>

የሞተን ፈረስ ለግልቢያ ማን ያስበዋል? አጋራችሁ አሜረካም ኤች አር 128ን አጸደቀችባችሁ!?! (ሉሉ ከበደ)

ይድረስ ለህውሀት ሰዎች። ቀን እየጨለመባችሁ ነውና ንስሀ ግቡ። እናንተና ፤ ከሌላውም ዘር ከአማራው ፤ ከኦሮሞው ፤ከሌሎችም ጎሳዎች ፤ ከእንሰሳ ትንሽ ሻል ባለ ሁኔታ የሚያስቡ ደካማ ግለሰቦችን እየመለመላችሁ ፥ በዙሪያችሁ በመኮልኮልና የሴራችሁና የተንኮላችሁ ሁሉ አስፈጻሚ በማድረግ ፤ የተጠቀማችሁባቸውን ግለሰቦች ጨምሮ ፤ ባለፉት ሀያሰባት አመታት  ለናንተ የምድር ገነት ለመላው ህዝብ ሲኦል  የሆነች ኢትዮጵያን በመፍጠሩ ረገድ የተሳካ ስራ ሰርታችኋል። በአለማችንም ሆነ በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ  ተሰምቶ የማይታወቅ አስደንጋጭና ዘግናኝ ድርጊት  አሳይታችሁናል።ኢትዮጵያ የባህር በር አያስፈልጋትም ብላችሁ ሊኖረን የሚችለውን የአሰብ ወደብ አሳጥታችሁናል። ኤርትራ ክፍለሀገር በሀይል እንዲገነጠል አድርጋችኋል። በሀይል ለተገነጠለ ክፍለሀገር የመንግስትነት እውቅና ከሁሉ ቀድማችሁ  ሰታችኋል።የመገንጠልን መብት በህገመንግስቷ ያጸደቀች በአለም ብቸኛዋ ሀገር ኢንዲኖረን አድርጋችኋል። ባባቶቻችን ደም የተጠበቀ ግዛት ቆርሳችሁ ለሱዳን አሳልፋችሁ ሰታችኋል። በመሬቱ ላይ የሚኖረውን ኢትዮጵያዊ ገበሬ ከባእድ ሱዳን ጋር ተጋግዛችሁ ጨፍጭፋችኋል። የመላ ሀገሪቱን ዜጋ እስከ ንኡስ ጎሳ ድረስ ዝቅ ብላችሁ  ከፋፍላችኋል። ለማጋጨት ደም ለማፋሰስ ስትቅበዘበዙ ህዝቡ አሻፈረኝ ሲላችሁ እራሳችሁ አንዳችሁ ያንዳቸውን ጎሳ ፤ አንዳችሁ የሌላውን ጎሳ ልብስ እየለበሳችሁ ፤ ሰላማዊ ኢትዮጵያውያንን በማረድና በማሳረድ  ብዙ ደም አፍሳችኋል።ሀያሰባት አመት የፈጸማችሁትን ግፍ ዘርዝሬ ለመጨረስ አይደለም። በቅርቡ ኦሮሞና ሶማሌ ክልል መሀል ላይ ጦር አዝምታችሁ  የፈጃችሁት  ባስርሺ የሚቆጠር የኦሮሞ ህዝባችን ደሙ አልደረቀም። ከሚሊዮን በላይ እንደተፈናቀለ መውደቂያ አቶ ስቃይ ላይ ይገኛል። ኢሬቻ በአል ላይ እንዲያልቅ ያደረጋችሁት ሰባት መቶ በላይ ኦሮሞ በልባችን የተወው የሀዘን ቁስል ጠገግ ሳይል ነው በሰላማዊው ህዝብ ላይ ጦር ያዘመታችሁት። ጨለንቆ አዝመራ ሊሰበስቡ ማሳ ላይ አርሶአደሮች ተሰብስበው ነበር። ስለምን  የሀገራቸውን ባንዲራ ያውለበለበ የሀገራቸው ጦር ሰራዊት እርሻ ውስጥ ገብቶ ገበሬዎችን እሩምታ ተኩስ ይከፍትባቸዋል? ይጨፈጭፋቸዋል? በጎንደር በጎጃም በወሎ በናንተ ጥይት የወደቁ ዜጎች ድምጽ ከመቃብር በላይ ይጮሀል። የፈሰሰው ደማቸው እስካሁን ጠገግ አላለም። ይህን ሁሉ የምታደርጉት የያዛችሁት የመንግስትነት ስልጣን አይታችሁ በማታውቁት ሀብት ስላጥለቀለቃችሁ፤  በጃችሁ የገባው ሀይልና ስልጣን ህዝቡን እንዳሻችሁ ለማድረግ የሀገሪቱን ሀብት እንዳሻችሁ ለመዝረፍ ስላስቻላችሁ ፤ ዘላለማዊ ገዢ ለመሆን ወሰናችሁ።  ዘላለማዊ ተጠቃሚነትን ለመቀጠል አሰባችሁ። መስሏችኋል። ሁሉም ነገር ልክ እንዳለው አላወቃችሁም።
