>

እናንተ የእፉኝት ልጆች ትንሿ የመውጫ ቀዳዳችሁን በደም እያከረፋችኋት ነው (ሙሉነህ ዮሃንስ)

ህወሃት የሚዘውረው ኢህአዴግ እና ግሳንግሶቹ ጭንቅ ውስጥ ገብተው በይፋ ስብሰባ ከተቀመጡ 6 ወራት ዘለቁ! ይፋ ያልሆነውን ቁጥር የለሽ የሽኩቻ ስብሰባ ትተን ማለት ነው። የመንግስት ስራ የሚባል ቆሟል! የውጭ ምንዛሬ ነጥፏል! ህዝብ ስልጣን ልቀቁ ብሏል! እነሱ ግን መሪያቸውን መምረጥ እንኳን ተስኗቸዋል! በትረ ስልጣኗን እየተራኮቱባት ነው! አይደለም ለህዝብ ሊያስረክቡ ከራሳቸው ላለ አካል ማስተላለፍ ሞት ሆኖባቸዋል። 27 አመት ሙሉ አንድ አምባገነን ጨቋኝ ስርአት ህዝባችንን አንገሽግሾታል። የስርአቱ ቁንጮ ነፍሰ በላዎች በሙሉ በእድሜ ገርጅፈው ሰባዎቹ ውስጥ ናቸው…የናጠጡ ሃብታሞች መሆናቸው ሳያንስ አሁንም ህዝብን ተረግጠው የሙጥኝ ብለዋል። ከ40 አመት በፊት ኢትዮጵያን ለማመስ ጫካ ከገቡበት የተረገመች ቀን ጀምሮ እስካሁን ድረስ የአራት ትውልድ እድልን ካልዘወርን ብለው ጃጅተዋል። በተፈጥሮ መሞትን እድል ለራሳቸው እየነፈጉ ነው።
የለውጡ ባለቤት ህዝብ ግን ግልፅ አቋም ይዟል። የነሱ መሿሿም ማብቂያ የሌለውን ድራማ እንሞቀውም። እናንተ የእፉኝት ልጆች ትንሿ የመውጫ ቀዳዳችሁ በደም ያከረፋችሁትን ስልጣን ለኢትዮጵያ ህዝብ መመለስ ብቻ ነው። ስላሰራችሁን ወይም ቅልብ ኮማንዶ ስለላካችሁብን ቀን የገዛችሁ እንዳይመስላችሁ። ይልቅ የትግላችንን ግለቱን ይጨምረዋል! እንደ ሚንቀለቀል ብረት ተቀጥቅጦ የሚበሳ ጦር! የሚቀላ ጎራዴ! የሚቀነድሽ አረር ይወጣዋል! ልቀቁ! ድምፃችን ልቀቁ ነው! ህዝቤን ልቀቁ እንዳለው የፈጣሪ ቃል!
ኢትዮጵያ መንግስት የላትም!
ሕዝቡ መንግስት ይመስርት!
Filed in: Amharic