>

" የሞያሌው ዕልቂትና የቦረና ሰማእታት " (ዘመድኩን በቀለ እና በድሉ ሌሊሳ)

#ETHIOPIA | ~ ሞያሌ ~ ተረኛዋ  ቢሾፍቱ ፣ ወልድያ ፣ ጨለንቆ ፣ ባህርዳር ፣ ጎንደር ፣ ነቀምቴ ፣ ጨለንቆ ፣ ጋምቤላ ፣ ሲዳማ… … የጅምላ ጭፍጨፋ ።

~ትናንት ~ የካቲት 30 / 2010 ዓም ከሞያሌ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኝ ከተማ ሁለት የመከላከያ ሠራዊት አባላት ማንታቸው ባልተወቁ ሰዎች ተገድለው ተገኙ ተባለ ።

~ዛሬ መጋቢት 1/2010 ዓም ~ ሙሉ ትጥቅ የታጠቀ ሠራዊት ሞያሌ ከተማ ገብቶ ሀገር ሰላም ብሎ የተቀመጠውን ነዋሪ በሙሉ በመንገድ ላይ የሚሔደውንም ፣ ከቤቱ በራፍ የተቀመጠውንም ፣ በሆቴል የሚስተናገደውንም ፣ ከመስጊድ የሚወጣውንም ብቻ ወደሚንቀሳቀስ ሰው ላይ መተኮስ ጀመረ ። ከወታደሮቹ በሚተኮሰው ጥይትም በርካታ ዜጎች በየሥፍራው መውደቅ ጀመሩ። ረገፉ ፣ እንደቅጠል ረገፉ ።

በከተማዋ የሶማሊያው አልሸባብና የአልቃይዳ ሠራዊት የገባ እንጂ የገዛ የመንግሥታችን የኢትዮጵያን መለዮ የለበሰ ሠራዊት እየፈጸመው ያለ ድርጊት አይመስልም ነበር ይላሉ የዐይን እማኞቹ ።

መንግሥት ባመነው 9 ሰዎች የአይን እማኞች እንደሚናገሩት ደግሞ 17 ንጹሐን ዜጎች በቀን በብርሃኑ በጠራራ ፀሐይ ይጠብቀናል ብለው ግብር እየከፈሉ በሚያስተዳድሩት የገዛ ሠራዊታቸው በሆነው የኢትዮጵያ ጦር ተረሸኑ ።

~ ሲመሽ ወደ ማታ መንግሥታችን እንዲህ አለ ።

” ይቅርታ ወታደሮቼ የተሳሳተ ኢንፎርሜሽን ደርሷቸው ነው ይኽን ግድያ የፈፀሙት።ለማንኛውም ህዝቡን የገደሉትን ወታደሮች በቁጥጥር ስር አውያለሁ ። እናም ለተፈጸመው ስህተት በጣም ይቅርታ” ብሎን አረፈው።

በኢትዮጵያ ውስጥ እንደ ” ሞትዜና ” የተለመደ ነገር የለም ። ትገደላለህ ፤ ከዚያ ለአሟሟትህ ቆንጆ የአሸባሪ ስምና ፀረ ምናምን የተባለ ማዕረግም ይወጣልሃል ። ከስንት ዓመት አንዴ ደግሞ እንዲህ መንግሥትህ ይረሽንህና ” ይቅርታ በስህተት ነው ” ይልሃል ። ሰማይ አይታረስ ንጉሥ አይከሰስ ትልና አንተም ጮጋ ዝም ጭጭ ብለህ ሌላ የሞት ዜና ትጠብቃለህ ።

አሁን ቁስለኞች በየደቂቃው እየሞቱ ነው ተብሏል ። በዚህ መሠረት የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ አንደሚችል እየተነገረ ነው ። የሞያሌ ከተማ ኗሪ ግን ቤት ንብረቱን ጥሎ ወደ ጎረቤት ሀገር ኬንያ መሸሹ ተነግሯል ።

~ አባዱላ ገመዳና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ይታወጅ ፣ ጦሩም እንደፈለገው ይግደል ብለው እጃቸውን በማውጣት ዜጎች እንዲገደሉ የሞት ዓዋጁን ያፀደቁት የፓርላማ አባላትስ የዛሬውን አሰቃቂ ድርጊት ሲያዩ ምን ይሰማቸው ይሆን? አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴስ ነገ ደግሞ በቴሌቭዥን ቀርቦ ምን ይለን ይሆን?

