>

የለማና ዶክተር አብይ ቡድን እስከዛሬ የመጣበት መንገድ ቀላል የሚባል አይደለም!!! (ሰይፈአርዕድ አምደፅዮን)

 

የህዝብን የልብ ትርታ እያዳመጡ አባዛኛውን የኢትዮጵያ ህዝብ ከባባድ የሊቀሰይጣን ወያኔን የተንኮል ወጥመድ በእርጋታና በጥበብ እየበጣጠሱ የመጡ ቢሆንም ዛሬ ከፊትለፊታቸው በጥቂት ሰአታት ውስጥ የሚከፈተው መጋረጃ ወይትንሳኤያቸውን ወይ በመሳሪያ አፈሙዝ የሚደፈቁበትን እና ትግሉን እንደፍጥርጥሩ ብለው ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚያስረክቡበትን ሁኔታ የሚያሳይ ይሆናል!!!

የወሰዱት ህዝባዊ ሀገራዊ አመለካከት በእነሱና በሊቀሰይጣኑ ወያኔ እንዲሁም የዚህ አውሬ ቡድን ጋሻጃግሬ የህይወት ዘመን አሽከሮች መካከል የሚደረግ እጅግ አታካች የአንገትላንገት ትንቅንቅ ነው!!!

ልዩነቱ ሊቀሰይጣን ወያኔ በህዝብ እየተወገዘ እየተተፋ የመሳሪያ አፈሙዝ ተደግፎ ትግራይ ትግራይ እያለ እነለማ የኢትዮጵያን ህዝብ ልብ ስቅዝ አድርገው ይዘው በህዝብ እየተወደዱ እየተከበሩ ግን በባዶ እጃቸው ኢትዮጵያ: ሀገር: ህዝብ: እያሉ ሀቅንና እውነትን ይዘው እየተደረገ ያለ ግብግብ ነው!!!

አሁንም በቀረችው እያንዳንዷ ሽርፍራፊ ሰአትና ደቂቃ የውስጥለውስጥ ሽኩቻው በዛቻና ማስፈራራት ታጅሎ እስከመጨረሻው የተጧጧፈበት ሁኔታ ነው ያለው!!!

ውጤቱም ስልታዊና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የሚያስቀይር ያለፈርቅ እና ቀብድ ስልጣን መረከብ የሚያስችል የጠቅላይ ሚንስትሩን ስልጣን ለሽግግር ወቅት ብቻ ለመጠቀምና ሁሉም ኢትዮጵያዊ እኩል የሚሳተፍበት ሁሉም ባለድርሻ አካላት አዎንታዊ ሚና የሚጫወቱበት ኢትዮጵያን በክብር አንድ የሚያደርግ 84 የዘር ሳጥን ሰባብሮ የሚጥል ኢትዮጵያውያን በዘር በነገድ ሳይሆን በዜግነታቸው የሚለኩበት ሁኔታን ሁሉ ለማመቻቸት ያሚያስችል ቋሚ አዲስ ጠንካራ ሁሉአቀፍ መንግስት ለመመስረት መቁረጥን መወሰንን የሚጠይቅ ሁኔታ መኖሩን መገንዘብና ለዚህ በፅናት መቆምን የሚጠየቅ ነው!!!

አዲሱ ኦህዴድ ቀብድ ሳይከፍል ሊቀሰይጣን ወያኔም በስውር ፈርቅ ሳይበላ ከተንቀሳቀሰ የእነ ለማና ዶክተር አብይ አዲሱ ኦህዴድ የኢትዮጵያ ህዝብ ይሁንታ እንዳለውና የሽግግሩን ሁኔታ ለማመቻቸት ኃላፊነቱን ከወሰደ ችግር እንደማያጋጥመው በማሳብ ትኩረቱን በሊቀሰይጣን ወያኔ ላይ በማሳረፍ በጥበብ በብስለት በመደራደር የሊቀሰይጣን ወያኔን ሴራ በብልሃት በማክሸፍ እራሱንም ሁሉንም የኢትዮጵያ ህዝብ ከሰይጣናዊ አገዛዝ ነፃ እንዲያወጣ በአክብሮት እየጋበዝነው በውስጡ ከ20-30 አመት ድረስ አገልግሎት ያላቸውን የሊቀሰይጣን ወያኔ የህይወት ዘመን አሽከሮችን የማፅዳት ዘመቻን እና እራሱን የማጥራት ቆራጥ እንቅስቃሴ ታሳቢ አድርጎ ውስጥ ለውስጥ ደረጃ በደረጃ መከተል ይኖርበታል!!!

አባዱላ ገመዳን(ምናሴ ወልደጊዮርጊስ) ወርቅነህ ገበየሁ ወልደኪዳን, ኩማ ደመቅሳ(ታዬ ተክለኃይማኖት), ሙክታር ከድር, ድሪባ ኩማ, ጌታቸው ዳባ, እሸቱ ደሴ, የአንድ ወቅት የድሬዳዋ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አብደለዚዝ ኩማ የአዲስአበባ ከንቲባ እያለ የእሱ የፅ/ቤት ኃላፊ መሆን የቻለው ጎፍጫላውን ዳባ ደበሌ(ባሬስታው) እና የመሳሰሉትን የህይወት ዘመን አሽከሮች ወይም አስጠቂዎችን እንኮኮ ብሎ ከሄደ እንኳን ለኢትዮጵያ ህዝብ እና ለኢትዮጵያ ለእራሱም መሆን አይችልም!!!መጨረሻውም የእሳት እራት ነው የሚሆነው!!!

እነኝህን አስጠቂዎች ከውስጡ አፅድቶ የኢትዮጵያን ህዝብ እና ኢትዮጵያን አክብሮ በፍቅር በጥንቃቄ መሄድ ከቻለ በእርግጠኝነት ሊቀሰይጣን ወያኔ የሚመካበትን የመሳሪያ አፈሙዝ ታቅፎት ይቀራል ከዛም ለኢትዮጵያ ህዝብ ሳይወድ በግድ ተገዶ ያስረክባል!!!

ሌላው ነገር ነገ ቁርጡ ይለያል የትግል ስልታችንን እኛም እንደ አንድ ዜጋ ውጤቱን አይተን ነገ እንወስናለን!!!

Filed in: Amharic