የአፋህድ ጥቅምት 20፣ 2018 ወቅታዊ መግለጫ
በኦሮሚያ ክልል ዳግም የተቀሰቀሱ የጄኖሳይድ ግድያዎች እና ቅስቀሳዎች የዓለምን ትኩረት ይሻሉ!
በኦሮሚያ ክልል ፣ ምሥራቅ አርሲ ዞን፣ በጥቅምት ወር 2018 ዓ.ም ብቻ የ 2 ዓመት ሕፃን እና የ75 ዓመት አዛውንትን ጨምሮ 25 ንፁሃን በብሄር እና ኃይማኖታዊ ማንነታቸው ሳቢያ በግፍ ተገድለዋል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አባቶች ሰሞኑን ይፋ ባደረጉት ሪፖርት፣ ችግሩ የቆየ ቢሆንም፣ ከዚህ ቀደም ሰላማዊ ተብለው በሚታሰቡ አካባቢዎች እየተስፋፋ ይገኛል። በዚህም መሠረት፣ በጥቅምት ወር ከተፈፀሙት ጥቃቶች መካከል የሚከተሉት ይገኛሉ፦
1ኛ — በኦሮሚያ ክልል፣ በአርሲ ዞን፣በጉና እና መርቲ ወረዳዎች አዋሳኝ ጥቅምት 14 ለ15 አጥቢያ 17 ሰዎች በብልፅግና ጄኖሳይደር ታጣቂዎች ተገድለዋል።
2ኛ—በኦሮሚያ ክልል፣ በአርሲ ዞን፣ በሽርካ ወረዳ፡ ጥቅምት 17 ለ18 አጥቢያ ሌሊት 3 ሰዎች በቤታቸው በብሄር እና ኃይማኖታዊ ማንነታቸው ሳቢያ በብልፅግና ጄኖሳይደሮች ታጣቂዎች ተገድለዋል።
3ኛ— በኦሮሚያ ክልል፣ በአርሲ ዞን፣ በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ፡ ጥቅምት 18 ለ19 አጥቢያ ሌሊት 5 ሰዎች በብሄር እና ኃይማኖታዊ ማንነታቸው ሳቢያ በብልፅግና ጄኖሳይደር ታጣቂዎች ተገድለዋል።
በኦሮሚያ ክልል በእንደዚህ ዓይነት ማንነት ተኮር ጥቃቶች ውስጥ በአብዛኛው የመንግሥት መዋቅሮች ተሳትፎ እንዳላቸው ባለፉት 7 ዓመታት ተሞክሮ በተጨባጭ የተረጋገጠ ሐቅ እንደመሆኑ መጠን፣ የኢትዮጰያ መንግስት ገለልተኛ የማጣራት ምርመራ ሊያካሄድ አይችልም።
ለዚህ እውነታ አንድ ማሳያ የሚሆነው፣ በኦሮሚያ ክልል፣ ምዕራብ ሸዋ ዞን፣ የኖኖ ወረዳ አንድ ኃላፊ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እና አመራሮች ባሉበት መድረክ ሰሞኑን ያስተላለፈው የጄኖሳይድ ጥሪ እና ዛቻ ነው።
የወረዳ ኃላፊው በቅርቡ ወታደራዊ ስልጠና ተሰጥቷቸው ለተመረቁ ወጣቶች ባደረገው ንግግር የሚከተለውን ብሏል :-
“የአማራ ፅንፈኛ እና መንገደኛ፣ (ወደ ወረዳችን) አርሶ ሊበላ መጣ እንጅ፣ ውስጣችን ቁጭ ብሎ ታገለን አላልነውም። መታገልም አይችልም። አይፈቀድለትም። እንደዚህ ዓይነት መብትም የለውም። እንደዚህ ዓይነት ታሪክም እኛ ጋር የለውም።
ስለዚህ ለእነሱ ያለንን ተቃውሞ መግለፅ የምንችለው (በቃላት) በመቃወም ብቻ ሳይሆን፣ ታጥቆ የሚወጋንን ገድለን በማሳየት ነው።
እዚህ ከፊት ለፊቴ ያላችሁት ወጣቶች፣ ይህን ኃይል ባለበት ሳይንቀሳቀስ የምትጨርሱበት፣ በእጃችሁ የያዛችሁትን ዱላ፣ ፈጠሪ ካለ፣ በቅርቡ ወደ ክላሽ ይቀየርላችኋል።
ክላሽ ግዙ። ጥንድ በሬ ካለህ አንዱን ሽጠህ ግዛ። ነጋዴ ከሆንክ ከንግድህ ቀንሰህ ክላሽ ግዛ። ክላሽ ያለው ይከበራል፣ ያስከብራል።
እናንተ ግዙ እንጂ እኛ ከጎናችሁ ነን። ፓሊሶችም አሉ፤ ህጋዊ እናደርግላችኋለን።ያደረጉብንን እጥፍ አድርገን እናሳያቸዋለን ” በማለት በአገዛዙ አይዞህ ባይነት ጎረቤት በጎረቤት ላይ እንዲዘምት ግልፅ ቅስቀሳ አድርጓል። (ቪዲዮውን አያይዘናል።)
ስለዚህም፣ በቀጠናው ያሉ የሚሊዮኖች ህይወት አደጋ ላይ የወደቀ መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት፣ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በአፋጣኝ ጉዳዩን በገለልተኝነት አጣርቶ እንዲደርስላቸው እናሳስባለን። በመንግስት ኃይሎች የሚፈፀሙ ማንነት ተኮር ግድያዎች የአንድ ሀገር የውስጥ ጉዳይ ሳይሆኑ፣ የመላው ዓለም ጉዳይ ናቸው።
በተጨማሪም፣ ይህን እኩይ ድርጊት ኦሮሞን ጨምሮ መላ ኢትዮጰያዊያን ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን እንዲያወግዙት እና እንዲታገሉት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
ክብር እና ሞገስ ለሰማዕታት!!!
ድል ለአፋህድ እና የአማራ ፋኖ ሁሉ!!!
ድል ለአማራ ህዝብ!!!
ድል ለኢትዮጰያ ህዝብ!!!
