ክፍል አንድ
በቅድሚያ የትግሬ ወያኔዎች ፀረ-አማራ ፕሮግራም በእነማንና መቼ ተጠንሥሦና ተጠናቆ ለእስከዛሬው የአማራን ዘር የማጥፋት ሰቆቃ እንደዳረገን እንመልከት፣
በአጭሩ የፕሮግራማቸው ይዘትና አላማ ምንድነው? “ትግራይ በዐፄ ምኒልክ የዐማራ አገዛዝ ቅኝ ግዛት ሥር ከመውደቋ በፊት ለብዙ ዘመናት ራሷን የቻለች ነፃ አገር ነበረች። ለዚህም ብቸኛው መፍትሄ የትግራይ ሕዝብ ቀንደኛ ጠላት የሆነውን ዐማራ ማስወገድና “የትግራይን ሪፐብሊክ አገር መሥርቶ በመገንጠል የትግራይን ሕዝብ ከድህነት ማውጣት ነው።ትግራይን እንደ አገር በእግሯ ለማቆም፣ ከጎንደር ወልቃይትን፣ ጠለምትን፣ ጠገዴን፣ ታችና ላይ አርማጨሆን፣ ሠቲትን ወዘተ፣ከወሎ ደግሞ ራያ፣ ዋጃ፣ አላማጣ፣ ኮረም፣ ቆቦ፣ ወልድያን ወዘተ ከዐማራ በማፅዳት ወረዳዎቹን ወደ ትግራይ ማጠቃለል” የሚል ነው። እነኚህ አገርና ሕዝብ አጥፊ ትግሬዎች! በ1966ዓ.ም፣ ዛሬ “ሸንጎ” በሚባለው ድርጅት ውስጥ በተሸጎጠው በአረጋዊ በርሄ የተፃፈውን ረቂቅ ፕሮግራም በመያዝ፣ በእሱው መሪነት እነሥዩም መሥፍንን አሥከትሎ በ1967 ዓም ጥር ወር ላይ ለትጥቅ ትግል ሥልጠና ወደ ሻዕቢያ ዘለቁ።ረቂቁንም ሻዕቢያ አሻሽሎ ሰጣቸው። የካቲት 11ቀን ወደትግሬ ደደቢት ተመልሰው፣ሥምንት ሰዎች ያሉበት በአረጋዊ በርሄ ሊቀ መንበርነትና ተሳታፊነት የመጨረሻውን ፕሮግራም (ዛሬ የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ተብዬው ውስጥ በአመዛኙ የተካተተውን)የካቲት ወር 1968 አፀደቁ።
ለዚህም ተግባራዊነት አባሎቻቸውን በቅድሚያ ወደ ትግራይ ሕዝብ አሠማርተው ሥብከት ሲያካሂዱ፣ “ትግሬ ራሷን የቻለች አገር ሆና እንደማታውቅ እና አማራም የትግሬ ጠላት ሆኖ እንደማያውቅ” በአንድነት የሚያምኑት ትግሬዎች ተቃውሞ በማሰማታቸው ቀስ በቀስ አንድ በአንድ ለቅመው ጨረሷቸው። ኢትዮጵያዊነትን ከትግራይ ምድርና ከትግራይ ሕዝብ አእምሮ እንዲጠፋ አደረጉ። የተቃወሟቸውን ቀሳውስቶች እና የራሳቸውን አባሎችም ጭምር ጨረሱ።ቀሪዎቹን ቀሳውስቶች ካድሬዎች አደረጉ።
ቀጥሎም ፊታቸውን ወደ ዐማራው፣ ወደእነወልቃይት ጎንደር እና ወደእነራያ ወሎ አዞሩ። “በእነዚህ አካባቢዎች የሚኖረውን የአማራ ሕዝብ ሥነልቦናና ባህል ቀስ በቀስ በማስለወጥ፣ ነባር ማንነቱን አውልቆ የትግራዊነት ማንነት ሊያጠልቅ የሚችልበትን ሁኔታ ማመቻቸትና ተገዥ ማድረግ፣ግዛቶቹ የትግሬ እንደሆኑ ሲነገረው ከተቀበለ ጊዜያዊ አጋራችን አድርገን እንጠቀምበታለን፣የማይቀበለውን እናስወግደዋለን(እንገለዋለን)” የሚል አቋም ያዙ።
በእነወልቃይትና በሌሎቹም አካባቢዎች በሚኖሩ ዐማራዎች ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲፈጸምባቸው እነ አረጋዊ በርሄ፣ሥብሃት ነጋ እና መሰሎቻቸው አመራር ሲሰጡ፣ እነሥዬ አብርሃ፣የብሮድካስቱ ዲሬክተር ዘርዓይ አስገዶምና የመሳሰሉት ደግሞ የጥቃት መመሪያውን ተግባራዊ አድርገዋል።መጀመሪያ ወደወልቃይት የተላከው በአንድ በኩል ከአማራ በሌላ በኩል ከትግሬ የሚወለደው ዛሬ አሜሪካ የሚገኘው መኮነን ዘለለው የሚባለው ወያኔ ነበር።