«ተከዜ ለሁለታችንም ተፈጥሯዊ ወሰን ነው!»

የኮከብ ልደት

የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት አማራ ምሁራን ማኅበር

(ሐምሌ 19/2018 ዓ.ም.) ያወጣው ይፋዊ መግለጫ

የትግራይ ልሂቃን፣ ምሁራንና የተቃዋሚ ፖለቲካ መሪዎች የትግራይን ውስጣዊ ቀውስ ወደ ውስጥ ተመልከተው እንዲፈቱና አውዳሚ የጦርነት ዝግጅትን በተግባር እንዲቃወሙ ጥሪ አቅርቧል!

ከመግለጫው የተወሰዱ 4 ቁልፍና ወሳኝ መልእክቶች፦

​1️⃣ ተፈጥሯዊ ወሰናችን ተከዜ ነው!

​”የወልቃይት ጠገዴ አማራ ሕዝብ፣ የራሳችንን አሳልፈን አንሰጥም አልን እንጂ የማይገባንን ለሁለታችንም ተፈጥሯዊ ወሰን የሆነውን ተከዜ ወንዝን አልፈን አልጠየቅንም፡፡ እኛ የናንተን ትግራዋይ ማንነት እና ወሰን እንደምናከብረው ሁሉ እናንተም የኛን አማራዊ ማንነት እና ወሰን ልታከብሩ ይገባል፡፡”

​2️⃣ የሰላምና የአብሮነት ባህል፦

​”የወልቃይት-ጠገዴና ጠለምት አማራ ሕዝብ እንኳንስ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ከሚጋራቸው ሕዝቦች ቀርቶ ከጎረቤት ሀገራት ወንድም ሕዝቦች ጋርም በሰላም፣ በፍቅርና በመከባበር መኖር የሁልጊዜም ምርጫው፤ የጥንት ታሪኩም አካል ነው፡፡”

​3️⃣ ችግሩ ውጫዊ ሳይሆን ውስጣዊ ነው — ሕወሓትን «ኦዲት» አድርጉ!

​”የትግራይ ሕዝብ ወደ ውስጡ በማየት ግማሽ ክፍለ ዘመን በላዩ ላይ ተጣብቆ የቆየውን ሕወሓትን ኦዲት ሊያደርገው ይገባል! ተጠያቂነትን የማያውቀው የዚህ ድርጅት አሰራር የትግራይን ሕዝብ ዘመድ እያሳጣው፣ ዋጋ እያስከፈለው ይገኛል፡፡ እንደ ሰላም ወዳድ ጎረቤት ምክራችን የትግራይ ልሂቃን፣ ምሁራን እና የተቃዋሚ ፖለቲካ መሪዎች የትግራይን ውስጣዊ ቀውስ ወደ ውስጥ በመመልከት እንጅ ውጫዊ በማድረግ የሚገኝ መፍትሔ፤ የሚቀየር ሁኔታ የለም፡፡”

​4️⃣ የጦር ወረራ ከአሸባሪነት የተለየ አይደለም!

​”የጦር ወረራ ከአሸባሪነት እና ከአገር አፍራሽነት ተግባር ተለይቶ የሚታይ አይደለም፡፡… በመሆኑም በትግራይ ሕዝብ ስም የሚነግዱ የጥፋት ቡድኑ አመራሮች፣ እያደረጉት ያለው አውዳሚ የጦርነት ዝግጅት፣ በተግባር በመቃወም፤ አውዳሚ ጦርነቱን ለማስቀረት ከወገናችሁ የአማራ ሕዝብ እና ቀሪው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን በመሰለፍ ታሪካዊና ሞራላዊ ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡”

መደምደሚያ

የወልቃይት-ጠገዴና ጠለምት አማራ ሕዝብ በሰላምና በመከባበር መኖር የሁልጊዜም ምርጫው ቢሆንም፤ በደሙ ያስከበረውን ማንነቱንና ተፈጥሯዊ ወሰኑን ግን አሳልፎ አይሰጥም!

​(ምንጭ፦ የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት አማራ ምሁራን ማኅበር ይፋዊ መግለጫ — ሁመራ-ጎንደር ኢትዮጵያ)

የኮከብ ልደት @Amhara_wisdom On X

ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.