ወልቃይትና ራያ የአብይ አህመድ ATM ካርዶች!

ህወሓት እና ኦነግ (መለስ ዜናዊና ሌነጮ ለታ) በጫካ ሆነው ያሰናዱት በ1983 ዓ.ም የተፈጨውና በ1987 ዓ.ም በህገ አራዊት የተቦካው አማራን የመበታተን ኢትዬጲያ የምትባል ትልቅ ሃገርን በውስን ዘውጌዎች በመከፋፈል የመገነጣጠል ሴራው መጋገር የተጀመረው ከዛሬ ሰባት አመት በፊት አብይ አህመድ የሚባል ፀረ አማራና ፀረ ኢትዬጲያውያን ፋሸስት ወደ ምንሊክ ቤተመንግሥት ከገባ በኋላ ነው። ኦህዴድ (ኦነግ) ደራ ላይ በደርግ ውድቀት ዋዜማ በምርኮኞቹ አባዱላና ኩማ ደመቅሳ ከተመሰረተ ጀምሮ የመለስ ዜናዊ ህልፈት እስከታወጀበት 2004 ዓ.ም ድረስ እዚህ ግባ የሚባል የፓለቲካ መድረክ አልነበረውም። ይልቁንም በአውራጃ እየተከፋፈለ ከአማራ ህዝብ ላይ ተቀንሶ የተሰጠውን የተንቦረቀቀ ክልል በአግባቡ መምራት ስለማይችል አብዛኞቹ የኦሮሚያ አካባቢዎች ላይ የህወሓት ካድሬዎች በበላይነት አመራር ሰጪዎች ነበሩ።ኦህዴድ ልክ እንደ ወንድሙ ብአዴን የኦነግ አባልና ደጋፊ ናቸው ያላቸውን የኦሮሞ ወጣቶች በማሰር በማሳደድና በመግደል ለወላጅ አባቱ ህወሓት ታማኝነቱን ያስመሰክር ነበር።በወቅቱ አብዛኛው የኦህዴድ ካድሬ መደበኛ ሥራው መሬት መደለልና መቸርቸር ብቻ ነበር አዳነች አበቤና ሽመልስ አብዲሳ ንብረቱን በጠራራ ፀሐይ አፍርሰው ያባረሩት 112 ሺህ የአዲስ አበባ አማራ ራሳቸው የኦህዴድ ሰዎች ደላለና ሻጭ ሆነው አማራው በህጋዊ መንገድ ገዝቶ ቤት የገነበባቸው ይዞታዎች ናቸው።አንዳንዶቹ ቦታዎች ሆነ ተብሎ እሰከ አራት ጊዜ ካሳና ምትክ ተወስዶባቸዋል።ይህን ዘግናኝ ግፍ እድሜ ይስጠን እንጂ ከድል በኋላ በትላልቅ መድብሎች እንተርከዋለን።ለመጪው የአማራ ትውልድም የጠላቶቻችንን አውሬነት እናሳይበታለን።በጫካ ያለው ኦነግም በሽግግሩ ወቅት በመለስ ዜናዊ ተሸውዶ ወደ 21 ሺህ ሰራዊቱን ሰብስቦ ካስፈጀ በኋላ በየቦታው ተበታትኖ አመራር ነን ያሉትም በኤርትራና በአውሮፓ መደበኛ ኑሯቸውን እየኖሩ ባለበት ነው እንግዲህ የመለስ ህልፈት የተከሰተው ።

የዚህ ማስታወሻ ፀሐፊ ማጎሪያ ቤት በነበረበት ወቅት ለመለስ ዜናዊ መታሰቢያ ተብሎ ለ13 የኦነግ ደጋፊ ተከሳሾች በነፍስ ወከፍ አንድ አንድ ጧፍ ሲታደል ሁሉም በአንድ ድምፅ ‘’አናበራም’’ በማለት ሰብስበው ለእኛ ሰጡንና የዘወትር ፀሎት ላይ አበራነው ።ይህቺን ሁኔታ እኔና አብሮኝ የነበረ አንድ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የህግ ባለሙያ በሰፊው ተወያየንበት። ከዛች ቀን በኋላ ኦህዴድ የበለጠ ጥርስ እያወጣ ህውሃት ወደ መቀሌ መሰደዷ እንደማይቀር የመታጠፊያ መብራት መሆኗን ተስማማን።ይባስ ብሎ የኦነግ ሰዎች ዳርፋር በሚባለው አንደኛ ቤት ታሰረው በአማርኛ የህወሃትን መሸነፍ በአደባባይ መናገር :ፍርድ ቤት ችሎት ላይ መሳደብ ስልክና አደንዛዥ እፅ እሰከማስገባት ደረሱ። ኦህዴድ ከጫከውና 50 አመት አንዲት መንደር ላይ ተታኩሶ ከማያውቀው የነ ዳውድ ኢብሳ ማሽላ ቆራጭ ሰራዊት ጋር በሻዕቢያ መልካም ፈቃድ እየተነጋገረ ድምፅ ማሰማት ጀመረ።ወንድሙ ብአዴን በበኩሉ በሁለት ጎራ ተሰልፎ አቅም ለማጠናከርና የህዝቡን ብሶት በመቀስቀስ እንባ አባሽ ለመምሰል ብዙ ተጋጋጠ።በመጨረሻው እንባ አበባሽ ሆኖ ወደ ኮርቻነቱ ተመለሰ እንጂ።

