>

ሚኒሊክ ~ ዓድዋና ~ ባንዳ የዓድዋ ጦርነት አሳፋሪ ገጾች (ዘመድኩን በቀለ)

     ~ ” ባንዳ ሆድ እንጂ ብሔርና ሀገር የለውም “ አከተመ ።
~ ሼህ #ጧላ እና #ራስ_ስብሃት የመጀመሪያዎቹ ከወራሪው የጠላት ጦር ጎን ተሰልፈው የሀገራቸውን የኢትዮጵያን ጦር ለመውጋት የተሰለፉ ትግርኛ ተናጋሪ ባንዳዎች ።
~ ሀገሩን የከዳ ባንዳ በትግርኛ ሲምል ሲፎክር ሲሸልልም ” አነ ወዲ ጎይታ ቶለንቲኒ” ይልነበር ። ቱ አሁን የጠቅል አሽከር ብሎ መማል መፎከር ነው የሚቀለው ወይስ ቴላቴሊ ፣ እስፓቶሊ ፣ ባላቶሊ ማለት ነው ። የቱ ነው የሚቀለው? ለእኔ በአሉላ አባነጋ ፣ በዮሐንስና በምኒሊክ እና በቴዎድሮስ ስም መፎከሩ ይሻለኛል ።
#Ethiopia ~ ሚኒሊክ ~ ዓድዋና ~ ባንዳ ።
በተለምዶ የዓድዋ ዘመቻ የሚባለው ከአምባላጌ ጦርነት እስከ ዓድዋ ድረስ ያለው ጣልያንን ለማንበርከክ የተደረገው ውጊያ ነው::አድዋ የዘመተው የኢትዮጵያ ዘማች ጦር -የመጀመርያውን ጦርነት ያካሄደው አምባአላጌ ላይ ነበር:: ሁለተኛው ጦርነት ደግሞ መቀሌ ምሽግ ላይ ሲሆን- ሦስተኛውና የመጨረሻው ደግሞ አሻሾ -ራዕዮ እና ሰማያት የሚባሉ ተራሮች ላይ መሽጎ ከነበረው ከጣልያን ጦር ጋር የተደረገው ዋናው ውጊያ ነው።
የአድዋ ጦርነት አንዱ አካል የሆነው አምባአላጌ ላይ የተሰለፈው የጣልያኑ ጦር ጀነራል ቶዚሊ ሲሆን አምባላጌ ኮረብቶች ላይ እጅግ ጠንካራ ምሽግ ሠርቶ ተዘጋጅቶ ነበር:: የሚገርመው የጀነራል ቶዚሊ ጦር ዋና ቀኝና ግራ እጅ ኢትዮጵያኖች ነበሩ ። በቀኝ በኩል ያለውን የቶዚሊን ጦር የሚጠብቀው #ሼህ_ጧላ ሲሆን 350 ሃምሳ ወታደሮችን ይዞ በዘመናዊ ትጥቅ ተደራጅቶ የገዛ ወገኖቹን ሊወጋ ተዘጋጅቷል። በግራ በኩል ደግሞ የነበሩት #ራስ_ስብሃት ናቸው:: ራስ ስብሃትም 350 ዘማንዊ ጠመንጃ ከኢጣልያ ተቀብለው ባንዳ በመሆን ከጀነራል ቶዚሊ ጋር አብረው መሽገዋል:: ሁለቱም ከራስ መንገሻና ከራስ አሉላ ጋር ተጣልተው ነው ከጣልያን ጋር ያበሩት ። በዓድዋ ውጊያ ላይ የተሳተፉ የመጀመርያ ባንዶች ናቸው ። ሁለቱም የአካባቢው ተወላጅ በመሆናቸው ትግርኛ ተናጋሪዎች ስለነበሩ ለጣልያን ጦር ብርቱ ተስፋ ነበሩ። በአንድ ወገን ቦታውን ያውቃሉ ። በሌላ ወገን ትግርኛ ቋንቋቸው ስለሆነ ሕዝቡ ለጣልያን እንዲገዛ ሰበካ ያካሂዱ ነበር::
ጳውሎስ ኞኞ ኣጤምኒልክ በሚለው መጽሓፉ ላይ ገጽ 167 እንድህ ይገልጸዋል
“በፊታውራሪ ገበየሁ አበጋዝነት  የሚመራው የኢትዮጵያ ሰራዊት አምባላጌ ደረሰ:: ከራስ መንገሻና ከራስ አሉላ ጋር ተጣልተው ለኢጣልያ ገብተው የነበሩት ራስ ስብሃት 350 ዘመናዊ ጠመንጃ ከኢጣልያ ተቀብለው ፋላጋ ኮረብታ ላይ እንዲሆኑ የአምባላጌው ጦር አዛዥ ቶዚሊ አዟቸው መሽገዋል:: .. በስተቀኝ በመቶአለቃ ቮልፒቺሊ የሚመራው ጦር በሱ ጎን ደግሞ ቶጉራ ኮረፕታ ላይ ከኢትዮጵያ ከድቶ ለኢጣልያ የገባው ሼህ ጧላ 350 ዘመናዊ ጦር ይዞ ለጣልያን ጦር ሊዋጋ መሽጓል”
