
በነገራችን ላይ አማርኛ ስትናገሩ ለአማራ እንደጠቀማችሁ ማሰባችሁን ማቆም አለባችሁ፡፡ አማርኛ በመናገራችሁ እናንተ ናችሁ የምትጠቀሙት፡፡ አማራ ቤሳ ቢስቲን አያገኝም፡፡ እንግዲያውማ አንድ “መሪ” የሚያስተዳድረውን ህዝብ ቋንቋ መናገሩ ተገቢ ነው፤ ስሜታዊ ትስስር (Emotional attachment) ይፈጥራል፡፡ ስለዚህ አብይ በኦሮምኛም፣ በትግርኛም መናገሩ ተገቢ ነው፡፡ ተገቢ ያልሆነው ነገር ግን የተናገረው ንግግር ይዘት ነው፡፡ ንግግሩን እንኳን በትግርኛ በ”ልሳንም” ቢናገረው ትክክል ካልሆነ አልሆነም ነው፡፡ እናም የህወሀት ካድሬዎች አብይን ትግርኛ ማናገር ብቻ ሳይሆን ትግሬ ማድረግ ትችላላችሁ፡፡ የእኛ ጉዳይ አይደለም፡፡ የእኛ ጉዳይ ወልቃይትን መልሱ፤ ከዛም ባሻገር እኔ እኔ ብቻ አትበሉ ነው፡፡ እውን እዛ መቀሌ ላይ ሲናገሩ የነበሩት ሰዎች እና ሌሎች ካድሬዎች የሚያስተጋቡት አብሮ የሚያኖር ነው? እዛ ስብሰባ ላይ የተናገሩት እና መላ ካድሬዎች ትግሬ ለምን ንብረቱ ተቃጠለ፣ ለምን ተነካ ነው እንጅ አማራስ ለምን ይገደላል፤ ኦሮሞስ፣ ኮንሶስ፣ ጌዴዎስ ለምን ይገደላል አላሉም፡፡ እንዲህ አይነቱ ጭፍን ያለና ራስ ወዳድ ነገር ነው አብሮ የማያኗኑረው፡፡ አሁንም ይደገም፡- አንድስ እንኳ አማራና ሌሎች ለምን ተገደሉ የሚል አለመገኘቱ አንድ አገርነትን፣ አንድ ህዝብነትን ያመለክታል ወይ? አእምሮ ላለው እና በጥሞና ለሚያየው በጣም አሳዛኝ ነገር ነው፡፡ ለማጠቃለልም- ለወደፊቱ የአማራን እና የአማርኛ ተናጋሪን አጀንዳ ለይታችሁ ተንቀሳቀሱ፡፡ አማርኛ ተናጋሪው በሚያነሳው አጀንዳ ሁላ እየዘለላችሁ አማራ አትበሉ፡፡