>
5:33 pm - Sunday December 5, 4184

ፍትህ ለካፒቴን በሃይሉ ገብሬ (ቴዎድሮስ አስፋው አለም)

የ1997 ዓ.ም ምርጫን ተከትሎ የአየር ሃይል አዛዥ የነበረው ጀነራል ሞላ ሃይለማርያም የድሬዳዋን የአየር ምድብ ፓይለቶች ህዝቡን ለማስጨፍጨፍ በተጠንቀቅ እንዲቆሙ አዘዘ። ነገር ግን ካፒቴን በሃይሉ ገብሬ ህዝቤን አልጨፈጭፍም በማለት ብቻ ከጓደኛው ከመቶ አለቃ አብዮት ማንጉዳይ ጋር በመሆን MI-35 ተዋጊ ሄሊኮፕተር ከድሬደዋ አስነስተው ጅቡቲ አረፉ።
***
በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በኃይል የተጫነው አገዛዝ ከጂቡቲ መንግስት ጋር በመነጋገር ሁለቱም በጅቡቲ ለተወሰነ ቀናቶች እንዲታሰሩ ካደረገ በኀላ ተላልፈው እንዲሰጡት በማድረግ ካፒቴን በሃይሉ ገብሬ ላይ በወታደራዊ ፍ/ቤት የእድሜ ልክ እስራት በመፍረድ በዝዋይ እስር ቤት እስካሁን እያሰቃየው ይገኛል። መቶ አለቃ አብዮት ማንጉዳይ ግን 10 አመታትን በስቃይ አሳልፎ ከአንድ አመት በፊት ተፈትቷል።
***
ይህ በምስሉ ላይ የምታዩት ካፒቴን በሃይሉ ገብሬ አሁንም በዝዋይ በስቃይ ጨለማ ቤት ይገኛል። በድብደባ ብዛት ወገቡ ተጎድቷል። በአጠቃላይ የጤና እክል ገጥሞታል።
***
ህዝብን አልጨፈጭፍም በማለቱ ብቻ የሰማዩ ጀግና በእስር ቤት እየማቀቀ ነው።
ፍትህ ለካፒቴን በሃይሉ ገብሬ!
Filed in: Amharic