>

“ሀገሪቱ በየቀኑ የሚያስፈልጋት የነዳጅ አቅርቦት ያለምንም ችግር እየቀረበ ነው” - EBC  “የማይመስል ነገር ለህዝቡ አትንገሩ”

[ሳሙኤል ኅይለስላሴና ጸጋዬ አራርሳ
ከዚህ በፊት እኮ፤ 
•~ “የነዳጅ ዋጋ መቀነሱን ተከትሎ ማደያዎች እንከስራለን በሚል ስጋት ነዳጅ ባለማዘዛቸዉና ባለማራገፋቸዉ” . . . ብቻ የነዳጅ እጥረት ተከሰተ ብላችሁን ነበር።
•~ “አንዲት ነዳጅ ጫኝ መርከብ በመዘግየቷ የነዳጅ አቅርቦት ተስተጓጎለ”ም ነግራችሁን ነበር።
•~ “ማደያዎች፤ . . . በሃገሪቱ እየታየ ካለው የዶላር እጥረት አኳያ፤ በየወሩ ንግድ ሚኒስቴር የሚያወጣውን የዋጋ ተመን ተከትለው፤ ነዳጅ ላለማስገባት ስለሚሞክሩ የአቅርቦት እጥረት መከሰቱን” . . . እንደነገራችሁንም ትዝ ይበላችሁ።
•~ “ጂቡቲ ላይ በጣለው ከባድ ዝናብ”. . .  “ባህርዳር መግቢያ ላይ ድልድይ ተበላሽቶ” . . . “አፋር ላይ ከባድ ዝናብ ጥሎ” . . . እነዚህ ሁሉ ለነዳጅ እጥረት መከሰት ሰበቦቻችሁ ነበሩ። ውሸት የማይሰለቸው ኢቢሲ ይህን ቢልም ቄሮ ፋኖ እና ዘርማ ወያኔ በአማራጭነት የያዘውን በባቡር የማጓጓዝ ውጥኑንም አይሰራም አትሞክሩት እያሉ ነው።
ማሳሰቢያ:-
የነዳጅ ተአቅቦው አዲስ አበባ ውስጥ ባሉት የነዳጅ ማደያዎች:ላይ ፍፁምና የተሟላ ተፅዕኖ እንዲኖረው፥ አስፈላጊ የሆኑ ተከታታይ እርምጃዎች ይወሰዳሉ።
1. ሁኔታው እየታየ እንዳስፈላጊነቱ የተአቅቦው ጊዜ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ይደረጋል።
2. እስካሁን አትኩሮት የተደረገው የቦቴ መኪናዎች ላይ ቢሆንም ወያኔ ሌላ አማራጭ ልትጠቀም ትችላለች ከሚል እሳቤ በመነሳት (ብዙ ሊትር የሚይዙ የባቡር ነዳጅ ጫኝ ፉርጎዎችን በቴሌቪዥን ሲያሳዩ ነበር!) የነዳጅ ተአቅቦው ከሰበታ ተነስቶ ጂቡቲ እስከሚገባ ድረስ ያለውን የባቡር መስመር ለማስቆም የሚችል እንዲሆን እንደአስፈላጊነቱ እርምጃ ይወሰዳል። የባቡር መስመሩ በኤሌክትሪክ የሚሰራ ስለሆነ ይኸን ማድረግ እንደማያስቸግር እንኳን ቄሮ ወያኔም ታውቃለች።
በመሆኑም በዚህ አቅጣጫ ለሚወሰዱ እርምጃዎች ሁሉም በያለበት ዝግጁ ሆኖ እንዲጠብቅ እናሳስባለን።
Filed in: Amharic