>

ዘመቻ "በጋዜጠኛ" (በዘጋቢ) ሄኖክ ሰማእግዜር ላይ!!! (ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው) 

የዛሬ አራት ዓመት አካባቢ ግ7 እንደዛሬው ሳይበለሻሽና ሳይመረዝ ከአርበኞች ግንባር ጋር አንድ በነበረበት ጊዜ “በአርበኞች ግንቦት 7 ሕዝባዊ ትግል ላይ ከየአቅጣጫው እየተሰነዘሩ ያሉ ፈተናዎችና ማርከሻ መድኃኒታቸው!” በሚል ርዕስ በጻፍኩት ረዘም ያለ ጽሑፍ ላይ ስለ የአሜሪካ ድምፅ የአማርኛው ክፍል ጋዜጠኛ (ዘጋቢ) ሄኖክ ሰማእግዜር የሚከተለውን ብየ ነበረ፦
“”””…………አሳቢ የመሰሉ አካላት የሚሰጡትን ምክር ሐሳብና ተቃውሞ አሳቢ ሆነው ሳይሆን ወያኔ ገዝቷቸው ቅጥረኞች ስለሆኑ እንደሆነ በምን ልናውቅ እንችላለን? ይሄን ለመለየት በተለይ በአሁኑ ጊዜ ብዙም የሚያስቸግር አይመስለኝም፡፡ ለማንኛውም እነኝህ ነጥቦች ይጠቅማሉ ብየ አስባለሁ፡-

1. የሚናገሩትና የሚጽፉት ነገር ከረጅም ጊዜና ከአጭር ጊዜ አኳያ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ሀገርንና ሕዝብን ሳይሆን ወያኔን የሚጠቅም ከሆነ፡፡

2. የሚናገሩትና የሚጽፉት ነገር ትግሉን ወደኋላ ለመሳብ ለማሰናከል የሚያሴር ከሆነ፡፡

3. አሳቢ መስለው እኩይ ሥራቸው የሚከውኑት ወሳኝና አንገብጋቢ ወቅትን (timing) እያዩ ከሆነ ማለትም ወያኔ ሥጋት በተጋረጠበት ሰዓትና አጋጣሚዎች ላይ ከሆነ፡፡ ለምሳሌ ባለፈው አርበኞችና ግንቦት ሰባት ውሕደት በፈጸሙ ወቅት፣ ሰሞኑን ማጥቃት በመጀመሩ ትግሉን ሊያጠናክሩ የሚችሉ ወሳኝ ወሳኝ ምእራፎች በሚመዘገብበት ወቅቶች ላይ ማለት ነው እነኝህ ቅጥረኞችም ይሄንን እመርታ ሊቀለብስ የሚችል ሥራን በመሥራት እራሳቸውን ጠምደው ታይተዋል፡፡

4. እነዚህ አሳቢ መስለው የቀርቡ ግለሰቦች ሕዝባችን ነጻ እንዲወጣ የሚያቀርቡት ተጨባጭና ጠቃሚ አማራጭ የሌለ መሆኑና “ዝም ብለን አርፈን በወያኔ መገዛት ነው የሚሻለን” የሚል ዓይነት ከሆነ፡፡ እነዚህ እነዚህ ነጥቦች ቅጥረኞችን ለመለየት ይጠቅማሉ የሚል እምነት አለኝ፡፡

