>

እንዴ! እነኝህ ሰዎች ግን የምር ቂል ናቸው ልበል???

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
የወያኔ ካድሬዎች (ወሽዋሾች) የተሞሉበት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተብየ የዛሬው ጉባኤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ያጸደቀበትን ውሳኔ ብዙዎች ያልጠበቁት እንደነበር ሲናገሩ እያየሁና እየሰማሁ ነው፡፡ በጣም ይገርማል! አሁን በእነኝህ ደካማ ንቃተሕሊና ባላቸው ሰዎች ተመርቶ ነው ሕዝባዊ ትግሉ ወያኔን ለመደምሰስ ወይም ለማስወገድ የሚበቃው???
ወያኔ ጉባኤው የፓርቲውን ፖለቲካዊ ፍላጎትንና ዓላማን መሠረት ባደረገ መልኩ ማዕከላዊነትን በጠበቀ አሠራር በመንጋ በመነዳት የሚሠራ ሳይሆን እያንዳንዱ የሕዝብ ተወካይ ከሕዝብ የተወከለ በመሆኑና በዚህም ምክንያት ተጠሪነቱ ለሕዝብ በመሆኑ የወከለውን ሕዝብ ፍላጎት፣ ዓላማና ጥቅም ለማስጠበቅ ለማስከበር በመቆም የሐሳብ ፍጭትና ግጭት የሚስተናገድበት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጉባኤ እንደሆነ ለማስመሰል የዛሬውን ጉባኤ በዝግ እንዲካሔድ አድርጓል፡፡
የወያኔ ድራማ (ትውንተ ኩነት) በዚህ አላበቃም፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በ346ድምፅ ድጋፍ በ88 ተቃውሞና በ7 ድምፀ ተአቅቦ እንዲያልፍ አድርጓል፡፡ ምክንያቱም በእንዲህ ዓይነት ጉዳይ ላይ በጉባኤው የሐሳብ ልዩነት ካልተንጸባረቀ ወይም የሚቃወም ከሌለ ጉባኤው የሕዝብ ውክልና አሠራርን በሚቃረን መልኩ የፓርቲ ፖለቲካዊ ፍላጎትን መሠረት ባደረገ ማዕከላዊነትን የጠበቀ የደቦ አሠራር የሚሠራበት መሆኑን፣ ነጻነት የሌለበት ከመሆኑም አንጻር ሕይዎት የሌለው ጉባኤ መሆኑን ሊያሳብቅበት ሆነበታ!
ስለዚህ እንዲህ ዓይነት ትዝብት እንያይወሰድበት ውሳኔው 88 ተቃውሞን 7 ድምፀ ተአቅቦን አስተናግዶ ያለፈ ለማስመሰል ሞክረ፡፡ በቃ ያለው ነገር ይሄው ነው! ሌላው የኞቹ ጅሎቹ የሚያስቡት ቅዠት ነው እንጅ ምንም ነገር የለም አልነበረምም፡፡ እንደሌለና እንዳልነበረም ይሄው የሕዝብ ተወካዮች ነን ባዮቹ ምንደኞች የግፈኛውን የወያኔን ዕድሜ ለማራዘም ሲሉ ወከለን የሚሉት ሕዝብ በማንም አረመኔ የወያኔ ጭፍራ ያለ ፍርድ የትም እየተደፋ እንዲያልቅ ውሳኔያቸውን በማስተላለፍ በሚገባ አረጋግጠዋል፡፡
እኔማ በተደጋጋሚ “ኧረ ተው! ኧረ ተው! ወያኔ ሲያጃጅለን ነው እንጅ ኦሕዴድም ሆነ ብአዴን እያደረጉት ያለው ነገር ሁሉ ትወና ነው አትመኑ! እውነት ቢሆን ኖሮ በዚህ በዚህ ምክንያት ይሄን ይሄን ነገር ያደርጉ ነበረ እንጅ ይሄን ይሄን ነገር ሲያደርጉ አይገኙም ነበረ፣ ፓርቲው በተፈጥሮው እንዲህ ዓይነት ልዩነትንና ነጻነትን የሚያስተናግድ አይደለም አትጃጃሉ!” እያልኩ ኡኡ! ብል ብጮህ አልሰማ ብለው ሲጃጃሉ ከርመው መድኃኔዓለም ክርስቶስ የኦሕዴድንና የብአዴንን ሸፍጠኛ የሎሌነት አስመሳይ ተግባር መጋለጫ አጋጣሚ ፈጠረና ትክክለኛ ማንነታቸውን አጋልጦ ኩም አደረገልኝ፡፡ እንዴት ደስ እንዳለኝ!!!
በቃ ከዚህ በኋላ እያንዳንድሽ ሳትወጅ በግድሽ ኦሕዴድ፣ ብአዴን ምንትስ የሚል የወያኔ የዳቦ ስም እየጠራሽ መጃጃል ማላዘንሽን ትተሽ ወያኔ/ኢሕአዴግን በአንድ ፊቱ ቆርጠሽ ትታገያለሽ!!! ወይ ደግሞ ምን ይታወቃል መቸም ሞኝ በስሎ አይበስል አይደል? ተንኮለኛው፣ ሸፍጠኛው፣ ሴረኛው ወያኔ ደሞ ሌላ መጃጃያ ፈጥሮ ይወረውርልሽና እሱን አንሥተሽ መጃጃልሽን ትቀጥይ ይሆናል፡፡ ኧረ ተው! ኧረ ተው! መጃጃሉ ይብቃ!!! ጊዜያችንን፣ ሕይዎታችንን፣ ሁለነገራችንን እየተጃጃልን በከንቱ አናስጨርሰው??? ይልቁንም ተገቢውን ቆራጥ አቋምና አስተሳሰብ ይዘን በመታገል ወያኔን ለመደምሰስ እንጠቀምበት???
በነገራችን ላይ ወያኔ ሒሳብ አይችልም አይደል? ከ547 የሕዝብ ተወካዮች መቀመጫ አሁን በሕይዎት የሌሉትን አባላቱን ቁጥር ቀንሶ “ስንት የድጋፍ ድምፅ የሰጡ፣ ስንት የተቃውሞ ድምፅ የሰጡ፣ ስንት ደግሞ ድምፀ ተአቅቦ ያደረጉ አድርጌ አካፍየ ውሳኔውን ላሳልፍ?” ብሎ ሒሳብ ሲሠራ የተሳሳተ ሒሳብ አስልቶ ኖሮ መጀመሪያ ቀን ቀትር ላይ በብዙኃን መገናኛ ይፋ ባደረገው ዜና ላይ 346 የድጋፍ ድምፅ የሰጡ ተብሎ ነበረ የተነገረው፡፡ በኋላ ላይ ደገፈ፣ ተቃወመ፣ ተዓቅቦ አደረገ የተባለው ድምፅ ሲደመር አሁን በሥራ ላይ ያለውን የተወካዮች ቁጥር እንዳልሞላ ተነገራቸው መሰለኝ ዘግይተው ባወጡት የታረመ ዜና ላይ ደግሞ 395 ድጋፍ የሰጠ ብለው ለማስተካከል ሞክረዋል፡፡ አየ ወራዳው አጭበርባሪው ወያኔiii እንዲህ እንደቀለድሽብን አትቀሪ!!!..
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
Filed in: Amharic