ቄራ ፔፕሲ በሚገኘው ግዜያዊ ማቆያ ጣቢያ ስደርስ በመጀመሪያ ያገኘኃቸው ማሂና ወይንሸትን ነበር የወጣትነት ግዜዋን ለሃገር እና ለወገን ፍቅር እየገበረች ያለችው ማሂ እጅግ የምትገርም ፍጡር ከራሡአ ይልቅ ስለሌሎች የምታስብ እና የምትጨነቅ እንደሆነች አውቃለው።
ማሂዬ አንዳንዴ ለራስሽም ግዜ ስጪ እንጂ? አልኩአት ከሠላምታው በኃላ አሌክሶ አሁን እኮ የራሴን ኑሮ እየኖርኩ ነው የታሠርኩት ለምን ትጠያየቃላችሁ ብለው ምን አጠፋሁ አለቺኝ ? እንደመቀለድ እያለች በፈገግታ ምንም እንዳላጠፋችሁ እማ እንኩአን እኔ ሃገር ምድሩ ያውቃል! ግን እኔ ልልሽ ያሠብኩት ከተፈታሽ በኃላ መች አርፈሽ ታውቂያለሽ እስር ቤት እየተመላለሽ ታሳሪ ስትጠይቂ ተፈቺ ስትቀበይ ፍርድ ቤት ስትመላለሺ የሌሎቹን ክስ እና ጉዳይ እየተከታተልሽ ለህዝቡ ስታቀርቢ መቼ ነው ላንቺስ ግዜ የምትሠጪው ማለቴ ነው ስላት ይኸው ቤቴ አሁን አረፍኩ ብላ እራሡም ስቃ ፈገግአስባለችኝ ስለኬዛቸው እስካሁን ምንም አይነት ክስም ሆነ እንግልት እንደሌለባቸው እና በርግጠኝነት እንደሚፈቱአቸው ሁለቱም አውርተውኝ በል ደሞ እነበፍቄን ጠይቃቸው ብላኝ ደጉአ ማሂ በፌስታል ኩኪስ እንድወስድላቸው ከሠላምታ ጋር ልካኝ ተለያየን እነ በፍቄ ጋር እስክደርስም ለብቻዬ አለ ፍቅር አለ እያልኩኝ በልቤ እያዜምኩኝ ነበረ። ወንዶቹ አንድ ላይ ስለነበሩ በበፍቄ አማካኝነት ሁሉንም ሠላም አልኩአቸው እና ጨዋታ ጀመርን እስክንድር ጎበስ ቀና እያለ ሲያወራ በመሃል ደግሞ የሚያምር ፈገግታውን ብልጭ ሲያረግ በደንብ ላስተዋለው እራሡን የቻለሃ ሃገር ይመስላል በፍቄ አሁንም ይቀልዳል ይጫወታል አስገራሚ ፅናት እና ጥንካሬ እንዳለው በቅርበት ሥላየሁት ብዙም አልገረመኝም።
የውጪውን አየር በቅጡ ሳይተነፍስ መልሶ የታሠረው ዘላለም ወርቃገኘው ትህትናው እና ፈገግታው አሁንም አብሮት አለ ጀግናው አንዱአለምም ሞቅ ያለ ሠላምታ አቀረበልኝ ሌሎቹም በሥም የማውቃቸው በአካል የማላውቃቸው ታሳሪዎች በፈገግታ ታጅበው ሠላም ሲሉኝ እራሴው በራሴ በውስጤ አንድ ጥያቄ አጫረብኝ ማነው ግን የታሠረው እኔ ወይስ እነሡ ያስብላል ሠላም ካሉኝ ልጆች ውስጥ ግን ከነሡ ጋር አንድ በልጅነታችን ኢለመንተሪ አብሮኝ የተማረ ልጅም ወደኔ ቀርቦ በፈገግታ ታጅቦ አንተ ነህ እንዴ አሁን እኮ ነው ያወኩህ አለኝ እኔም ግራ በመጋባት ስሜት ሞቅ ያለ ሠላምታ ሠጥቼው ለበፍቄ በልጅነት አብረን እንደተማርን ነገርኩት ግን ለምን ከነሡ ጋር አሠሩት ብዬ ልጠይቀው ስል? ወዲያው ከውጪ ውብሸት እና ናቲ ሊጠይቁአቸው መጡ እና ጨዋታችን በነሡ ሠላምታ ተቁአረጠ እኔም ጥያቄን ገታሁት በዚህ መሃል እጅግ የምወደውን ሠው ተሜን እንዲጠራልኝ በፍቄን ጠየኩት ተሜ ተኝቱአል ሲለኝ ክው አልኩኝ ቀስቅሠው ልለው ብዬ ለሡ ያለኝ ፍቅር እና ክብር አፌን ያሸብቦ ያዘው እና ተወው በቃ ይተኛ አልኩትኝ በአክብሮት እና ከአብዛኞቹ ጋር ስለጉዳያቸው አውርተን በተለይ ናቲ ከውጪ ለበፍቄ ባወራለት ዜና ተደስቼ ሁሉንም ተሠናብተናቸው ወጣን ናቲ እንዳለው ኮማንድ ፖስቱ ምንም አይነት ክሥ አልደረሠኝም ብሉአል ይሄንንም በቃና ቲቪ ላይ ሁላ ሣይቀር ተናግሮታል በቃ ይፈታሉ ማለት ነው ብዬ ደስ እያለኝ ወደቤቴ አመራሁ አንድ ነገር ግን ከነከነኝ ያ ከነ እስክንድር ጋር የታሠረው በልጅነታችን የማውቀው የኢልመተሪ ጉአደኛዬ ምን አድርጎ ነው ይሄን ጥያቄ ለማወቅ ታክሲ ውስጥ ሆኜ ስልክ ወደ አጥኔክስ ደወልኩኝ ከሠላምታ በኃላ ቀጥታ ጥያቄዬን አቀረብኩ አታውቀውም እንዴ ስንታየው ቸኮል እኮ ነው አለኝ እንዴ ስንታየው ቸኮልን በስም ባውቀውም በአካል ግን እሡ ይሆናል ብዬ ፈፅሞ አልገመትኩም ነበር እሡም ልክ ስለኔ እንደተሠማው ሁሉ ለማንኛውም ያገሬ ልጆች አንድ ነገር ከሠማሁት ተነስቼ ልንገራችሁ እነ እስክንድር ይፈታሉ እንዴት አወክ ላላችሁኝ ምክንያቴ ኮማንድ ፖስቱ እማውቀው ነገር የለም ብሉአላ መልካም ዜና ሠምቶ መልካም እና ደግ ደጉን መመኘት ኢትዮጵያዊ ወጋችን ነው እና መልካም ፍቺ ለጀግኖቼ ሻሎም!!!
@alex sheger