ዛሬ አረጋዊ በርሄም ሆነ መኮነን ዘለለው እንዲሁም ሠዬ አብርሀ ከእነመለስ ጋር በሥልጣንና በመሳሰሉት ተገፍትረው፣ተቃዋሚ መስለው እኛን ለማደነጋገር ብቅ አሉ እንጅ ልባዊ አቋማቸው አልተቀየረም። የወልቃይት አማራ ግን ከመጀመሪያው ጀምሮ በቻለው መንገድ ሁሉ ሲታገላቸው እንደቆየና ዛሬም እየታገላቸው እንደሆነ ይታወቃል። ይህ በዚህ እንዳለ በ1969 አረጋዊ በርሄ እና ሥብሀት ነጋ የሚገኙበት ቡድን “ትግራይ የትግሬዎች ብቻ ሥለሆነች”በማለት በትግራይ ውስጥ የሚኖሩ ዐማራዎች፣ኦሮሞዎችና ሌሎች ነገዶች ከትግራይ መሬት ለቀው እንዲወጡ አደረጉ።ከዚያ ቀደም ሲል ግን በአካባቢ ያገኗቸውን ዐማራዎች እየመረጡ ይገድሉ ነበር።
ምንም እንኳን የመጀመሪያ እቅዳቸው ትግራይን ከጎንደርና ከወሎ በሚወስዷቸው ግዛቶች አሥፍተው ለመኖር ቢሆንም፣በለስ ቀንቷቸው ከትግራይ አልፈው ሠፊዋን ኢትዮጵያ እንደሚቆጣጠሩ ሲረዱና ወደአዲስ አበባ ለመጓዝ ሲያቅዱ ደግሞ ወደፊት አማራውን ለማዳከምና አቅመቢስ በማድረግ ከጊዜ ጋር ለጥፋት ዳርጎ ለመግዛት የሚያበቃቸውን ካርታ ፍፃሜ ማድረስ ነበረባቸው።በዚህም መሠረት ቀደም ሲል ሊወስዷቸው ተግባር ከጀመሩባቸው የጎንደርና የወሎ ግዛቶች በተጨማሪ ከአማራው ቆርሶ ሰፊውን መተከልን ለቤኒሻንጉል፣ሠፊውን የወሎ የምሥራቅ አካባቢ ለኤርትራ አሰብ ከተሰጠው በተጨማሪ ለአፋር በማካለል አዘጋጁ።በዚህ ብቻ አላቆሙም፣ በሚከልሉት የአማራ ክልል ውስጥም የአዊ፣የኦሮሞ፣የቅማንት፣ የአርጎባ ወዘተ የሚሉ ቦታዎችንም ሥንቅር አሥገቡ።ለሱዳን የሚሠጡትን የአማራ መሬትም ወሰኑ።
አዲስ አበባም እንደገቡ በ1983ዓ.ም ግንቦት ወር የሽግግር ወቅት በሚል በእነሌንጮ ለታ ኦነግ ሕገ መንግሥት አርቃቂነትና ተባባሪነት፣የተለያዩትን ጎሳዎች ሰብስበው፣ የነባሯን ኢትዮጵያ ማንነት ካርታ፣ የኢትዮጵያን አንድነት እና ሠንደቅ ዓላማዋን አሽቀንጥረው በመጣል፣በአዲስ ባንዲራ በመተካት፣በዘር የተሸነሸነች አዲስ ካርታ ሠሩ። አማራው ግን ጎሳን ባለማቀንቀኑና በኢትዮጵያ አንድነት ብቻ ፀንቶ በመቆሙ ያለድርጅት የነበረና ይህን ስብሰባ ያልተካፈለ ብቸኛው ህዝብ ነበር።
ትግሬ! በእነሌንጮ ኦነግ ተባባሪነት! የተለያዩትን ነገዶች በክልል የሸነሸናቸው ለነገዶቹ አስቦ ሳይሆን፣የአማራውን ኅልውናና አማርኛ ቋንቋን ለማጥፋት ብቻውን እንደማይችል ቀድሞ ሥለሚያውቀው፣ የተለያዩት ነገዶች አማራውን እንደበዳይ ቆጥረው፣ከትግሬ ጎን በመቆም እንዲዘምቱበት ለማድረግ ነው።አንቀፅ 39ኝንም ያሰፈረው አሥቀድሞ ያሰበውን የትግሬን መገንጠል “ህጋዊ ሽፋን” ለማላበስ ነው:: እንግዲህ ከዚህ ስብሰባ በኋላ በአማራ ሕዝብ ላይ በየትኛውም የአገሪቱ ክፍል፣የዝመቱበት ቅስቀሳ ተካሄደበት።ይህም እየተደረገበት አሁንም አማራው የኢትዮጵያን አንድነት የሙጥኝ እንዳለ ነበር።
