪ ተገልብጠው ኢትዮጵያ ትቅደም ።ብሄርተኝነት ይውደም እያሉ ነው።ትናንት አፋህድ መነሻችን የአማራ ህልውና መድረሻችን የኢትዮጵያ አንድነት የሚል ማንፌስቶ ለማስተዋወቅ ከእኛ ውጪ አማራ የለም ብለው የቲክ ቶክ አደባባይን የሞሉት ሰፈርተኞች ዛሬ አፋህድ ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያ የሚለው ስህተት ነበር በማለት ስፍራ ቀይረው ተከስተዋል ።
እውነት እናውራ ካልን በዚህ የህልውና ትግል ውስጥ ትክክለኛው መስመር የአፋህድ ሰነድ ብቻ ነው።እንኳን ገና ወደፊት ለሚመጣ የብሄርተኝነት አደረጃጀት ይቅርና ወያኔና ኦነግ ከብሄርተኝነት ምን እንዳተርፉ የማይረዳ አማራ ካለ እሱ በራሱ ሞት ላይ ተስማምቷል ።ይቺ አንድ ሰው ከፊት ለማምጣት ሲባል የተቀነቀነች አጀንዳ ነገ አማራውን ለመበተን በህወሓት ህገ አራዊት ሰነድ መሰረት ሃገሪቱን አፈራርሶ አማራን በያለበት የሚያሳርድ የዘረኝነት አጀንዳ ናትና ወደ ሰገባዋ መልሷት።
አማራ እውነተኛ አደረጃጀት ፈጥሮ አፋህድ በሰጠን የማታገያ ሰነድ ጠላቱን ያሸንፋል ።አዲስ አበባ የምንሊክ ቤተመንግሥት ገብቶ የአምስት አመት የሽግግር መንግስት ይመሰርታል ።በዚህ ጊዜ የሽግግር ፍርድ ቤትና የፍትህ አካላት ይቋቋማል ።ለተበደሉት ፍትህ ለበደለኞች ፍርድ ይሰጣል ።አብይ አህመድና አዳነች አበቤ የዘረፉትን የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ንብረት ማስመለሰና ለተቀማው ፍተሃዊ ክፍፍል ይደረጋል ።በአማራ ህዝብ ላይ የፈረሱ ተቋማት በሙሉ ይገነባሉ ።የአማራ ህዝብ ለወደመበት ንብረት በሙሉ ካሳ ያገኛል ።ከኢትዮጵያውያን ጋር በመነጋገር እኩልነት ሊያሰፍን የሚችል አዲስ ህገ መንግሥት ረቂቅ እንዲዘጋጅና ህዝቡ እንዲመክርበት ይደረጋል ።ሁሉም የፋኖ ሃይል በሚፈልገው የሙያ ዘርፍና እውቀቱ ይሰማራል ።ጠንካራና ህዝባዊ የፀጥታ ተቋማት በፋኖ የሽግግር መንግሥት መሪነት ይቋቋማሉ ።ይህ እውን እንዲሆን አንተ ባመንክበት ቦታ ላይ ቆይ ።አማራ እንዲያሸንፍ ካሰብክ ስፍራህን አትልቀቅ ?
“…..ቆመ ማእከለ ባህር” ባህር አየች ሸሸችም ዬርዳኖስም ቆመ።
ከአዳባይ
ጥር 11 ቀን 2018

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.