>

"ኪሳራ ላይ ነን" እያለ ለ20 አመታት ወርቅ ሲያግዝ የኖረው ሜድሮክ ለቀጣይ 10 ዓመት ውሉን አደሰ!?! (ዘውዱ ታደሰ)

 
በሚድሮክ ስር የሚተዳደረው በሻኪሶ ለገደንቢ እሚገኘው ከ20 ዓመት በፊት  በሼህ-አላሙዲን ቁጥጥር ስር የነበረው
የወርቅ ማውጫ ከወራት በፊት ኮንትራቱ እንዳለቀ እና የአካባቢው ነዋሪዎች በOBN ኦሮምኛ ፕሮግራም ተጠይቀው ለ20 ዓመታት በሙሉ ለአካባቢው ማህበረሰብ ምንም ሳይሰራና ሳይጠቅማቸው የኖረ በመሆኑ ይበልጥ ወርቁን ለማውጣት ድርጅቱ በሚጠቀመው ኬሚካል ህብረተሰብ እየተጎዳ እንደሆነ ገልፀው ነበር ።
ነዋሪዎቹም ድርጅቱን መንግስት ወስዶት የአካባቢው ህብረተሰብ ተጠቃሚ እንዲሆን ጠይቀው ነበር ከዚህም ጋር ተያይዞ የክልሉ ስራ ሀላፊዎች ተጠይቀው ድርጅቱ ኮንትራቱን ጨርሳል ለቆ ይወጣል ብለው ነበር ። ሆኖም ለህዝብ በሚዲያ ቃል የተገባው እና በተግባር የሆነው ለየቅል ነው።
የሚድሮክ ሀላፊዎችም በጉዳዩ ዙሪያ በሰአቱ ሲጠየቁ  ለ20 ዓመታት ከትርፍ ይልቅ በኪሳራ ሲሰሩ እንደኖሩ ገልፀዋል ህዝቡ እያለ ያለው እና በመሬት ላይ ያለው እውነት ይለያያል ነበር ያለው የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ  ። ወርቅ እያመረቱ ትርፍ ከሌለ ለምን ድርጅቱ ቦታውን ለቆ ሳይወጣ ቆየ ? አሁን ደግሞ ኮንትራቱን ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ ለ10 ዓመት ሚድሮክ የወርቅ ቁፍሮውን እንዲያካሂድ ዛሬ ውል ታድሶለታል የሀገሪቱን 63 ከመቶ ወርቅ እሚያቀርበው ይህ ድርጅት ነው፡፡
Filed in: Amharic