ከላይ በጥቂቱ የነካካሁት ሃሳብ የአብይ አህመድ ገዳይ ቡድን ዛሬ ጀግና ጀግና ለመጫወት የሚውተረተረው የመለስ ዜናዊ አምባገነን የዘረኝነት ሥርዓት በየቦታው የቀብራቸው ፈንጅዎች ለአብይ እንደ ATM (automatic teller Machine ) ጊዜና ሁኔታዎችን እየጠበቀ እንዲመነዝር እድል አመቻችቷል ለማለት ነው። የወለጋ አማራ የተጨፈጨፈው ።በበደኖ በአርባጉጉ :በሐረር በጅማ በአምቦ በደራ :በወልቃይት በራያ በመትከል :በአዲስ አበባና በሻሸመኔ እንዲሁም በሌሎች በርካታ አካባቢዎች አማራው እንዲፈናቀል እንዲገደል :ሃብት ንብረቱ እንዲዘረፍና ሃገር አልባ እንዲሆን ምንጩ ህወሃትና ኦነግ (ኦህዴድ ) ናቸው ።

ዛሬ በወልቃይት አማራ ላይ የተከፈተው ጦርነት እነዚህ ሃይሎች ሲፈልጉ የተጣሉ መስለው ካልሆነም አጋርነት መስርተው አማራንና የአማራ የሆነውን ማጥፋት እንደ ድርጅት የተዋቀሩበት አላማቸው ነው።በስም ይለያያሉ እንጅ በፅንሰ ሃሳብ ደረጃ:-
-ህወሃትም ኦህዴዴም (ብልፅግና ) ተገንጣይ ናቸው
-ሁሉቱም አማራን በጠላትነት የፈረጁ ናቸው
-ሁለቱም የኢትዮጵያን ሃብትና ንብረት እየዘረፉ ኢትዮጵያን ይጠላሉ
-ሁለቱም ትልቋን ሃገር እየመሩ ትናንሽ አውራጃ ለመመስረት ይታገላሉ
-ህወሃትም ኦህዴድ ኦነግም የሚወክሉትን ህዝብ በስሙ ይዘርፉበታል እንጂ አያውቁትም
-የሁለቱም ድርጅቶች አመራሮች በራስ መተማመን ስለሌላቸው የመጨረሻውን ስልጣን ይዘው እንኳን የአማራን ህዝብ ይፈሩታል ።ይጠሉታል ።በማይድን በሽታ መለከፍ ይሏል እንዲህ አይደል?።
የሰሞኑ የወልቃይት ወረራና የአብይ አህመድ ሚሊሻዎች ከራያ መውጣት ለአማራ ፋኖ ግልጽ መልእክት ይመሰለኛል ።ከላይ ለማመላከት እንደሞከርኩት እነዚህ በሚዲያው ላይ ጠላት ለመመሰል የሚሞክሩ የአማራ ጠላቶች ውስጣዊ አንድነት ፈጥረው አማራውን በየአቅጣጫው ለመምታት የተጠነሰሰ ሴራ በመሆኑ በቂ ወታደራዊ ዝግጁነት እና በጥበብ አሸናፊ ሆኖ ለመውጣት መዘጋጀትን ይጠይቃል ።በአንድ በኩል አማራውን እርስ በእርሱ ለማገዳደል ከወልቃይት አማራ ጋር እንድንታኮስ በሌላ በኩል የፋኖ ሃይል በየቦታው ተከፋፍሎ ወደ አራት ኪሎ የሚያደርገውን ጉዞ ለማስቆምና ውጊያውን በሙሉ በአማራ ክልል ላይ ለማቆየት የተጠና ሴራ መሆኑን መገንዘብ ብልህነት ነው ።የወልቃይት ጉዳይ ከአማራው ህልውና በላይ ተሻጋሪ ፍላጎትና በተቃራኒ አቅጣጫ የተሰለፋ የአፍሪካ የአረቡ አለምና የእነ አሜሪካም ጭምር እጅ እንደገባበት ከሳምንት በፊት የአማባሳደሩን ጉብኝትና የትናንቱን የምክትል ውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩን የአዲስ አበባ ጉዞ ማጤን ይጠቅማል ።በሌላው አቅጣጫ ደግሞ አብይ አህመድ ከምርጫው በፊት ለአጀንዳ የሚሆን ድል እየናፈቀ ሰለሆነ በህወሓት ሰበብ ወደ ኤርትራ ድንበር ትንኮሳ በማድረግ ቀጠናውን የበለጠ የጦርነት አውድማ ሊያደርገው ስለሚችል የአማራ ህዝብና የፋኖ ሰራዊት በቂ ዝግጅትና የሁኔታዎች ትንተና ማድረግን ይጠይቃል ።ህወሃት በዚህ ጦርነት ተሳክቶላት ወልቃይትን መያዝ ከቻለች በማግስቱ ኦህዴድ ኦነግ የራሱን ሃገር ወደማወጅ ሊያመራ እንደሚችል ቀድሞ ማሰብ ብልህነት ነው ።ፋኖ በውስጡ ያሉ ጥቃቅን ጉዳዮችን በይደር ማቆየት :አማራን በአማራ ለማስፈጀት የተዘረጋውን የሴራ መረብ በጥንቃቄ በመበጣጠስ አብይ አህመድ በየጊዜው የሚስባቸውን ካርዶች በሥር ነቀል ለውጥ ማጥፋት ወደሚያስችል አቅጣጫ መጓዝ ይኖርበታል ።ከጎረቤት ሃገራት ጋር የሚከወኑ ድንበር ዘለል ጉዱዬችን በትዕግሥት መፈተሽና የአማራ ህልውና ትግል እንዳይቀለበስ መጠንቀቅ ያሻል እላለሁ ። ሌላው ለእኛው በእኛው ይለቅ?

ከአዳባይ
ጥር 21/2018

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.