>

አደዋን የካደ የአደዋ ሰው  (ሚሊዮን አየለች) 

በሀገራችን አባባል ‹‹ሙት ወቃሽ አታድርገኝ›› ይባላል እግርግጥ ነው የሞተን ሰው ከሞተ በኋላ መውቀሱ ጥቅሙ የዚህን ያህል ነው እንደ መንፈሳዊ ሆነን ስናስበው ሟቹ አንደኛውን በሰራው ስራ ለመጠየቅ ወደ ፈጣሪው ስለሄደ የሱ ነገር አብቅቶለታልም ሰለሚባል መውቀሱ አይጠቅምም ይባላል ፍርዱን ለፈራጁ ስለተሰጠ ፡፡
እኛን ግን ይህንን አባባል አንድንጥስና መለስ ሳይሞት በፊት የሰራቸው መርዘኛ ስራ ለትውልዱ መቃቃርንና መጠራጠርን ብሎም ኢትዮጵያዊነቱን እንዳያምን ሁሉም ብሄሮች ባዕድነት እንዲሰማቸው በማድረጉ ይህንን ስህተት መቅረፍ እስክንችል ደግመን ደግመን መንፈሱን ሳይቀር እንወቅሰዋለን፡፡
አሁን አሁን ላይ ለ27 ዓመት ሙሉ ዓደዋን ከነመኖሩ የረሱት የህውሀትና የኢህአዲግ ሹማምንቶች አደዋን ታላቁን የኢትዮጵያውያንን ድል ለፖለቲካ መጠቀሚያቸው ለማድረግ ደፋ ቀና ሲሉ ስናይም ስለ ታሪክ የነበራቸውን ሀሳብ እያጣቀስን ይህንን ግዙፍ በዓል በዓሉን ለሚያከብሩት ኢትዮጵያውያን ተውልን እንላለን አደዋን ለፖለቲካ ፕሮፖጋንዳ ማስፈፀሚያ አታድርጉት፡፡
የአደዋ ድል ለትግራይ ህዝብ ምኑ ንው?
ጠቅላይ ሚኒሲትር መለስ ዜናዊ በሕይወት በነበሩበት ጊዜ በአንድ ወቅት የተናገሩት ልብ አቁስል ንግግር እንዲህ በማለት ነበር የጀመሩት
<<የየአክሱም ሀውልት ለወላይታው ምኑ ነው? የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስትያናት ለደቡብ ህዝቦች ምኑ ነው የጎንድር ነገስታት ገግንቦች ለኦሮሞው ምኑነው >> በማለት በታሪካችን በቅርሳችን በአባቶቻችን ታላቅነትና ገናናነት የምንኮራውን ህዝቦች ታሪክ አልባ ማንነት አልባ ሀገር አልባ አድረጎ እንዳሸማቀቀን ግልጽ ነው።
የአድዋ ድል ለትግራይ ህዝብ ምኑ ነው? ቀላል ነው ለትግራይ ህዝብ አድዋ ድልማለት  የማንነቱ መገለጫ ደምና አጥንት የከፈለበት ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር በአንድ በመሆን ድልን የተቀዳጀበት አኩሪ ታሪኩ ነው አበቃ ለትግራይ ህዝብም ሆነ ለሌሎች ኢትዮጵየያኝ የአዸዋ ድል ታላቅ ታሪካቸው ነው ፡፡
ነገር ግን በዚህ ጽሁፌ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሞተ አመታት ቢቆጠሩም ነገር ግን አሁንም የህውሀት ታጋዮች ጥልቅ ጉድጔድ ቆፍረው ስላልቀበሩት እኔም እሱንና ጉምቱ የህውሀት ባለስልጣኖችን አንስቺ ስለአድዋና ሰለሀገሪቷ  ባላቸው አመለካከት ላይ በዚህ ፅሁፍ ልወቅሳቸው ፈለኩ አስቀድሜ ግን ህውሀቶች ሰውዬውን ኢትዮጵያውያን ዳግመኛ እንዳያነሱትና እንዳያስቡት ጭምር ጥልቅ ጉድጓድ ቆፍረው ቢቀብሩት መልካም ምክሬን እገልፅላቸዋለሁ ፡፡
