>

ህወሃት ህወሃት ዶር አቢይ እንዳይመረጥ  መምዘዝ ያለበትን ካርድ ሁሉ መዟል! (ገረሱ ቱፋ)

አሁን እንደድርጅት  የቀረኝ ህወሃት ነው!!
ህወሃት በለፉት የ42 ዓመት እድሜው ብዙ መሰዋዕትነት የከፈለ ድርጅት ነው።መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ድርጅቱ ወደ ስልጣን ለመምጣት ከ60,000 በላይ የትግራይ ወጣቶች ተሰውተዋል። በለፉት 27 ዓመት በህወሃት መሪነት ኢህአዲግ ስልጣን ላይ በቆየባቸው እድሜው የኢትዮጵያ ህዝብ ብዙ መሰዋዕትነት ከፍሏል።
በለፉት 27 ዓመት የኢትዮጵያ ህዝብ በተጠበቀው መጠን ባይሆንም ያገኛቸው ብዙ ጥሩ ነገሮች አሉ።
ኢህአዲግ ላጠፋቸው ነገሮች በቀዳሚነት ህዋሃትን የምንጠይቅ ከሆነ ለመጣውም በጎ ለውጥ የአንበሳውን ድርሻ መውሰድ ያለበት ህዋሃት ነው።
የዛሬይቷ ኢትዮጵያ እና አሁን ያለውን ስርዓት ከነ ምናምኑ ከህወሃት ውጭ ማሰብ ይከብዳል።
ህወሃት ዶር አቢይ እንዳይመረጥ እልህ አስጨራሽ ትግል አድርጓል።ህወሃት እንደ አንድ ጥሩ የእግር ኳስ ቡድን ዶር አቢይ እንዳይመረጥ እስከ ዘጣናኛው ደቂቃ ተጫውቷል። ህወሃት ሰዓት ማባከን የሚጠቅመው ከመሰለው አባክኗል።
መምዘዝ ያለበትን ካርድ ሁሉ መዟል። ህወሃት ለድርጅቱ በአሸናፍነት መውጣት በለው ቁመና ማድረግ የሚችለውን ሁሉ አድርጓል። እኔ ህወሃት እሄንን በማድረጉ ብዙም አልገረመኝም።ምክንያቱም ይህ የአፍሪካ እና የአቢሲኒያ ፖለቲካ ነው።
እንዲሁም የድርጅቱ አንጋፋ አባላት ዛሬም ለዓላማቸው ስኬት ምን ያህል ፅኑ እንደሆኑ ያየሁበት ነው።
እንደዚያም ሆኖ ድርጅቱ የፈለገው ነገር አልሆነም።
ነገር ግን በአጠቃላይ ከየነው ህወሃት በተለይ ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ ፍትህ እና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲገነባ  መስዋዓትነት የከፈሉት የትግራይ ልጆች ትላንትና ያሸነፉበት ቀን ነው።
በሰው ልጅም ሆነ በድርጅት ህይዎት ውስጥ ባህል ከባድ ነገር ነው።መጥፎም ሆነ በጎ ነባር ባህልን ትቶ አዲስ ባህልን መቀበል እጅግ ፈታኝ ነው።
ይህንን ማድረግ የሚችሉ ድርጅቶች በዓለማችን ላይ የተሳካላቸው ተብለው ይመዘገባሉ።ህወሃትም ሆነ ማንኛዉም ግራ ዘመም ድርጅት አስቸጋር ባህል አላቸው።
ምንም ሆነ ምን ህወሃት እልህ አስጨራሽ ትግል አድርጎ የሱ ሃሳብ ሳይሆን የሌላኛው ሃሳብ በብዙሃኑ ተቀባይነት ሲያገኝ ያንን አሜን ብሎ መቀበሉ ያስመሰግነዋል።ህወሃት የግራ ዘመም ፓርቲዎች ባህል የሆነውን መጥፎ ባህል ለመስበር እየሞከረ ነው።ከጊዜው ጋር ለመራመድ ጥረት እያደረገ ነው።በዚህ ሊወቀስ ሳይሆን ሊበረታታ ይገባዋል።
በአጠቃላይ እና በኔ ግምት ህወሃት ትላንት ባራመደው ሃሳቡ ባያሸንፍም ህወሃት ፍትህ እና ዲሞክሲያው ስርዓት ለመገንባት ጫካ የገባለት ዓላማው እና መስዋዓትነት የከፈለለት ሃሳቡ ትላንት አሸንፏል።
ህወሃት ከዚህ በኃላም ያንኑ ገፍቶትበት ኢትዮጵያን ከዚህም በላይ ከፍ ያላች ሀገር ለማድረግ የማይተካ ምና እንደሚጫወት እምነቴ ፅኑ ነው።
Filed in: Amharic