>

"የበላይ" የሚባለው ስውሩ መንግስት የዜጎችን በነፃነት የመንቀሳቀስ መብት እያገደ ነው!?!

እስክንድርን አሁን በስልክ አግኝቼው ሁኔታውን እንዲህ ገልፆልኛል፦
ናፍቆት እስክንድር (ሰርካለም ፋሲል የእስክንድር ባለቤት)
 “ዕቃዬን አስገባኹ። ቦርዲንግ ፖስ ካላፈ በኅላ ኢምግሬሽን ለማለፍ ስሄድ፣ አንዲት ሴት ፖስፖርቴን ተቀብላኝ ወደ ቢሮ ገባች።  ለብቻህ ተቀመጥ አሉኝ።
ፖስፖርቴን ሲነጥቁኝ “ይሄ ነገር እታች ያላችሁ ወስናችሁ ከሆነ መንግስት ላይ ከፍተኛ ጭቅጭቅ ስለሚፈጥር የበላይ ጠይቃችሁ ተመለሱ አልኳቸው”
እነሱም “የበላይ ትዕዛዝ ነው” አሉኝ
“እርግጠኛ ናችሁ?” ስል ደግሜ ጠየኳቸው…
” እርግጠኛ ነን የበላይ ትዕዛዝ ነው” አሉኝ በድጋሚ
ግማሽ ሰዓት ያህል ከጠበኩ በኅላ አንድ ሰው መጥቶ ኢምግሬሽን ዋናው ቢሮ ሄደህ ማናገር ትችላለህ ተብዬ  ፖስፓርቴን ቀምተው መልሰውኛል “

#ፍትህ ለእስክንድር ነጋ

እንደ ትህነግ/ህወሓት ያለ ደንቆር ቡድን በዓለም ተፈልጎ አይገኝም!

ጌታቸው ሽፈራው

~የአሜሪካ ኮንግረንስ “ይለወጡ ይሆን” እያለ በሚጠራጠርበት ወቅት የዜጎችን በነፃነት የመንቀሳቀስ ሕገ መንግስታዊ መብት በይፋ፣ ያውም ስሙ በዓለም በገነነ ሰው ላይ ጥሶታል!
~እስክንድር የሚሄደው  የአምነስቲ ምስረታ በዓል ላይ ለመገኘት ነው። በዚህ በዓል በርካታ የመብት ተሟጋች ግለሰቦች፣ ሚዲያዎችና የሌሎች የሰብአዊ መብት ተቋማት ወኪሎች ይገኛሉ። የ”ኢትዮጵያ መንግስት የዜጎችን በነፃነት የመንቀሳቀስ መብት አሁንም እያገደ ነው” ተብሎ በቋሚ ምሳሌነት የሚነሳበት በዚህ መድረክ ነው!
~እስክንድር በዛ መድረክ መገኘቱ በራሱ ገዥዎችን ያበሽቅ ይሆናል። እስክንድር  ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ኢትዮጵያ ውስጥ ስለሚፈፀመው በደል መግለፁ አይቀርም ነበር። ይሁንና  እስክንድርን ያህል ሰው በነፃነት የመንቀሳቀስ ሕገ መንግስታዊ መብቱን መነጠቁ የአምነስቲን በዓል የሚያከብሩት ታዳሚዎች ኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈፀመውን የመብት  ጥሰት ተጨባጭነት  እስክንድር ተገኝቶ ከሚገልፀው በላይ እንዲረዱ የሚያደርግ ነው!
 ገዥዎቹ ለእስክንድር ባላቸው ጥላቻ ሲመልሱት ይህን ሁሉ አያስቡትም!  የዱር እንሰሳት  እንኳ በወራት ውስጥ ሰው የሚሰራውን  ይላመዳሉ። እነዚህ ጉዶች  የሰው ልጅ ሊተገብር የሚገባውን 27 አመት ለመልመድ አልቻሉም!
Filed in: Amharic