መለስ የአድዋን ድል ብቻ አይደለም የካደው የመላው ኢትዮጵያን ታሪክም ጭምር ነው የካደው ከ3000ሺ ዓመት በላይ ተከብራ ተፈርታ ሉአላዊነቷ በልጆቿና በአምለኳ ተጠብቆ የኖረችውን ሀግር እንዲህ በማለት ነበር የቅጥፈት ወሪውን የነገረን
<<ኢትዮጵያ የሶስት ሺ አመት እድሜ ጠንካራ ታሪክ የላትም በአንድ መእከላዊ መንግስት መተዳደር ከጀመረች ከዳግማዊ ሚኒሊክ ወዲህ 100 ዓመት አይሞላትም>> ታላቋ ኢትዮጵያ በሚኒሊክ የተፈጠረች ገና 100 ዓመት የማይሞላት ጨቅላ አድርጎ ሲነግረን ሲያስነግረን ቆይተል
የኢርትራ መሬትና ህዝብ ከእናት ሀገሯ ጋር ብዙ ሺ አመታት እንዳልኖረች ሁሉ ኢትዮጵያን  በዳይና ጨቜኝ ዐዽርጞ ለዐለም ሀገራት ኤርትራ የኢትዮጵያ ቅኝ ተገዥ ነበረች ብሎ ማስቀመጥ የለየለት እብደትም ውርደትም ጭምር ነው ኤርትራዊያን ለኢትዮጵያ ነጻነት የተጋደሉ ደማቸውን ያፈሰሱ አጥንታቸውን የከሰከሱ በድንበር በኩል ይመጡ የነበረውን ጥላት ለብዙ አመታት አሳፍረው የመለሱ ጀግኖች ኢትዮጵያውያን መሆናቸው የኢትዮጵያኝ ታሪክ እያወቀ ያጣመመውም አቶ መለስ በደንብ ይረዳዋል።።
እንዳለመታደል ሆኑ የኢትዮጵያ የሰሚኑ ክፍል ከጥንት ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ጦርነት የማያጣው ለነፃነትም ከውጪ ወራሪዎች ጋር በመፋለም የሀገራቸውን ዳር ድንበር ሲያስከብሩ ማዕከላዊውን መንግስት ለማሸበርም ነውጥ ለመፍጠር ለጦርነት ቀጠና የሚመርጡት የህኛውን የሰሜኑን ክፍል ነው በእርግጥ የሰሜኑ ክፍል በመልካ ምድራዊ  አቀማመጥ በተለይ ገዢ መሬት ይዞ ለተዋጋ አመቺ  መሆኑን በተለያዩት ጊዜ የተደረጉጥ ጦርነቶች ታሪኮቻቸውን አስነብበውናል፡፡
ይህ ሁሉ ቅጥፈት አልበቃቸው በሎ የአድዋን ድል ከመላው ኢትዮጵያ ከኦሮሞው ከሀድያው ከወላይታው ከጉራጊው ብሎም ከሌሎች ኢትዮጵያውያኖች ለመለየት ያሴሩት ሴራ እጅግ በጣም አናዳጅም አሳፋሪም ጭምር ነው
የአደዋ ድል ፈረንጆች እንደሚሉት የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በባርነት ለሚማቅቀውም ለመላው አፍሪቃ ድልም ጭምር ነው በላዩም በቀኝ  ለተገዙት ሌሎች የዓለም ሀገራት ቅኝ ገዢዎቻቸውን ማሸነፍ የሚችሉበትን ታላቅ ጥበብ እና በራስ መተማመን ያስተማረ ታላቅ ድል ነው
ከአደዋ ድል በፊት ሌሎች በቅይ በቅኝ ግዛት የተገዙት ሀገራት ባርነትን እንደፀጋ ተቀብለው ይኖሩበት የነበረበት ዘመን ነው ለነጮች የቅኝ ጌታቸው ፈጣሪያቸው የሰጣቸው ፀጋ መግዛትን ማንበርከክን ጥቁሮች ደግሞ ሲፈጠሩም ለመገዛትና ለባርነትና ለውርደትም ጭምር ሆነው የተፈጠሩ እስኪመስላቸው ድረስ አሜን ብለው የተቀበሉበት ጊዜ ነበር
ይህን ጊዜ ነው የአድዋ ድል ለብዙ ጥቁርና በባርነት ለተያዙት ህዝቦች የነፃነትን ፋና ወጋገን የበራላቸው ከዛ ጊዜም ጀምሮ ነው ጥቁሮች እራሳቸውን ችለው መኖር እንደሚችሉ ሀገር መምራት መስተዳደር እንደሚችሉ በጥልቀቅ ማስብ የጀመሩት
