>

የጦር ወንጀለኛዉ ብቻዉን ይቆማል፤ ወርቅ ነኝ የሚለዉ በእሳት ይፈተናል!! (ሃራ አብዲ)

ሃያ ሰባት አመት፤ ያከማቸዉ ሃጢያት፣
ምድሪቱን ከበዳት፤ መሸከም አቃታት።
የኢትዮጵያን ፓርላማ፤ በጦር አስፈራርቶ፣
አዋጅ ካስጸደቀ፤ በጉልበት ደንፍቶ፣
አናጸድቅም ካሉም፤ ለህዝቡ ወግነዉ፣
ፓርላማ አፍርሶ፤ ለቅሞ ካሰራቸዉ፣
ወይ በእንቢተኝነት፣ ጭዳ ካረጋቸዉ፣
ታሪክ ይቀየራል ፤ ከዛሬ ጀምሮ፣
ልክ እንደተባለዉ፤ ይለያል ዘንድሮ፣
ይለያል ዘንድሮ፤ የወያኔ ኑሮ!!1
ሃጎስ ወርቁ ቢባል፤ መብራቱ በረከት፣
ናዝሬትም ቢወለድ፤ ጎንደር ቢሰነብት፣
ቁዋንቁዋዉን ቢናገር፤ ስሙ ቢለዋወጥ፣
ከሚመጣዉ ቁጣ ፤ አይችልም ለመምለጥ።
ስንዴዉን ከእንክርዳድ፣ መንጥረን አጣርተን፣
በሰፈረዉ ቁና፤ እንሰፍርበታለን!!!!!
ገራፊ አስገራፊ፤ ገዳይና አስገዳይ፣
የፊጢኝ ታስረዉ፤ ለፍርድ ይቀርባሉ፤
ከፋሽስት ወያኔ፤ የወገነዉ ሁሉ፣
በዝምታ ሽፋን ፤ የተባበራቸዉ፣
ከአመድ ላይ ተነስቶ፤ ፎቅ በፎቅ የሆነዉ፣
ወያኔን በጉያዉ ፤ ሽሽጎ የያዘዉ፣
ዋጋዉን ያገኛል፤ ልክ እንደሚገባዉ።
በኢትዮጵያ ህዝብ እንባ፤ ንዋይ ያከማቹ፣
ቆጥረዉ ይሰጣሉ፤ ለባለ መብቶቹ፣

አጥፍቼ እጠፋለሁ፤ ብለዉ ከቆረጡ፤
መሰቀያቸዉን ገመድ፣ ይዘዉ ይምጡ።
የትግሬዉን ያህል ድህነት አያዉቅም፣
ደግሞም የደም ገንዘብ፤ ኢትዮጵያዊ አይወድም ፣
ያጋየዋል ደርሶ፤ ለጠላት አይተዉም።
ሃያ ሰባት አመት፤ ያከማቹትን ሀብት፣
ያስቡ ይሆናል ፤ እንዴት እንዲያሸሹት፣
ጥለዉ ይፈርጥጡ፤ እኔ ልምከራቸዉ፣
በህዝባችን ስቃይ ያገኙት ንብረት ነዉ፣
የኛ ተፈናቅለዉ፤ እነሱ ወረሱት፣
የኛ ሰዉ ሲቀጠፍ፤ የነሱ ረባበት፤
የሚሞቱት የኛ ፣ የሚገድሉ እነሱ፣
በምድረ-ኢትዮጵያ፤ ልክ እንደ አሸን ፈሉ፣
ዛሬ ጭንቅ መጣ፤ ወዴት ይገባሉ???
ከጫፍ እጫፍ ድረስ፤ እንደ እምቦጭ ተስፋፍተዉ፣
ምድሪቱን ሲነጩ፤ አፋቸዉን ተክለዉ፣
ደራሽ ዉሃ መጣ፤ ሊያጥለቀልቃቸዉ።
ጨርቃቸዉ ተራግፎ፤ ሙልጫቸዉን ይዉጡ፣
ወትሮስ ከደደቢት፤ ምን ሰንቀዉ መጡ?
ሰላም ባስ ይደርደር፤ ጠርጎ ይዉሰዳቸዉ፣
ቸሩ ኢትዮጵያዊ፤ በሳቅ ይሸኛቸዉ፣
ፊታቸዉን ላያይ፤ ርግሞ ይስደዳቸዉ።
በዚህ ካልተስማሙ፤ አያዋጣም ካሉ፣
በጦር ይሞክሩን፤ ቀሊል ነዉ ነገሩ።
አማራ፣ ኦሮሞ፣ ወላይታ፤ ሶዶ፣
ጉራጌ፤ ሃደሬ፤ ጋምቤላና ጋሞ፣
አፋርና ቅማንት፤ ቤንሻንጉል ተዳምሮ፤
በኢህአዴግ ጥላ፤ ወያኔ ያጋዘዉ፣
በቅኝ ግዛት ይዞ፤ ግፍ ያስፈጸማቸዉ፣

ወንጀል ድርጊታቸዉ ፤ ይቅርታ ያገኛል፣
ወርቅ ነኝ የሚለዉ፣ የጦር ወንጀለኛዉ፤
በእሳት ይፈተናል ፣ ብቻዉን ይቆማል፣
በሰፈረዉ ቁና ፣ ይሰፈርበታል፤
ብዙ ተለምነዉ፤ ከኛ ጋር ያልቆሙት፣
ከእንግዲህ ያበቃል፤ እሽሩሩ ማለት፤
ተያይዞ መጥፋት፤ ሲሉ የነበሩ፣
ስድስት ሚሊዮኖች፤ እስኪ ቀመር ይስሩ፤

Filed in: Amharic