እነዚህ ኅሊናቸውን ብቻ ሳይሆን ሁለንተናቸውን ለሆዳቸው የሸጡ ምንደኛ ግለሰቦች ለወያኔ ያደሩ ሳይመስሉ መርዘኛ ሐሳቦቻቸውን ሳይፈሩና ሳያፍሩ በነጻነት ለመናገር ለመጻፍ የሚጠቀሙበት አንድ ሽፋን አለ “ሐሳብን በነጻነት የመግለጽን መብት ከመጠቀምና ተግባራዊ ከማድረግ አኳያ” በሚል ሽፋን ነው፡፡ እንዳሉትም በትክክል ሐሳብን በነጻነት ከመግለጽና ይሄንን ዲሞክራሲያዊ መብት ለመጠበቅና ለማስጠበቅ ከሚል አንጻር ያደረጉት ከሆነ ሚዛናዊነትን ሲጠብቁ ከሁለቱም አቅጣጫዎች ጠንካራ ጠንካራ ሐሳቦችን ሲያስተናግዱ ታገኟቸዋላቹህ፡፡ ነገር ግን ከሁለቱም አቅጣጫዎች ያሉ ጠንካራ ጠንካራ የመከራከሪያ ሐሳቦችንና ተሟጋቾችን የማያስተናግዱና ሚዛናዊነትንም የማይጠብቁ ወያኔን ተጠቃሚ ወደሚያደርግ ወገን የማድላት ዝንባሌ የሚታይባቸው ከሆነ ይሄንን “ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን ተግባራዊ ከማድረግ” የሚለውን መብት ሥውር ተልእኮዋቸውን ለማሳካት ለሽፋን እየተጠቀሙበት ነውና ቅጥረኞች መሆናቸውን ልታረጋግጡ ትችላላቹህ፡፡

ለምሳሌ የቪኦኤው “ጋዜጠኛ” ሔኖክ ሰማእግዜር አቶ ኃይለማርያም ከተማሩበት ዩኒቨርስቲ ሊያገኙት ስለነበረውና በተቃውሞ ምክንያት እንዳያገኙ የተደረገውን ሽልማትና እውቅና ዘገባ በሠራበት ጊዜ ዘገባውን የሠራበት መንገድ ግልጽ በመሆኑ ማንነቱን ለመለየት አስቸጋሪ አልነበረም፡፡ ምክንያቱም ሆን ብሎ የጋዜጠኝነትን መርሖዎች ግልጽነትንና ሚዛናዊነትን ባለመጠበቅ ወያኔን ለመጥቀም በማሰብ ትክክለኛ መረጃወች እንዳይካተቱ በማድረግ ዕውነትን ያዛባ ዘገባ ሠርቷል፡፡

ይህ ሰው ይሄንን ዐይን ያወጣ ስሕተት ረዳት አብራሪ ኃይለመድኅን አበራ ቦይንግ 767 የመንገደኞች አውሮፕላንን (በረርትን) በመጥለፍ አውሮፓ ጥገኝነት የጠየቀበትን ዘገባም በተከታታይ በሠራበት ወቅት ወያኔ “አብራሪው ለረጅም ጊዜ የአእምሮ ጭንቀት ላይ ነበረ ይሄንን ያደረገው ሕመሙ ተባብሶበት ከዚህ ችግሩ የተነሣ ነው” ብሎ የደረሰበትን የፖለቲካ ኪሳራ ለመሸፋፈን ጥረት በማድረግ የሰጠውን ሐሰተኛ ስም አጥፊ መግለጫ እውነት ወይም ትክክለኛ ለማስመሰል በማሰብ አሁንም ሚዛናዊነትን ያልጠበቀና የወያኔን ጥቅም ለማስጠበቅ የጣሩ ዝግጅቶችን አቅርቦ ነበር፡፡ እናም ማንም ጋዜጠኞችም ሆኑ የብዙኃን መገናኛዎች ግልጽ የሆኑ የሞያዊ አሠራር ግድፈቶችን ሲፈጽሙ ስታዩ ያ ሰው ወያም ያ አካል ለሚከላከልለት ሀቁን ለደበቀለት (ለወያኔ) ያደረ የተገዛ የሱን ጥቅም ለማስጠበቅ የሚጥር እንደሆነ ልታረጋግጡ ትችላላቹህ፡፡ እንዲህ መሆኑ በግልጽ የታወቀ ሰው በዚያ የጥፋት ዲርጊቱ ቢገለልና ቢወገዝ ተወገዝኩ ተገለልኩ ጥቃት ደረሰብኝ ብሎ ሊከስ ሊያማርር ሊወቅስ አይችልም መብትም የለውም፡፡