ነገር ግን መለስና የመለስ ሹማምንቶች አድዋን ከአፍሪቃም ከአለም የባሮች ድልም ብቻ ሳይሆን የነጠሉት ከኢትዮጵያዊያንም ጭምር ነው በአንድ ወቅት ላይ አቦይ ስብሃት ነጋ ከነጋድራስ ጋዜጣ ላይ በሰጡት ቃለ ምልልስ ስለ አድዋ ድል ያላቸውን አስገራሚም አናዳጅም አስተሳሰብ እንዲህ በማለት ነበር የተናገሩት
<<አራዳ ላይ ያለው የአፄ ሚኒሊክ ሀውልት የአድዋ ማስታወሻ አይደለም ሊሆንም አይችልም ቦታውንም ሆነ ስሜቱን አዲስ አበባ ላይ አድርጎ ማሰብ ሀገር መካድ ነው ህዝብና ሀገር ክደህ ሀገር አትገነባም የኛ መሪዎች በዛን ጊዜ ስህተት አልነበራቸውም ማለት አይደለም ቀደም ሲል ባይሳሳቱ ኑሮ ኤርትራ በጣሊያን አትወሰድም ጅቡቴም ለፈረንሳይ አትሰጥም ነበር…>> እንዴት ያለ ጉድ ነው የአቦይ ትንተና አሁንም አርጅተው የዘር ጥላቻ አለቀቃቸውም እስኪ መጀመሪያላይ ያሉትን አንዴ ይድገሙልኝ<<አራዳ ላይ ያለው የአፂ ሚኒሊክ ሀውልት የአድዋ ማስታወሻ አይደለም ሊሆንም አይችልም >> ምን ጉድ ኖት አቦይ መላው ኢትዮጵያ አደዋ ላይ ሄዶ ለመዋጋት አራዳላይ እንደተሰበሰቡ ዘንግተውት ነው ወይንስ ታሪኩን አላነበቡም ሚኒሊክም ቢሆን ወደ አድዋ ይዘውት የሄዱት የአራዳውን የጊዮርጊስን ታቦት ጭምር መሆኑ ደግሞ ለማንም የተሰወረ አይደለም እንደየውም የአድዋውን ድል የተነተነው አንድ እንገሊዛዊ ፀሀፊ ይመስለኛል <<አፄ ምኒሊክና የአድዋ ድል>> በሚል መጽሀፉ << ሚኒሊክ የጊዮርጊስን ታቦትና የማሪያምን ታቦት(ታቦተ ፂሆንን) ይዘው መዝመታቸው እግዚአብሔር በግልፅ ለምኒሊክና ለኢትዮጵያ ህዝብ መወገኑን ያሳያል>> በማለት አስቀምጦታል እንግዲህ ይሄነው ሀቁ አቦይ ግን ግድ የለም ይቀጥሉ አቡይ አላቌርጦ
<< የእከሌ ወይም የራስ እከሌ ሳይሆን የአድዋ ድል የመላው ኢትዮጵያዊ ድል መሆኑን ለማሳወቅ እየጣርን ነው ድሉን በትክክል ማሳወቅ ካልተቻለ ከባድነቱ እንደቀጠለ ይቆያል ቦታው ላይ ወስደህ ጦርነቱ ይህንን ይመስላል ልትለው ያስፈልጋል ቁም ነገር ተይዞ ነው መቀስቀስ ያለነት ቁምነገሩ ሳይያዝ የሚደረግ ቅስቀሳ ወደ ቁምነገሩ እንዳትገባ ማደንዘዣ ነው ልክ እንደ ኢትዮጵያ ትቅደም የአድዋ ድል መቼ ነው ታስቦበት የተከበረው 100 ዓመቱ ላይ አይደለም ከዛን በኌላ ሚሊኒየም ላይ ነው እሱ ደግሞ ሁሉ ስለሚከበር የተከበረ ነው >> እንዴት እንዴት ነው እኘየህ ሰውዬ ቤተመንግስቱ ኢትዮጵያ ውስጥ አይደለም ወይስ እነሱ ከኢትዮጵያ ውጪ ናቸው እስኪ ምን ነበር ያሉት አቦይ<< የአደዋ ድል መቼ ነው የተከበረው መቶኛ አመቱ ላይ አይደለ ከዚህ በኌላ ደግሞ ሚሊኒየሙ ላይ ነው የተከበረው …>> በእርግጥም እነዚህ ሰውዬ ኢትዮጵያውስጥ አይደሉም ይህንን ባሉ ወቅት የአድዋ ድል ለ115 ዓመት በመላው ኢትዮጵያ መከበሩ ተዘግበል እነሆ አሁን ደግሞ ለ121 ዓመት እናንተ ገድሉንና ታሪኩን ብታሳንሱትም ኢትዮጵያዊያን በታላቅ ድምቀትና ወኔ ያከብሩታል አበቃ በየአመቱ የሚከበር በዓል ነው ሌላም ትንተና አሎትና እስኪ ይቀጥሉ
