>

ለእኛ ፋሲካ ሲሉ (ታደለ ጸጋዬ)

መቼም ሁሉም ሰው ፋሲካን ይወዳል። ፋሲካን ስናከብር ግን ስቅለቱን መርሳት የለብንም። እኛ ስቅለቱን መኖር ካቃተን ለእኛ ፋሲካ ሲሉ ራሳቸውን የሰጡትን ወንድሞችና እህቶች ለአፍታ እንኳን ልንዘነጋ አይገባንም። ሰሞንኛ አጀንዳዎች ሁሉ ያልፋሉ። በሰሞንኛ አጀንዳ ተጠምደን በግፍ ታስረው ያሉ ወንድምና እህቶችን መዘንጋት የለብንም። በሰላማዊ መንገድ መንግስት ያሰራቸውን ወገኖች እንዲፈታ ልናስገደድው ይገባል። የታሰሩ ወገኖችን በመጠየቅም ቢያንስ ስለእኛ መታሰራቸውን እንዳወቅንላቸው እንዲረዱና እንዲበረቱ ልናደርግ ይገባል። የአገራችን ሁኔታ እንዳያችሁት ነው። ገዥው ፓርቲ አሁንም አልጠራም። ለመጥራትም ፍላጎቱም ብቃቱም ያለው አይመስልም። ከድሃው ህዝብ የተሰበሰበ ግብር ቅርጥፍጥፍ አድርጎ የበላ ባለስልጣን የሚሾም የሚሸልም ሥርዓት በአስተሳሰብ የተለዩ ሰዎችን ምንም አይነት የህግ መተላለፍ ባይኖርባቸውም እንኳን ያስራል። ሰላማዊነትን በኢህአዴግ ዘንድ ሽብር ነው። ቤተሰባዊ ወግ በታጥቦ ጭቃዎች ዘንድ ወንጀል ነው። ስለበሰበሰው ኢህአዴግ ላወራ አይደለም። ጊዜም የለኝም። ማለት የፈለግሁት እየተከፈለልን ያለውን መስዕዋትነት አንርሳ ነው። የኢህአዴግ መጫዎቻ የሆንነው አሁን ላይ የደረስነውም ስለምንረሳ ነው።
Filed in: Amharic