
_
በጥይት ተቀጥቅጦ እንዲገደል የወሰኑት ውሳኔ ተግባራዊ ተደረገ ፤ ወታደሮች የጠብመንጃቸውን የእሳት መለኮሻ ምላጭ ደግመው ደጋግመው ሳቡ ፤ በወንጀለኛው ወታደር ላይ የጥይት ጎርፍ ለቀቁበት ፤ ጭንቅላቱ ተበርቅሶ ፣ ጀርባው ወንፊት ሆኖ በሕዝብ ፊት ተገቢውን ቅጣት ተቀብሎ ተገደለ! ሕዝቡም የደርግ መንግሥትን አመሰገነ ! እርምጃው አዲስ አበባ ካሉት ሊቀመንበሩ ዘንድ ደረሰ ፤ ” ደግ አደረጋችሁ!!!” አሉ ፤ የደርግ መንግሥት ከትግራይ ክ/አገር ለ 17 ዓመታት ስሙኒ ሳንቲም ግብር አልሰበሰበም!!! 17 ቀኖች ወይም ወሮች አይደሉም ! 17 ድፍን ዓመታት!!! ከዚህ በተጨማሪም አጤ ኃይለሥላሴ የደበቀውን የትግራይ እና የወሎ ህዝብ ረሀብን ለመላው ዓለም ያጋለጠው የደርግ መንግሥት ነው ፤ የወታደራዊው መንግሥት ግብረገብነት ከዚህም ይልቃል! የኢትዮጵያ አብዮታዊ ሠራዊት ፍጹም ጨዋነት ከዚህም ይልቃል ፤ ዛሬ ግን በዘመነ ድንቁርና ህወሓት ፣ ያንን ምስኪን ሠራዊት አለግብሩ ቆሻሻ ስም ተለጥፎበታል ፤ ይህንን አለምክንያት አልጻፍኩም ፤በምክንያት ነው ! ከሥር የምትመለከቷት እህታችን አያንቱ ሙሀመድ ትባላለች ፤ የሀረርጌ ቆቦ ከተማ ነዋሪ ናት ፤ ባለትዳርና የ 7 ወሮች እርጉዝ ነበረች ፤ በትላንትናው ዕለት በአግአዚ ሠራዊት አጠገብ ” አገር አማን ” ብላ ታልፋለች ፤ ወታደሮቹ ለቅኝት የተላኩ እንጂ ፣ በእሷ ላይ የሞት ደብዳቤ ይዘው መምጣታቸውን አላስተዋለችም! ወታደሮቹ በግዳጅ የወሲብ ጥቃት ሊፈፅሙባት ሲሞክሩ ” ኧረ የሰው ያለህ! ኧረ የሕግ ያለህ ድረሱልኝ!” ብላ ጮኸች ፤ በዚህን ወቅት አውሬዎች ባነገቱት ጠብመንጃ እሳት ግንባሯን አነደዱት ፤ እስከወዲያኛው አሸለበች! ሁለት ነፍስ በዘግናኝ ሁኔታ ገደሉ ፤ ወታደሮቹ ይህንን በማድረጋቸው ዛሬ ላይ ምንም የተወሰደባቸው የቅጣት እርምጃ የለም! ቢበዛ ቢበዛ ወደሌላ የግድያ ቀጠና ቢቀየሩ ነው ፤ ነገ ግን የግፉአን አለኝታ የኾነው የጉልበተኞች ሁሉ ጉልበተኛ አላህ ፣ ያልጠበቁትን መዓት እነሱ ላይ እና ፣ ግርድና የቆሙለት አረመኔ መንግሥት ላይ ያወርዳል!!!
ግን ግዜአችሁ ቀርቧል ፤ ደም እንባ የምታለቅሱበት ግዜ ቀርቧል ፤ አብይ አህመድ ሆይ ብልህ ከሆንክ በግዜ እንደ ኃይሌ መልቀቂያ አስገባ! ከተጠያቂነት አታመልጥም ፤ ጊዜ ለኩሉ ፤ የደርግ እና ህወሓት መንግሥት ልዩነቱ በጥቂቱ ይህንን ይመስላል ፤በተረፈ እህቴ ሆይ አላህ ጀነቱል ፊርደውሰል አዕላ ማረፊያሽን እንደሚያደርገው ጥርጣሬ የለኝም! ሸሂድ ነሽ ፤ የጀነት ምንጣፍ መላኢካዎች ያንጥፉልሽ! የጀነት መዓዛ እመቃብርሽ ዘንድ አለማቋረጥ ይግባ ፤ ባል ሆይ! ሰብር አድርግ ፤ የትክክለኛ ሷቢር ምንዳ ጀነት ነው! ስብራትህን አላህ ይጠግንልህ!!!