<< አሁን የአድዋ ጦርነት ብሔራዊ በዓል ሆኖ እንዲከበር መግባባት ላይ ተደርሰል የፌድሬሽን ምክር ቤት እያየው ያለው ነገር አለ በአሉ የት ነው የሚከበረው በየ አመቱ እንዴት ነው የሚከበረው በየ አምስት አመቱና በየ አስር አመቱ እንዴት እንደሚከበር በህግ ላይ ይሰፍራል ተብሎ ይጠበቃል የበአሉ ባለቤት ማን ይሆናል እንደዚሁ አንድ አጀንዳ ነው>> ይሄንን ልብ የሚያቆስል ሊያውም ስለአድዋ ታሪክ የሚሰጡትን ትንና አቦይ ይቀጥላሉ እኛ ግን እዚህ ጋር ገታ እናድራጋቸው አቦይ ይህንን ቃለ መጠይቅ ሲሰጡ አሁን ስድስተኛ ዓመቱን ደፍነል ነገር ግን በየ አምስት አመቱ እንዴት እንደሚከበር መግባባት ላይ ተደርሰል ይላሉ አውቆ ታሪክን ለማጥፋት የተቀመጠ ሰው እንዴት ብሎ ታሪኩን ማሰብ ይቻላል በየትኛውም በኩል የፈጠራ ድርሰት ቢፅፉም የአድዋን ድል ከመላው ኢትዮጵያ ድል ሊያርቁት አይችሉም የአድዋን ድል በአንድ አከባቢ ስለተደረገ ብቻ ለአንድ ብሔር ጠቅልሎ መስጠት የለየለት ቅጥፈትም ጭምር ነው
ቆይ ቆይ በዋናነት የት እንደሚከበር መግባባት ላይ ተደርሰል ሲሉ ምን ማለታቸው ነው የት እንዲከበር ነው የሚፈለሁት ታንዛኒያ፣ ኡጋንዳ፣ ናይጄርያ ነው ወይስ ምን ማለታቸው ነው ይሄ እኮ መግባባት የሚያስፈልገው ጉዳይ አይደለም የአድዋ ድል መከበር ያለበት በመላው ኢቶዮጵያ በድምቀትና ከፍ ባለ ሀገራዊ ሰሜት ነው አበቃ። ቢሹ በየክልሉ ያሉት ህዝቦች ሰላዊ ሰልፍ አደዋን ደግፈው በመውጣት ቢሹ የበፓናል ውይይት አዘጋጅተው ታሪኩን ለትውልድ ሊያስተላልፉት ይችላሉ ምክንያቱም አቁ የአድዋ ድል የመላው ኢትዮጵያውያን ድል ስለሆነ ከጥግ እስከ ጥግ ለአንዲት ኢትዮጵያዊነት በሀገር ፍቅር ስሜት ተነቃንቀው በባዶ እግራቸው ዳገት ቁልቁለቱን ጠጠርና እሹኩን ርሀብና ጥሙን ተቜቁመው … በደምና በአጥንታቸው ያገኙት ድል ነው ክብር ለነሱ
ይህ ሆኖ ሳለ ሀቁ እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ አቶ መለስና አቦይ ሰበሃት እንዲሁም የክህደት ልጆቻቸው አድዋን ከትውልዱ ልብ ውስጥ አውልቀው የምኒሊክን ጀግንነትና አይበገሬ ባይነት በመረዝ በመመረዝ ምኒሊክን ክፉና ጨካኝ አድረገው ያስቀምጠ ቸዋል ባናቱም ኢቶጵያን በቀኝ የገዙ የኦሮሞ ቅይ ገዤ የኤርትራ ቅይ ገዤ የወላይታ የከንባታ የሀድያ የጉረጘየ ቅይ ገዠየ ወዘተርፈ በማድረግ ከጣራ በላይ እንድንስቅም ያሰርጉናል።