 ኢፈርት የሚባል የዘረፋ ድርጅት አቋቋማችሁ።ከአርባ በላይ ግዙፍ ኩባንያዎችን በስሩ ያስተዳድራል። መላውን የሀገሪቱን የስራ መስክ ተቆጣጥሮ ለናንተው ብቻ የሚሰራ ገንዘብ በአካፋ የሚያስገባላችሁ ድርጅት ሆነ። በተሰረቀ የሀገርና የህዝብ ገንዘብ የተቋቋመ ድርጅት ነው። የሀገር ብሄራዊ ሀብት መሆን ሲገባው በቡድን ተቆጣጠራችሁ ይዛችሁታል።ትከሻችሁ ሊሸከመው የማይችል ሀብትና ንብረት ተንገብግባችሁ አዝላችሁ ቆማችኋል።የመንግስቱንም ሆነ የግሉን ስራ በሀገር ያለውን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በሙሉ ተቆጣጥራችኋል።ኢንዱስትሪ ፤ የውስጥና የውጭ ንግድ፤ ትራንስፖርት፤ ማእድን፤ የርሻ ልማት፤ ግንባታ፤ ሌላው ቀርቶ  ደም ፤ የልጆቻችንን ደም ነግዳችሁበት የገንዘብ ምንጭ ፤ የሚሊዮን ዶላር ገቢ ምንጭ አድርጋችሁታል።በሰላም አስከባሪ ስም የምእራባውያንን ጥቅም ለማስጠበቅ ልጆቻችንን በገፍ በሱማሊያና በየትም ስታዘምቱ እናያለን። የተባበሩት መንግስታት ለዘማቹ ሰራዊት የሚከፍለውን ጠቀም ያለ ገንዘብ የህውሀት ጀነራሎች እየተቀበሉ ባንካቸው ያጭቁታል። የሌላው አገር ወታደር ደሞዙ እንዳለ በቀጥታ  ሳይቀናነስ ይከፈለዋል።የኛው ሰራዊት ግን ከመደበኛ ደሞዙ ትንሽ ሳንቲም ተጨምሮ ባንክ ገብቶልሀል ይባላል። ጥያቄ ቢያነሳ ይገደላል።አብላጫው የደሙ ዋጋ የወያኔ አዛዦች ኪስ ይቀራል። አለ የተባለውን ስራ ሁሉ ከህዝቡ ቀምታችሁ ወስዳችኋል። ኢትዮጵያ እናንተ እጅ ላይ ከመውደቋ በፊት አፈር ልሰው የተነሱ ባለሀብቶች ፤ ክቡር ዜጎች  በሙሉ ዛሬ የሉም። ስራቸውን ቀምታችሁ ሀብታቸውን ንብረታቸውን ዘርፋችሁ ለራሳችሁ ወስዳችሁታል። ባለቤቶቹን ካገር አባራችኋል። የሚታሰረውን አስራችኋል። ቆሽቱ የነደደም ሞቷል። እናንተ በተድላ በደስታ በሀብት ላይ ሀብት እየጨመራችሁ በመኖር ላይ ናችሁ። ድሀውንም ከየመኖሪያ ቀዬው እያፈናቀላችሁ መሬቱን ትቸበችባላችሁ።  