ምክንያቱም ጉዳይ ከሞያዊ ግድፈት አልፎ ሞያውን በማርከስ ኃላፊነትና ግዴታውንም ለግል ዓላማውና ጉዳዩ በመተላለፍ ሞያው የጣለበትን ኃላፊነት አላግባብ ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ በመጠቀም ማለትም ወያኔ ወይም የወያኔ አባል በመሆኑ ሆን ብሎ የወያኔን ጥቅም ለማስጠበቅ በመሞከር ጉዳዩን ወደ የመደብ ትግል ፍትጊያ አሻግሮታልና ወይም እንዲለወጥ ያደረገ በመሆኑና የኢትዮጵያ ሕዝብ ደግሞ በወያኔ ላይ ተስፋ ቆርጦ ትጥቅ ያነሣበት ሁኔታ ላይ ያለ በመሆኑ ይህ ሰው ከመወገዝም አልፎ ቦታና ሁኔታዎች ቢፈቅዱና እርምጃ ቢወሰድበትም እንኳ ድርጊቱ ሕገ ወጥ ሊሆን የሚችልበት ሁኔታ የለም፡፡ ምክንያቱም በጋዜጠኝነቱ ያለውን ከለላ በሠራው ወንጀል አጥቶታልና፤ እራሱን ከጋዜጠኝነት አውጥቶ እንደ አንድ የወያኔ ታጋይ ሁሉ የወያኔ ጥቅም አስከባሪ አድርጓልና፡፡

ይህ እርምጃ ቢወሰድበት “ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ይከበር! እያሉ እነሱ ራሳቸው ይሄንን የሚያደርግን ሰው ያጠቃሉ” ተብሎ ሊገለጽ በፍጹም በፍጹም አይደባም፡፡ ይሄ ብየና አለመብሰልና አለማገናዘብም ነው፡፡ ምክንያቱም የሰውየው ሥራ ሆን ብሎ ከሞያዊ ሥነምግባሩ ውጭ በፈጸመው ስሕተት ምክንያት ሐሳብን በነጻ ከመግለጽ ጋራ ምንም የሚያገናኘው ነገር የሌለ በመሆኑና ይህ የፈጸመው ስሕተትም እራሱን እንደ አንድ የወያኔ ወታደር አድርጎ ስላቆመ ያለውን የጋዜጠኝነትም ሆነ የሌላ መብት ከለላውን ስለሚያሳጣው፡፡ ይህ ሰው ሚዛናዊነትንና ከሁለቱም ወገኖች ጠንካራ የሆኑትን ሐሳቦች ለማስተናገድ የፈቀደ ባለመሆኑ ይልቁንም ትክክለኛ መረጃዎችን ሆን ብሎ የሰወረ በመሆኑ ሐሳብን በነጻ የመግልጽ መብትንለቅጥፈቱ ሽፋን ሊያደርግ ስለማይችል፡፡