ፕሮፌሰር ሬይመንድ ደግሞ እንድህ ይገልጹታል The battle of Adwa ( 128)
” On the right some 400 men loyal to Sheik Talah occupied a position analogous to that of Ras Sebhat on the left. they covered the road that bypassed Amba Alage to the left…. their role was to prevent a turning movementthat treatened an alternative path of retreat”
የራስ መኮንን ጦር ሲመጣና አምባላጌን ለማስለቀቅ ውጊያ ሲከፍት በግራ በቀኝ የኢትዮያን ጦር የገጠሙት ሁለቱ ትግርኛ ተናጋሪ ባንዶች ራስ ስብሃትና ሼህ ጧላና ሰራዊቶቻቸው ነበሩ::
ግን የኢትዮጵያን ዘማች ጦር መቋቋም አልቻሉም::
ፕሮፌሰር ሬይመንድ ጆናስ ዘ ባትል ኦፍ አድዋ በተባለው መጽሓፍ ገጽ 128 ላይ  አምባላጌ ላይ የነበረው የባንዳው የራስ ስብሃት ጦር እንዴት በራስ መኮንን ጦር እንደተንኮታኮተ እንዲህ ተርከውታል
“mekonnen then directd Ras wele to lead his seven thoussand men to test Sibhat position on Italians left.Despite Sibhat dominant position, the disparity in numbers proved overwhelming; th reseolve of Sibhats men- built on animosity towards Mengesha wavered as thousands of their countrymen advanced. with in two hours Sibhats men were giving way “
በጀነራል ቶዚሊ የሚመራው እና በራስ ስብሃትና በራስ ጦላይ የሚታገዘው የጣልያን ጦር የቻለውን ያህል ቢዋጋም – በራስ መኮንን የሚመራው የኢትዮጵያን ጦር መመከት አልቻለም:: ብትንትኑ ወጣ:: የራስ ስብሃትም ሆነ የሼህ ጧላ ባንዶች ጣልያንን ሊያተርፈው አልቻለም::  ከጥቂት ሰዓታት ውጊያ በኋላ ራሱ ጀነራሉ ተገደለ:: የጣልያን ጦር ተደመሰሰ::
የሚገርመው
ጣልያን ለወገኖቹ ሀገር ለመስረቅ ነው የመጣው:: ቢዋጋ አይደንቅም:: የሚደንቀው የራስ ስብሃትና የሼህ ጧላና የተከታዮቻቸው ነገር ነው:: የነዚህ ባንዶች ትርፍራፊዎች ለረጅም ግዜ እነ ቶዚሊና የሱ አዋጊ ቶለቲሊ ጌታቸው እንደሆነ ያምኑ ነበር:: ሲፎክሩም በቶሊቲኒ ስም ነበር:: ይሄም አይደለም የሚገመርው- እነሱና ተከታዮቻቸው ባሉበት ቦታ ሁሉ የሚያስሉት ስዕል የሚጽፉት መጽሓፍ ቶሊንቲኒ ጌታቸው እንደሆነ የሚገልጽ መሆኑ ነው:: በትግርኛ ” ጎይታ ቶለንቲኒ” ይሉታል:: ጌታችን ቶለንቲኒ ሆይ እንደማለት ነው::
ሻሎም !  ሰላም !
Filed in: Amharic