ዝቅ ብላችሁ የህብረተሰቡን ስራ እስከ ተራ እንጀራና ጠላ ችርቻሮ ያለ ይሉኝታ ተቆጥራችሁ ደማችንን ስትጠቡ ሀያ ሰባት አማታት ተቆጠሩ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የግል ንብረታችሁ ሆኗል። ትግሬ የሚባል ወራሪ ቅኝ የገዛ እስኪመስል ድረስ  ባየር መንገድ ከጠራጊ እስከ የመጨረሻ ሀላፊ ያለ ይሉኝታ  እየተርመሰመሳችሁበት ነው። የግምሩክ መስርያ ቤት ይብሳል። የሚገባው የሚወጣው የትግሬ ንብረት ሁሉ አይቀረጥበትም። የሌላው ዜጋ ንብረት ከዘረፋ በማይተናነስ መልኩ ይዞ የመጣው እቃ ቢሸጥ የማይተካውን ገንዘብ እንዲከፍል ይገደዳል። የሚያስደነግጠው ነገር ወደውጭም ሆነ ሀገር  ውስጥ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚያደርገውን በረራ ሁሉ የሚመላለስበት ትግርኛ የሚናገር መንገድኛ ብቻ ሆኗል። ሌላው ህዝብ አልፎ አልፎ በአነስተኛ ቁጥር እንደሆነ ኢትዮጵያውያን አምርረው ይናገራሉ። የነበረውን የኢትዮጵያን ህዝብ ወዴት አደረሱት ያሰኛል።
ሀያ ሰባት አመት ሙሉ ሰው ገደላችሁ ፤ቤት አፈረሳችሁ፤ ንብረት ዘረፋችሁ፤ ህዝብ አፈናቀላችሁ፤ አሰራችሁ፤ ገረፋቹ ፤አኮላሻችሁ ፤ዘር አመከናችሁ፤ ዘር አጸዳችሁ ፤ሀገር ሸጣችሁ። እስካሁን ግን አልረካችሁም።በቃን ሳትሉ ቀኑ እየጨለመባችሁ መቷል።
በአፈና በግድያና በዘረፋ ቀፍድዳችሁ ሀያ ሰባት አመታት የቀጠቀጣችሁት ህዝብ ትግስቱም ፍርሀቱም ቁጣውም ግድቡን ጥሶ ተነስቷል። እራሳችሁ ኮትኩታችሁ ያሳደጋችኋቸው ወጣቶች የኢትዮጵያን ህዝብ ጥያቄ አንግበው እነለማና  አብይ ሌላ ገጽታ ለብሰው ብቅ ብለውባችኋል። ተከድታችኋል።ህዝቡም አንድ ሆኖባችኋል። ከምድር ኢትዮጵያ የናንተን  መጥፋት የማይፈልግ ሰው  የለም። ትግሉ የቄሮ የፋኖ የዘርማና የነብሮ እናንተን ሳይቀብር አይቆምም።
 በሎሌነት ስታገልግሉት የኖረው አሜሪካም አይቀሬውን ፍጻሜአችሁን አረጋግጧል።የምትቀጡበትን ህግ Hr 128 አጽድቆላችኋል። ይሕ ሕግ እንዳይጸድቅ በሚሊዮን ዶላር ከዚያው መከረኛ ህዝብ እየሰረቃችሁ ለሎቢስቶች ስትገፈግፉ ብትከርሙም አሜሪካ ብልጡ የሞተ ፈረስ አይጋልብምና የምትቀጡበትን ህግ ተስማምቶበት አድቋል። ልጆቻችን ጭዳ እየሆኑለት ለአመታት ልጆቹን ከሱማሌ የጦርነት እቶን አድኖ ነበር። አሸባሪዎችን እኛ እንዋጋልሀለን ብላችሁ። እድሜ ለናንተ የድሀ ልጆቻችን የደም ግብር እየከፈሉ አሜሪካ ልጆቿ ቤት ይውሉላት ነበር። አሁን ግን የኢትዮጵያ ህዝብ የናንተን ቀን ሊያጨልማት መሆኑ ስለገባው ሙት አያስታሙም። ምክንያቱም በምስራቅ አፍሪካ ቀንድ የናንተም አስፈላጊነት አክትሟል። ስድስት ሰባት የአለም ስልጡን ጦር ጂቡቲ ላይ ድንኳኑን ተክሏል።