ይሄ “ጋዜጠኛ” ሆነ ሌላ ማንነቱ የታወቀ ሰው ኢትዮጵያዊያን በሚያደርጉት ማንኛውም ኩነት ተገኝቶ ልዘግብ ቢልና ሕዝብ የሚያውቀው በወያኔነቱ በመሆኑ ከወያኔ ጋርም ልዩነታችንን በውይይትና በሌሎች ዲሞክራሲያዊ (መስፍነ ሕዝባዊ) መንገዶች ልንፈታ የምንችልበት መንደግ ዕድል ተጠርቆሞ የተዘጋ በመሆኑና በቀረልን ብቸኛ አማራጭ በኃይል እርምጃ ለመፍታት መብታችንን ለማስከበር የተገደድንበት ሁኔታ ውስጥ ያለን በመሆኑ እንዲህ ዓይነቱን ሰው ሕዝቡ በራሱ ዝግጅቶች እንዳይገኝ የመከልከል የማስወገድ መብት አለው፡፡ “እነዚህ የሚከለከሉ (ከዚህ ዞር በሉልን አንያቹህ!) የተባሉ ጋዜጠኛም ሆኑ ሌሎች ግለሰቦች የወያኔ ደጋፊ ወይም ወያኔ እንኳን ቢሆኑ በመነጋገር ነው እንጅ ልዩነቱ መፈታት ያለበት ለምን በኃይል ይሆናል?” ከተባለ በመነጋገር ልዩነትን ለመፍታት 24 ዓመታት ለምነን ተማጽነን አይሆንም አይቻልም ተብለን መብታችንን ተነጥቀን ተነጋግሮ ልዩነትን የመፍቻው ዘመን አልፎ ሳንወድ በግድ ተገፍተን ወደ ሌላኛው የተተወልን ብቸኛ አማራጭ ማለትም በትጥቅ ትግል የኢትዮጵያን ሕዝብ ነጻነትና መብት የማስከበር አማራጭ የገባንበት ወቅት ውስጥ በመሆናችን እንደዚህ ዓይነት ሰዎችን ካጠገባችን እንዳይደርሱ መከልከል ማራቅ እንችላለን መብታችንም ነው፡፡ ሌላ እርምጃ በእነሱ ላይ ለመውሰድ ያሉበት ሀገር ሕግና ሁኔታዎች አይፈቅዱም እንጅ እንደጠላትነታቸው ሁሉ ሁሉንም ዓይነት እርምጃ በእነሱ ላይ ለመውሰድ የያዝነውና የገባንበት ሕዝባዊ ትግል ያስገድደናል፡፡

ሌሎችም ድረ ገጾችና የብዙኃን መገናኛዎችም ቢሆኑ የመጻፍ፣ የመናገር፣ ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ሲባል የሕዝብን የጋራ ጥቅም የሀገር ደኅንነትንና ህልውናን ለመጠበቅ ለመንከባከብ የተለየ ሐሳብ ካለ እሱን ለማስተናገድ የተሰጠ መብት እንጅ ሀገርንና ወገንን የሚጎዳ ወይም ሀገርንና ወገንን የሚጎዳን አካል ጥቅም ለመጠበቅ የሚነገር የሚጻፍ ሐሳብን ለማስተናገድ የተሰጠ መብት አይደለም፡፡ በግልጽ አማርኛ ወያኔ የዚህች ሀገርና የሕዝቧ ቀንደኛ ጠላት እንደመሆኑ ማንም ሰው የወያኔ ቅጥረኛ ሆኖ የወያኔን ጥቅም ለማስጠበቅ ማለትም ከድሮ ጀምሮ የራሱን ቡድናዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ሲል የሀገርን ሕልውናንና የሕዝብን ደኅንነትና ጥቅሞች ለመጉዳት ለማጥቃት ለአደጋ ለመዳረግ የሚያሴረውን የወያኔን ጥቅሞች ለማስጠበቅ የተሰጠ መብት አይደለምና በዚህ ሽፋን ይሄንን ሊያደርጉ እንደማይችሉ ጠንቅቀው ሊያውቁት ይገባል፡፡ የትም ሀገር ቢሆን ያለው አሠራር ይህ ነው፡፡ አሜሪካም ብትሆን ዜጋዋ የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም የሚጎዳ ሥራ ሠርቶ “ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ነው” ቢል አትሰማውም “ብሔራዊ ጥቅሜን ለአደጋ ዳርጓል የሀገርንና የሕዝብት ደኅንነት ለአደጋ አጋልጧል ወይም ለጠላት ተቀጥሮ በመሥራት” ወንጂላ እንደ ስኖውደን ታሳድደዋለች እንጅ ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ነው ብላ አትምረውም፡፡ እነኝህ አካላት ሞያዊ ሥነምግባራቸውን በመጣስ የሀገራችንን ጠላት የወያኔን ጥቅም ለማስጠበቅ ከወያኔ ጋር በማበር የወያኔ ቅጥረኛ በመሆን መረጃን በማዛባት እንደሚንቀሳቀሱ ባወቅን ጊዜ ይሄንን መብት አጥተዋልና ይሄንን መብት ለሽፋን መጠቀም አይችሉም፡፡ አሜሪካ ጥቅሟን የሚጎዳባትን ሰውና ዘገባ የሀገርና የሕዝብ ጠላት አድርጋ እንደፈረጀችና እንደምታሳድድ ሁሉ እኛ ኢትዮጵያዊያንም የሀገራችንንና የሕዝባችንን ብሔራዊ ጥቅሞች የሕልውናችንና የደኅንነታችን ጠላት የሆነው ወያኔን ያገለገለ ወይም የደገፈ ጋዜጠኛንም ሆነ ማንኛውንም ሌላ አካል ሁሉ የሀገራችንና የሕዝባችን ጠላት እንፈርጃለን እናሳድዳለንም፡፡

