>

አባትና ልጅ በቤታቸዉ ዉስጥ ተገደሉ። የወያኔ ሰራዊት እንደ እብድ ውሻ ኦሮሚያ ዉስጥ እየተቅበዘበዘ ነው (ራዲዮ አፉራ ቢያ)

ለግድያ የተሰማራዉ የወያኔ ሰራዊት በኦሮሚያ መንደሮች ዉስጥ እንደ እብድ ዉሻ እየተቅበዘበዘ መሆኑ ታወቀ።
በዛሬዉ ዕለት ጉደር ዉስጥ ኣባትና ልጅ በመኖሪያ ቤታቸዉ ዉስጥ መገደላቸዉን ከስፍራዉ የተሰራጨዉ መረጃ ያመለክታል። ድጋፌ ዳንዳኣ የተባሉት ኣባት ታረሳ ዲጋፌ ከተሰኘዉ ልጃቸዉ ጋር በመኖሪያ በታቸዉ ዉስጥ በጭካኔያቸዉ ከናዚ ጋር በሚወዳደሩት የውያኔ ሰራዊት መገደላቸዉ ታውቋል።
በሌላ በኩል ደግሞ አብደታ ምትኩ የተባለ የኮሌጅ ተማሪ በተመሳሳይ ሁኔታ ኣምቦ ዉስጥ በነዝህ ኦሮሚያ መንደሮች ዉስጥ እንደ እብድ ዉሻ በሚቅበዘበዙ ነብሰ ገዳዮች ሀይወቱ ማለፉ ታውቋል።
በተመሳሳይ ሁኔታ ገመቺስ የሚባል የ16 ኣመት ህጻን ግምቢ ከተማ ዉስጥ በፋሺስቶቹ ጥይት ተመቶ ሆስፒታል መግባቱን ከስፍራዉ የሚደርሱ ዘገባዎች ያመለክታሉ። በተጨማሪ ሌሎች 3 ሰዎች በኣምቦ መገደላቸዉ የተዘገበ ሲሆን በመንዲ በነጆና በሌሎችም አጎራባች ከተሞች በተመሳሳይ መልኩ በሰላማዊ ዜጎች ላይ ጉዳት መድረሱ ሲዘገብ ዝርዝር ዘገባዎቹ እንደታጣራ ይፋ ይሆናል።
ይህ በንዲህ እንዳለ የኦሮሚያን ፖሊስና የኦሮሞን ቄሮ ለማጋጨት በመሞከር ላይ የሚገኙት የወያኔ ጦር አባላት በአምቦ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ቦምብ በመውርወር ብሁለት የኦሮሚያ ፖሊስ ኣባላት ላይ ጉዳት ማድረሳቸዉ ታዉቋል። ቦምብ ፖሊስ ላይ የወረወሩት ቄሮዎች እንደሆኑ ለማስመሰል ወያኔዎች የፈጸሙት ይህ የጅል ተግባራቸዉ ወዲያው የተነቃባቸዉ ሲሆን በዝ ህ የውያኔ ሰጣናዊ ተግባር የተጎዱት የኦሮሚያ ፖሊስ ኣባላት ህክምና በመከታተል ላይ መሆናቸዉ ታዎቋል።
Filed in: Amharic