
ነገር ግን ብዙም ትኩረት ያላገኘችው በአማራ ክልል በሰሜን ምስራቅ የምትገኘው ራያ-አላማጣ ተመሳሳይ አደጋ ላይ ከወደቀች ሰነባብታለች። አሁን ደግሞ ገበሬው ከመሬቱ እየተነቀለ በምትኩ ከሌላ አካባቢ ለመጡ ሰዎች በልማት ስም እየታደለ ነው። “ራያን በትግራይ ክልል የማካተት እቅድ አካል ነው” ያለኝ አንድ ወዳጄ “በግድ ትግሬ ናችሁ እያሉን ነው” በማለት ነበር ወቅታዊ ሁኔታውን በምሬት የገለፀው።
“ከጎንደር: ወልዲያ: ቆቦ: መርሳ፣ ከኦሮሚያ ክልል ሸሽተው የመጡ ትግሬዎች በራያ-አላማጣ ለማስፈር ገበሬው መሬቱን እየተነጠቀ ነው ያለው። አላማቸው መሬት መንጠቅ ብቻ ሳይሆን የማንነት ጥያቄ እንዳይነሳ በመፍራት የህዝቡ Demograpy መቀየርም ጭምር ነው። ልክ እንደ ወልቃይት ማለት ነው። እውነቴን ነው እምልህ እንደ ራያ ህዝብ ሚፈሩት የለም። ብዙ አክትቭስቶች ብዙ ይፅፉሉ ዋናው ወያኔ ጥያቄ እንዲነሳም ማይፈልጉት የራያ ጉዳይ ነው፣ ማንሳት ያለባቸውም ይሄው ነው።”

ጠቅላይ ምኒስትር አብይም እንዲህ ያሉ ጉዳዮችን ከማድበስበስ እና እውቅና ከመንሳት ተቆጥበው በድፍረት ቁርጠኛ አቋም በመያዝ ዘላቂ መፍትሄ እንዲመጣ ቢጥሩ ነው የሚሻላቸው። ያ ካልሆነ ምናልባትም የመርፌ ቀዳዳ የምታህል እድላቸውን በዚህ መሰል ጉዳዮች ሊያጡ እንደሚችሉ መገንዘብ የሚከብድ አይሆንም!
(ፎቶው በራያ አላማጣ ገበሬዎች መሬታቸውን ማረስ እንደማይችሉና ከመሬታቸው እንደተነቀሉ የሚያረዳ ደብዳቤ ነው)