~ ቅዱስ ፓትርያርካችን እና ቅዱስ ሲኖዶሳችንስ ይኽን እልቂት እንዴት ይመለከቱት ይሆን? ሟቾቹ ዜግነታቸው ኢትዮጵያዊ ሲሆን መንግሥት የሰጣቸው መታወቂያ ላይ ደግሞ ኦሮሞ ፣ ጌዶ ፣ ስልጤና የዐማራ ነገድ አባላት ናቸው ተብሏል ።

~የሞያሌው ፍጅትና ግጥምጥሞሽ የማይመስሉ ነገሮች

ከጥቂት ወራት በፊት ጨለንቆ ላይ 19 ሰዎች መገደላቸው ይታወሳል። የጨለንቆው ግድያ የተፈፀመው የ 17 ቀኑ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ስብሰባ ሊደረግ አንድ ሲቀረው ነበር። በትላንትናው የሞያሌ ፍጅትም ከ 12 በላይ ዜጎች ተገለዋል። የሞያሌውም ልክ እንደ ጨለንቆው የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ስብሰባ ሊጀመር አንድ ቀን ሲቀረው ነው። ስለዚህ የሞያሌው ፍጅት እና የጨለንቆው እልቂት ተራ ግጥምጥሞሽ አይደለም። በደንብ ተመሳሳይነት አለው ። የተሸረበ ሴራ ውጤት ይመስላል። ሌላ ጥርጣሬ የሚያጭር ነገር እንጨምር፣ ባለፈው ግዜ 4 ግለሰቦች #ሀማሬሳ ላይ ተገለው ነበር፣ግድያው የተካሄደው #የገበያ አድማ ሊጀምር አንድ ቀን ሲቀረው ነበር፣ይሄ ማለት አድማውን ስኬታማ ለማድረግ መከላከያው አመቻችቶ ኳስ ማቀበሉን ነው። ሲለዚህ በሆነ ቡድን እየተቀነባበሩ የሚለቀቁ የቤት ስራዎች ናቸው ማለት ነው ግድያዎቹ።

የሞያሌው ግድያ ለምን እንደተፈጠረ የግል ግምቴን ላስቀምጥ። ሀገሪቱ ችግር ላይ በሆነችበት በዚህ ወክት፣ ያለ ፖለቲካ አመራር በኮማንድ ፖስት እየተዳደረች ባለችበት ግዜ የዜጎች መገደል ህዝብ በነ #ለማ መገርሳ አስተዳደር ላይ እንዲበሳጭ እና ተስፋ እንዲቆርጥ ያደርገዋል። በኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ስብሰባ ዋዜማ እነ ለማን አጣብቂኝ ውስጥ መክተት ነው አላማው። እነ ለማ ሳንዱች ነው የሆኑት ፣ #በቃል አቀባያቸው በኩል ለህዝብ ገዳዮቹን ለህግ እናቀርባለን ቢሉም፣ ህዝብ ሰው በሞተ ቁጥር የምትለቁት ነጠላ ዜማ አረጋቹት እያለ ነው፣ በሌላ በኩል ግድያውን የፈፀመውን አካል አውግዘው አቋም እንዳይወስዱ ዛሬ የሚጀምረው የኢህአዴግ ጉባኤ በሌሎች አባል ድርጅቶች በጥርጣሬ እንዲታዩ እና የጠሚ ቦታውን ለማሳጣት የተዘጋጀ ሴራ ሊሆን ይችላል። በተጨማሪ ከውጭ ዘመቻ ተከፍቶባቸዋል። ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ ብለው ህዝብ ሲያልቅ ዝም አሉ፣ ገና ቤተ- መንግስት ሳይገቡ ያስጨርሱህ ጀመር የሚል የፌክ ሙሾ ተቀጣጥሎባቸዋል።

ስለዚህ የሞያሌ ግድያ የጨለንቆው ግድያ ኤክስቴንሽን(extention) ሲሆን አላማውም ህዝብን ብስጭት ውስጥ በመክተት #ከለማ አስተዳዳር መነጠል ሲሆን፣ እነ ለማንም ከተቻለ ከኢህአዴግ በራሳቸው ረግጠው እንዲወጡ መግፋት ልክ በሽግግር ወክት #የሌንጮ ለታ ቡድን እንዳረገው፣ ይህን የጠላት ዓላማ ለማሳካት አውቀውትም ይሁን ሳያውቁት ከውጭ እነለማ ላይ በህዝብ ደም ተረማምደው ለጠሚ ወንበር እየተሯሯጡ ነው የሚል ዘመቻ ተከፍትዋል፣ ካልሆነም ከህዝብ ጋር ከተቃቃሩ ተገደው ጉዳይ አስፈፃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ሌለኛው ግድያውን ያቀናበረው ቡድን ኢላማ ሊሆን ይችላል።

የሞያሌውን እልቂት በመጠቀም ኦህዴድ የስቸኳይ ግዜ አዋጁ እንዲሰረዝ በቂ መከራከሪያ ማድረግ ይችላል፣ የአሜሪካ መንግስት አዋጁን መቃወሙ ይታወሳል ፣ ስለዚህ የኢንተርናሽናል ኮሚኒቲ ድጋፍም ያገኛሉ ፣እንዲሁም ከየአቅጣጫው የተቀባበለበትን አፈሙዝም ማክሸፊያ መንገድ ይሆነዋል። በመጨረሻም አንድ አንድ ወገኖች አውቃችሁም ይሁን ሳታውቁት ለጠላት ዱላ እየሆናችሁ ስለሆነ ነገሮችን ብጥንቃቄ ብታዩ ለማለት እወዳለሁ።Bedilu Lelisa ነፍስ ይማር.!

Filed in: Amharic