እንደሰው የሚያስብ አእምሮ ካላችሁ የመዳን እድል  በጃችሁ አለ።የሚበጃችሁን በምሳሌ ልንገር። ሀይለኛ አውሎ ንፋስ ሢነሳ ለጥ ብሎ መሬት ላይ የሚወድቅ ተክል ይድናል። ተገትሮ ከማእበሉ የሚሟገት ዛፍ መጀመሪያ ቅጠሎቹን ያጣል።ቀጥሎ ቅርንጫፎቹ ሁሉ ተገነጣጥለው ይወድቃሉ። መጨረሻ ላይ እርቃኑን የቆመው ግንድ እንደተገተረ ከስሩ ተመንግሎ የመጨረሻ ሞት ይሞታል። ንፋሱ ሲያልፍ ያ የወደቀው ቀና ብሎ ህይወቱን ይቀጥላል። በግትርነታችሁ ከቀጠላችሁ እናንተም መሰበራችሁ ነው። ከዚያ በፊት ግን ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ለመተባበር ፍቃደኛ ከሆናችሁ እነ ዶክተር አብይ የጀመሩት ቀና የሽግግር መንገድ ማምለጫ ሊሆናችሁ ይችላል።
እየሸረባችሁት ያለውን ሴራ ተንኮልና ሸፍጥ አቁሙት። የትግራይ የበላይነት የሚቀጥልበት ተአምር ከንግዲህ ሺ ስብሰባ እየተደበቃችሁ ብታደርጉ አይኖርም። የትግራይ ህዝብ እኛ ከቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ እንበልጣለን ፤የበላይ መሆን አለብን በማለት እናንተን ለበላይነታችን ታገሉ ብሎ አልጠየቃችሁም።  ህውሀት ማለት የትግራይ ህዝብ ነው የምትሉትን ማጭበርበሪያ ማንም አይቀበልም። የትግራይ ህዝብ የኢትዮጵያ ህዝብ ነው። ይልቅስ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር የሚፋጠንበትን መንገድ ራሳችሁ ጀምሩት። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ  ህገ መንግስቱ ላይ ያለውን ሙሉ ስልጣኑን እንዲጠቀም ገለል በሉለት። ጦርሰታዊቱን ደህንነቱንና ፖሊሱን መልሶ እንዲያዋቅር ሁሉም የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም ሊያስጠብቁ በሚያችል መንገድ እንዲሆን ተባበሩ። የማይቀረውን ተጠያቂነትም ለመቀበልተዘጋጁ። ምክንያቱም የስንት ሺ ዜጎች ህይወት ያላግባብ ጠፍቶ፤ ስንትሺህ ህዝብ ከመኖሪያው ተፈናቅሎ፤ ሀብትና ንብረቱን አቶ ፤ ሀገር በሉአላዊነቷ ላይ ስንት ጉዳት ደርሶባት፤ ይህን ሁሉ ጥፋት ማለፍ አይቻልም። ለዚህ ይቅርታና ምህረት አይኖርም ። በስህተት የተደረገ ነገር ሳይሆን ሁሉም ሆን ተብሎ ታስቦበት ታቅዶ የተሰራ ወንጀል  ስለሆነ ይቅርታ አይኖረውም ። አማራና ኦሮሞን ለማጋጨት በቂ ስራ እንዳልሰራችሁ ባደባባይ ቁጭታችሁን መግለጻሁ  የቅርብ ማስረጃ ነው።ይህ ሁሉ ክፋት ተንኮልና ሸር በውስጣችሁ ታጭቆ እናንተን ይዞ መቀጠል የስር አት ለውጥ ሊያመጣ አይችልም። ሁሉም ነገር ፈርሶ እንዲሰራ ተባበሩ። እንቢ ካላችሁ ህዝቡ ያፈራርሳችሁና በመቃብራችሁ ላይ የኢትዮጵያ ትንሳኤ እውን ይሆናል።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
Filed in: Amharic