>
5:31 pm - Friday November 13, 4865

ለእውነት የታሰሩት አባቶች ተፈተዋል ይኽ የዘረኞች ጀምበር የመጥለቁ ምልክት ነው!!! (ዘመድኩን በቀለ)

~ በቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ተብዬዎች ባፍር ብሸማቀቅም ” የዋልድባ መነኮሳት አባቶቻችንን ግን ” እግዚአብሔር እንደ ዘመኑ ጳጳሳት፣ ካህናትና መነኮሳትም አይደለምና የቆብ ወንድሞቻቸውን ባይጠይቁ ፣ ባይሟገቱላቸውም ጊዜው ሲደርስ ይኸው ዛሬ ነፃ አምላከ ሳሙኤል ነፃ አውጥቷቸዋል።
~ ይኽ የዘረኞች ጀምበር የመጥለቁ ምልክት ነው ። አሁን በመንግሥታዊ ተቋማት ውስጥ ዘረኝነት ሸምቀቆ ገብቶበታል ። ዋናው የትግል አቅጣጫችንን ወደ ቤተክርስቲያን ውስጥ ተውሳኮች ማዞር አለብን
~ የእኛ ብቻ መፈታት ምን አያስደስትም ። የቀሩት የህሊና እስረኞች እስኪፈቱ ድረስ ለአምላካችንም ሆነ ወደ መንግሥት መጮሃችንን እንቀጥላለን ብለዋል ። ሰሞኑንም ቢያስገቡንም ባያስገቡንም ወደ ቤተመንግሥት ሔደን ጠቅላይ ሚንስትሩን እናነጋግራቸዋለንም ብለዋል።
~ ወዳጄ እስከ አሁን ታስረው የነበሩት መነኮሳቱ ብቻ አልነበሩም ። ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም እንጂ ። እስከ አሁን ሲዋረዱ የነበሩት ሁለቱ መነኮሳት ብቻ አልነበሩም ። ቅድስት ቤተክርስቲያንም እንጂ ። የአቡነ አረጋዊ ፣ የአቡነ ተክለሃይማኖት ፣ የአባ ሳሙኤል ዘዋልድባን ቆብ ጭምር ነው ህውሓት ስታዋርደው የከረመችው ። ህውሓት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንንና የዐማራውን ነገድ #ጨቋኟ_ዐማራ የሚል የክርስትና ስም አውጥታ ቤተክርስቲያኒቱን ለማዋረድ በማኒፌስቶዋ ላይ ጭምር በግልጽ ከትባና ቀርጻ ነው ትግሏን የጀመረችው ።
~ በብዙ መልኩም ቢሆን ተሳክቶላታል ። ቅርሶቿን አውድማለች ። ከ4 ሺ በላይ ተቀናሽ ትግርኛ ተናጋሪ ታጋዮችን ግማሹን በአስተዳደር ሥራ ላይ ፣ ግማሹን ቆብ አጥልቃ ጳጳስ በማድረግ ፣ ገሚሱን የአብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪ በማድረግ ፣ ገሚሱን ቄስ ዲያቆን በማስመሰል ቤተክርስቲያን ላይ እንደ ጆፌ አሞራ በላይዋ ላይ ሰፍረው እንዲቦጫጭቋት አድርጋለች ።
በቃኝ የማያውቁ ፣ ሼም ፣ ይሉኝታ የሌላቸው ፣ እንብርት ያልተፈጠረላቸው ፣ የማይጠረቁ ፣ ስግብግቦች ፣ በሁሉ ቦታ እንደ እርጎ ዝንብ ጥልቅ የሚሉ ፣ ለሚሠሩት ወንጀል ህግ የማይጠይቃቸው ፣ ትዕቢተኞች ፣ በበታችነት ስሜት የሚሰቃዩ ፣ ሌቦች ፣ ዘራፊዎች ፣ መላው የትግራይ ህዝብ በእነሱ ነውር የተነሳ እንዲሰደብ የሚያደርጉ ዘር አሰዳቢዎች።
ህውሓት እንዲህ አድርጋ ነበር ቅድስት ቤተክርስቲያንን ለማዋረድ የጣረችው ። ቤተ ክርስቲያን ግን የአዋራጇን የህወሓትን ውርደት እያየች ፣ አከርካሪዋን ሰብሬዋለሁ ያለችውን ህወሓት አከርካሪዋ ተሰብሮ መላወስ አቅቷት ጭንቅ ውስጥ ገብታ ስትቃትት እያየች እሷ ግን በክብር ቆማለች።
~ አሁን የእያንዳንዱን ጳጳስ ቪላ ፣ ፎቅ ፣ ድርጅት መዝግብ ፣ ፎቶ ቪድዮ ቀርፀህ ዶክመንት አስቀምጥ ። በባንክ የምትሠሩ የተዋሕዶ ልጆች የእያንዳንዱን ዘራፊ የባንክ ሒሳብ በዶክመንት መልክ አስቀምጡ ። ለእኔም ላኩልኝ ። ምድረ ዘራፊ የበላትን የሚተፋበት ጊዜ ሩቅ አይደለም ። ከድኻ መቀነት ተፈትቶ ለቤተክርስቲያን የተሰጠ ሳንቲም የማንም ጡረተኛ ታጋይ መዘሞቻ ፣ ሆኖ አይቀርም።
~ ሻሎም.!  ሰላም.!
Filed in: Amharic