“ኢትዮጵያ ዉስጥ ከእንግዲህ የኣንድ ብሄር የበላይነት ኣክትሞለታል። #የኣማራ ትምክህት በሃይል እገዛለሁ ቢል፣ #የኦሮሞ ጠባብ በሃይል እገዛለሁ ቢል፣ የትግራይም እንዲሁ ቢል በፍጹም ተፈጻሚነት የለውም፡፡ … ሃይል ተጠቅሜ የበላይነት ኣረጋግጣለሁ የሚል ግብዝ ሃይል ካለ እጣ ፈንታው ሽንፈት ነው። ኣንድ ኣድርጌ ጨፍልቄ እገዛለሁ የሚል ህልመኛ ቢመጣ እስከ ሞት እንዋጋዋለን እንጂ ኣይታሰብም። ቁርጡን ይወቅ:: ግፋ ቢል ሃገሪቱ ወደ መበታተን ያደርሳት እንደሆነ እንጂ ኢትዮጵያ ዳግም የገዢዎች መፈንጫ ልትሆን ኣትችልም። መገነጣጠል ድግሞ ኣማራጭ ሊሆን ኣይችልም፣ ተያይዘን መጥፋት ነው የሚሆነው። የሁላችን እጣ ፈንታ ኣንድና ኣንድ ነች.. የተበላሸ ነገር ካለ እያስተካከልን በጋራ እድገት ላይ መስራት። ከዛ በዘለለ ተያይዞ ጥፋት ነው።”
#ኣባይ_ፀሃየ ስለ ወቅታዊ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ጉዳይ ኣስመልክተው በትግሪኛ ከተናገሩት ተቀንጭቦ የተወሰደ