እነመለስና እነሌንጮ የመጀመሪያው የአማራው ማዳከሚያ ያደረጉት ነገር ቢኖር፣ አማራው የሚኖርባቸውን አካባቢዎች በመቀራመት የዝሆኑን ድርሻ ከወሰዱ በኋላ ቀሪውን የአማራ መሬት ወደአፋር ሌላውን ወደቤኒሻንጉል በማካለል መሸንሸንና አማራውን አጣብቂኝ ውስጥ ማስገባት ነበር። ይህም ከሞላ ጎደል እሥካሁን ሠርቶላቸዋል።ኦነግም በወያኔ ተባሮ የኤርትራ እጄታ እሥከሆነበት ጊዜ ድረስ በእነሌንጮ እየተመራ ከወለጋ ጀምሮ በሐረር በደኖ ወዘተ አማራውን አድኖ መግደሉንና ማፈናቀሉን አጧጡፎት ነበር።ኦነግ ሲባረር ደግሞ ይህንን ተግባሩን ኦሕዴድ ተረክቦት የአኖሌን ሀውልት እሥከማቆም ደርሷል።
ይህ በዚህ እንዳለ፣አማራው በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ክልልህ አይደለምና ውጣ እየተባለ ያለማቋረጥ ሲገደል፣ ሲፈናቀልና ሰቆቃው ጣራ ሲነካ፣አርቆ አሳቢው ክቡር ፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ ከባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅትን(መዐሕድን) አቋቁመው የአማራውን ሠቆቃ ለመታደግ ሲነሱ፣አንጀቱ ያረረውና ቀድሞ የነቃው አማራ ያላንዳች ማቅማማት ከጎናቸው ቆመ።የትግሬ ወራሪዎች!መዐሕድ እየጎለበተ ሲሄድና ሲያሰጋቸው ፕሮፌሰርን ከመሰሎቻቸው ጋር ለእሥር ዳርገው ለሞት አበቋቸው፣ ድርጅቱም ተዳከመ።
መዐሕድ!ከአማራ ድርጅትነት ወደ ኢትዮጵያ አንድነትነት (መኢአድ) ተለወጠ። የአማራው መገደልና መፈናቀል ግን ከድሮው በባሰ መልኩ እየጨመረ ሄደ።
ግድያውና ሰቆቃው እየባሰ በመሄዱ በውጭ አገር አማራው እንደገና የአማራ ድርጅት ፈጥሮ የአማራ መብት ይጠበቅ በማለት ሕዝብን እያነቃ ባለበት ወቅት፣በተለይ ደግሞ አገር ቤት በሐምሌ 2008ዓም አምሥት(5) ሚሊዮን አማራ እንደጠፋ በሚነገርበት ወቅት፣ብዙ ዓመታትን ያሥቆጠረው በወልቃይት ኮሚቴ አማካይነት እየተገፋ የመጣው ”የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ”፣ ፈንቅሎ መውጣት፣ በአማራነት ተደራጅቶ መመከትም እንደሚቻል ለሁላችንም ትምህርትና ድፍረት ሰጥቷል። የትግሬ ዘረኞች! የአማራ ዘር ዳግመኛ እንዳይነሳ አድርገን አከርካሪውን ሰብረነዋል፣ የኦርቶዶክስ ዕምነትም ከአማራው ጋር አልቆለታል ብለው በእርግጠኝነት ተናግረው ሳይጨርሱ፥የአማራው ወጣት በአርንጓዴ ቢጫ ቀይ ሠንደቅዓላማ ታጅቦ የአማራን ማንነት ጥያቄ ይዞ ብቅ ሲል ወያኔዎች የሚይዙትንና የሚጨብጡትን እንዳጡ ታዝበናል።
ይህችን ፅሁፍ በመፃፍ ላይ እንዳለሁ፣ መሣሪያውን እንዲያስረክብ፣55ትግሬዎች ቤቱን የከበቡት ጀግናው አማራ መቶ አለቃ ደርብ አየለ ከ13በላይ ትግሬዎች እርፍርፎ ማሸለቡን ተረዳሁ።ነፍስ ይማር ወንድሜ! ለቤተሰብም መፅናናትን እመኛለሁ። ይህን የሰማህ የትም ቦታ ያለህ አማራ ትጥቅህን እንዳትፈታ፣ከፈታህ በቁምህ ተሰቃይተህ እንደሞትክ ቁጠረው።
በ26ዓመት ተኩል ዕድሜ የኢትዮጵያ አንድነት ትግል ያላሥመዘገበውን ውጤት፣ በአማራ ልጆች ትግል” የአማራ ማንነት ጥያቄ” ጎንደር ላይ ተጀምሮ ዛሬ ወሎ ላይ በጉልህ ታይቷል።ሥለዚህ የአማራው ዘር እየጠፋ ህልውናውን ሳያስጠብቅ የኢትዮጵያን አንድነት ያሥጠብቃል ማለት ዘበት እንደሆነ ይህ ጉልህ ማስረጃ ነው። ልብ ያለን ልብ እንበል።