>

መላኩ ፈንታ የቂመኛው እና ሴረኛው በረከት ሰለባ!?!  (ሚኪ አምሀራ)

ህወሃት ባንድ ወቅት የህዝብ ትኩሳትን ለማብረድ ብሎ በሙስና ወንጀል የያዛቸዉን አባሎቹ በሙሉ ፈቷቸዋል፡፡ ትናንት ደግሞ በከባድ ሙስና ወንጀል ታስረዉ የነበሩ የፋብሪካ፤የሆቴልና የመሳሰሉ የህወሃት ባለሃብቶችን ፈቷል፡፡ ከተፈቱት ዉስጥ ነጋ ገብረእግዛብሄር ይገኝበታል፡፡ የነጻ ትሬዲንግ፤ኮሜት ሃላፊነቱ የተጠበቀ የግል ማህበርና ሌሎችም ባለቤት ነዉ፡፡ተከሰዉ የነበሩትም በመላኩ ፋንታ መዝገብ ነበር፡፡
ኦህዴድ ዘላለም ጀማነህ የተባለ እንዲሁ የኦሮሚያ ክልል የግብርና ቢሮ ሃላፊና የኦህዴድ ስራ አስፈጻሚ አባል የነበር ከሁለት አመት በፊት በከፍተኛ ሙስና ወንጀል ታስሮ ነበር፡፡ ሰሞኑን ተፈቷል ተብሏል፡፡
መላኩ ፈንታ ይሄ ነዉ የሚባል ጥፋት ሳይኖርበት እነዛን ኮንትራባንዲስቶች አገር ልታጠፉ ነዉ፡፡ የአማራ ህዝብ መፈናቀል የለበትም ስላለ ቂም ተይዞበት ይሄዉ ለመቅጣት እንኳን ጥፋት አተዉ 5 አመት ሆነዉ ፍርድ ቤት ከሚያመላልሱት፡፡ አገሪቱ እንደሱ አይነት ኢኮኖሚስት አይታ አታዉቅም፡፡ ብአዴን በአዉራ ጣቱ የሚፈርም ዱልዱም ሰብስቦ ከሚላቀስ ይሄን ኢኮኖሚስትና የፓሊሲ ከፍተኛ ባለሙያ አስፈትቶ ድርጅቱ ላይ ነብስ ቢዘራበት ነዉ የሚሻለዉ፡፡ ያኔ አማራነትን ስላቀነቀነ ነዉ የታሰረዉ፡፡ አሁን እኮ በቃ የአማራ ጉዳይ ተሰብሮ ወቷል፡፡ ሁሉም ወደ አማራነቱ ተመልሶ፤ ሁሉም እያቀነቀነ ነዉ፡፡ ከዚህ በኋላ አሱን አማራ ብሏል ብሎ ማሰሩ ትርጉም የለዉም፡፡
መላኩ በነገራችን ላይ የመጀመሪያ ዲግሪዉ ኢኮኖሚክስ ሲሆን፤ በቢዝነስ አድሚኒስተሬሽን የማስትሬት ዲግሪ (MBA); ሌላ የማስትሬት ዲግሪ በአለም አቀፍ የገቢ አስተዳደር፤ ሌላ ዲፕሎማ በከተማ ፕላንና መልካም አስተዳደር፡፡
የገቢወች ቢሮ መመራት ያለበት በተማረና ስነምግባር ባላቸዉ ባለሙያወች ነዉ ብሎ ከዩኒቨርስቲ የተመረቁ ወደ 10 ሺህ የሚጠጉ ሰራተኞችን ተገቢዉን ስልጠና በመስጠት ወደ ስራ አሰማርቷል፡፡
ከበረከት ጋር ያለዉ ቂም ምንድን ነዉ?
በረከት ስሞኦን  እንደ አቶ ከተማ ከበደ ያሉ ሰዎችን ያለ ማስረጃ እሰር በማለት፤ በታክስ የታያዙ ሰዎችን ልቀቅ በማለትና  አቶ መላኩ ህግ መከበር አለበት ሲሏቸው በዳኞች ላይ ተእጽኖ  በመፍጠር በማስፈታትና  ቀረጥና ታክሱ ብቻ ሁለት ሚሊዮን የሚሆን በባለቤታቸው ወንድም የመጣ ካሜራ  እንዲወረስ በማድረጋቸው ይህንንም  በብአዴን ሥራ አስፈጻሚ ግምገማ ላይ አቶ በረከት ስሞኦን ህግ እና ህገ መንግስቱን እየጣሰ ነው ብለው ጠንከር ያለ ሂስ ማንሳታቸውና  ከዚህ በኋላ አቶ በረከት ስሞኦን ቂም በመያዛቸው በአቶ  መላኩ ፈንታ እሥራት ቀንደኛ ተባባሪና የአሳሪዎች ተልዕኮ ወደ ብአዴን  ለማስወረድ ብርቱ ትግል ሲያደርጉ እንደነበር ውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ፡፡አቶ በረከት ስሞኦን በተመደቡበት ተቋም በአንዱም ለውጥ  ያላመጡ  ሌሎች የሚሰሩትን በመገምገም ተጠያቂ  በማድረግና በማስወገድ እንደሚታወቁ በስፋት ይታወቃል፡፡
የመጀመሪያዉ ፎቶ የህወሃት አባሉ በቅርብ የተፈታዉ፤ ቀጥሎ ያለዉ የኦህዴዱ አባልና በቅርብ የተፈታዉና ሶስተኛዉ የብአዴን አባልና እስር ቤት ያለ፡፡
It is really a shame to ANDM.
ANDM CC office ANRS Communication Affairs Office Gedu Andargachew
Filed in: Amharic