በግልጽ አማርኛ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉም ዕድሎች ተዘግተውበት መብቶቹን ለማስከበር ተገዶ የትጥቅ ትግል ውስጥ የገባበት ሁኔታ ውስጥ ያለ በመሆኑ ማንኛውም ሰው ወዶና ፈቅዶ የወያኔ አባልና ደጋፊ የሆነ ካለ ይህ ሰው ሊሸሸግበትና ሊታደገው የሚችል ምንም ዓይነት ዋስትና እንደሌለው ጠንቅቆ ሊያውቅ ይገባል፡፡…………..!”””” የሚል ነበረ ጽሑፉ፡፡

በወቅቱ በዚህ ጋዜጠኛ ተብየ ምክንያት ቪኦኤ ከየአቅጣጫው በደረሰበት ተቃውሞ ልጁን ከነበረበት ደረጃ አውርዶ በአንዳንድ አገለግሎት ብቻ እንዲወሰን አድርጎት እስከ አሁን አቆይቶት ነበረ፡፡ ልጁ በዚህ ቅጣት ሊታረም ባለመቻሉ አድፍጦ ቆይቶ እንደገና የቅጥረኝነት ተልእኮውን ቀጥሎበታል፡፡ በመሆኑም የአሜሪካ ድምፅ የአማርኛው አገለግሎት የወያኔ መጠቀሚያ መገልገያ መሣሪያ ካልሆነ፣ ሚዛናዊነትን ለጠበቀና ለሌሎች የጋዜጠኝነት ሞያዊ መርሖዎች ታማኝ ሆኖ አገለግሎቱን ለኢትዮጵያ ሕዝብ እያቀረበ ለመሆኑ እንድናምነው ከፈለገ ይሄንን የወያኔ ቅጥረኛና የጋዜጠኝነት መርሖን አውቆ ተረድቶ አክብሮ ሥራውን የመሥራት ብቃት ችሎታና ፍላጎት የሌለውን ስመ ጋዜጠኛ ሄኖክ ሰማእግዜርን በማሰናበት እንደ አዳነች ፍስሐዬ ያሉ ሌሎቹ ጋዜጠኞቹንም በመከታተልና በመቆጣጠር እንዲያረጋግጥልን አጥብቀን እንጠይቃለን!!! የአሜሪካ ድምፅ የአማርኛው አገልግሎት ክፍል ይሄንን ተገቢ እርምጃ እንዲወስድ ሁላችንም በየአቅጣጫው ጫናና ግፊት ማድረግ ይጠበቅብናልና ይሄንኑ እናድርግ!!!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
amsalugkidan@gmail.com

Filed in: Amharic