ቀድሜ እንደገለጽኩት ኢቶጵያ ከ 100 ዓመት በታች ስልጣኔ ያላት ገና ያላደገች ትንሽ ሀገር አድርገው ስለውልናል ይህ ድርጊታቸው በመላው ኢትዮጵያ ላይ ብቻ አልነበረም ያነጣጠረው የአክሱማይት መንግስትም ጥቂት የትግራይ ቀበሌዎችን ብቻ እንደሚያካልል አቦይ ስብሃት ቅጥፈታቸውን በልበ ሙሉነት ይነግሩናል አሁን ያለችዋ ትግራይ በሙል የቀዳማውያን ትግራይ የአክሱማውያን አስተዳደር እንዳልነበረች ሳያፍሩ ይሰብኩናል እስኪ ገለጣቸውን እዚህ ጋር ላንሳው ደ/ር አረጋዊ በርሄ እና አቦይ ሰበሃት ነጋ በአሜሪካ ድምጽ በትግረኛ ፐሮገራም ላይ በጥር 27/2004 ዓም ላይ ያደረጉትን አስገራሚ ክርክር ጋዜጠኛ ተመስገን በ.ጣፈው መፅሃፍ ላይ አካቶት አግኝቸዋለው ዋናው የውይይታቸው መነሻ ፍኖተ ገድል ሲሆነው በነገራችን ላይ ይህ መጽሐፍ ትውልድን ከትውልድ ጋር የሚያናክስ በውስጡ የለየለት ቅጥፈት የያዘ መጥሐፍ ነው ለመጸሀፍ ደራሲው እግዚአብሔር ከዘረኝነት ብሸታ ይማርህ ሳልለው ማለፍ አልፈልግም መጽሀፉ ውስጥ ያለው ታሪክ የአክሱም ሪክን የአክሱም ታሪክ ብቻ አድርጎ ነው የሚያቀርበው አረጋዊ በርሄ ይህንን ተቃውሞ የአክሱም ሀውልት ከቀይ በህር አንስቶ መላው ኢትዮይያን እንደሚያካልል አስረዳ አቦይ ስበሃት በበኩላቸው የአረጋዊ በርሄን ንግግር ተቃውመው አክሱምን (ትግራይን) እንዲህ አድርገው አሳነሰት
«ይህ ፅሁፍ እንደመነሻ ሲወሰድ አንተም እንዳነሳው አክሱም ከትግራይና ከኤርትራ ውጪ ጋንቤላና ሌላውን የሚያጠቃልል አይደለም ወደትግራይም ስንመጣ አሁን ያለውን ትግራይን ሙሉ የሚጨምር አይደለም ተንቤኝ የአክሱም አዊት ኢፓየር አካል ነበር ወይ? የሚል ጥያቄ አለኝ አጋሜስ ነበረ ወይ? በአንድ አጋጣሜ ፐርፕለስ ፈ ኤርትራ ጠሚል መፅሀፍ ላይ የአጋሜ ሰያሞ የሚል አገኘው ሰያሞ ደግሞ አጋሜ ብለውታል እናም አጋሜ የአክሱም አካል እንዳልነበር ተገነዘብኩ »
እንዴት ያለ ቅጥፈት ነው አለቃቸው መለስ የአክሱም ሀውልትን በንግግራቸው ከመላው ኢቶጵያ አርቀው አስከፉንም አስቆጡንም እኜህ ሰውዬ ደግሞ ጭራሽ የአክሱም ስልጣኔ መላው ትግራይን አይወክልም ብለው ቁጭ ታዲያ የአክሱም ሀውልት ያማን ነው? ምንም ጥርጣሬና ውዝግብ አያስፈልገውም የአክሱም አውልት የመላው ኢትዮጵያዎ ቅርስ ስልጣኔ ነው ።። ዘረኝነት ከክልልም ወርዶ መንደር ውስጥ የሚገባው ይሄኔ ነው አቦይ ስብሀት ግን አንድ ነገር አልተሳሳቱም አክሱማይት ኤርትራንም እንደሚያጠቃልል እኛ ደግሞ እንዲህ እንላለን በክፋትና በዘራችሁት መርዝ እንጂ የአክሱም ስልጣኔ የጎንደር የነገሥታት ግንብ፤ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስትያናት፤የሶፈ ኡመር ዋሻም የገዳ ስልጣኔም የመላው ኢትዮጵያ አንድ አካል ናቸው ብለን ጽሁፌን ሳበቃ ኢትዮጵያ ዳግም ታላቅ እንደምትሆን ስናገር ያለምንም ጥርጥር ነው በፀሀዬ ዮሀንስ ዘፈን እንደዚህ ብዬ ልሰናበታችሁ
ሩቅ አይደለም ቅርብ ነው
ደግሞ አይቀርም መድረሱ
ቃልኪደኗን ያከብራል ቃልገብተላታል እሱ
ያገናና ያስሟ ዳግም መመለሱ
ኢትዮጵያን እግዚአብሔር ይባርክ
ሚሊዮን አየለች
Filed in: Amharic