>

ሰበር ይቅርታ!!!ለካንስ ዛሬ የፕሮፌሰር መስፍን 88ኛ ዓመት የልደት ቀን ነው።...አለምነህ ዋሴ (አዋዜ)

ሰበር ይቅርታ!!!ለካንስ ዛሬ የፕሮፌሰር መስፍን 88ኛ ዓመት የልደት ቀን ነው።እንኲን ለዙህ አበቃዎ!!!መልካም ልደት!!

አለምነህ ዋሴ (አዋዜ)
ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም  –የኢትዮጵያ ህሊና–ለወጣቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ይሁንታ ሰጥተዋል።”ሰው ነው፤አረመኔ አይደለም “ሲሉ የሰብዕናውን ጨዋነት አድንቀዋል።እንዳሰበው ይሰራ፣ ይራመድ ዘንድም በትዕግስት የ6ወር ጊዜ ልንሰጠው እንደሚገባ አጥብቀው ይመክራሉ።ሙክታሮቪች የተባሉ አንድ የፌስቡክ አምደኛ በትክክል እንደጠየቁት እኚህን የሀገር መምህርና ተጋፋጭ ምሁር ኢትዮጵያ የክብር ሜዳልያ ታጠልቅላቸው ዘንድ ጊዜው አሁን ነው።የኔታ መስፍን ኩሩውን፣ቀብራራውንና አኩሪውን ስድስት ኪሎ ዩኒቨርስቲን ወደደኛ ብዙሀን ህዝቦች ዘንድ በራችን ድረስ አምጥተውልናል፤አደባባያችን መሀል ተክለውታል።ከእሳቸው ብዕርና ሰብዕና ተምረናል፤በገባንም ባልገባንም ነገርና ጉዳይ ሁሉ የወደድናቸውን ያህል ሰድበናቸዋል!አዋርደናቸዋል።ጎፈሬው መስፍን ተፋልሟል እንጂ እንደሌሎች ግብዞች “ምነው ከዚህ ሁሉ  በደረጃዬ !”ብሎአልተሰቀለም።አልራቀም!በእንግሊዝኛ አልፃፈም።መስፍን ከኛ መሀል አልጠፋም።ሊያስተምረን ብቻ ሳይሆን መስፍን ስለሚወደንም ነው።ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በቤተ-መንግስታቸው ለብቻው ሊያገኙትና ምክሩን ሊያዳምጡት የሚገባ “የኢትዮጵያ ህሊና “ነው መስፍን!!!የሀገሪቱ ከፍተኛ ደረጃ ዕውቅናና ሽልማት ይገባዋል።የማይነጥፍ ብዕር፣የማትዘናጋ ህሊናና የእናትና የሀገር ፍቅር እሱ ዘንድ ናት።ረጅም ዕድሜ ለፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም!!
Filed in: Amharic