>

የፓዊ ልዩ ወረዳ አስተዳደር ፤መንደር 127 እና መተከል (ሚኪ አምሀራ)

ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተፈናቅለዉ ባህርዳር የመጡ አማሮች አሳዛኝ ነዉ፡፡ ከአባቶቻቸዉ መሬት ላይ መፈናቀላቸዉ ደግሞ ቁስሉን ያብሰዋል፡፡ የተፈናቀሉት ሰወች የክልሉ መንግስት መኪና አዘጋጅቶ የዉሎ አበል ከፍሎ እንዲሁም የሚቋቋሙበትን መንገድ መክሮ ወደ ነበሩበት መመለስ አለበት፡፡ አንዳችም ሰዉ ከነበረበት ቀየ ዉጪ ሌላ ቦታ ሊሄድና ኑሮ ሊጀምር አይችልም፡፡ ይሄን ካልኩ በኋላ እስኪ የቢንሻንጉል አካባቢ በተለይም በመተከል (በቀድሞዉ የጎጃም ክፍለ ሃገር) አካባቢ ያለዉን ነገር እንየዉ ምናልባትም ለዚህ ችግር ዋና መፍትሄ የሚሆነዉ ችግሩን ከስሩ በማየት ይመስለኛል፡፡
 የፓዊ ልዩ ወረዳ አስተዳደር
መተከልና አካባቢዉ 80 ፐርሰንቱ ነዋሪዉ አማራ ነዉ፡፡ 95 ፐረስንቱ ነዋሪ ደግሞ አማረኛ ተናጋሪ ነዉ፡፡ ይህ ባለበት ሁኔታ በምን መስፈርት ወደ ቤንሻንጉል እንደተካለለ ጌታ እና ህወሃት ብቻ ነዉ የሚያዉቁት፡፡ እሰከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የፓዊ አካባቢ በልዩ ወረዳነት ነበር የሚተዳደረዉ፡፡ ምክንያቱም እዛ አካባቢ አብዛኛዉ አማራ ስለሆነ በራሱ በአማራ ልጆች ይተዳደር በቤንሻንጉል ክልል ዉስጥም ቢሆን ተብሎ ልዩ አስተዳደር ሆኖ ፓዊ ዋና መቀመጫዉ ነበር፡፡ የፓዊ መስመር የንግድ ቀጠና የነበረ ሲሆን አካባበዉም ሰፊ እርሻ ያለዉና እና አምራች ነዉ፡፡ በዚህም ምክንያት ፓዊ ትልቅ እና እያደገ ያለ ከተማ ነበር፡፡ የልዩ አስተዳደሩ ሃላፊ የነበረዉ የጎንደር ልጅ ጋሻዉ የሚባል ሲሆን ጠንካራና በተለየም እዛ አካባቢ የሚኖረዉን አማራ በማደራጀት ጠንካራ ህብረት እንዲፈጥር በማድረግ ምንም አይነት ጥቃት እንዳይደርስበት አድርጓል፡፡ ከዚህም ባለፈ ጠንካራ የማህበረስብ ትስስር በመፍጠር እርስ በእርሱ እንዲረዳዱ፤ እንዲደጋገፉና ኑሯቸዉን እንዲለዉጡ በማድረግ ብዙ ሚና ተጫዉቷል፡፡
አዝመራዉ የልዩ ወረዳዉ አስተዳዳሪ
ባጋጣሚ ጋሻዉ የሚበላዉ አስተዳዳሪ ታሞ በመሞቱ ለልዩ ወረዳዉ አዝመራዉ የተባለ ሌላ አስተዳዳሪ ይመጣለታል፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ነዉ መበላሸት የጀመረዉ፡፡ አማራዉ ጠንካራ ትስስር በመስራቱና አይነኬ በመሆኑ በአዲሱ አስተዳደር መሬቱ ይፈለጋል እየተባለ ግማሹን ወደ አንድ አካባቢ ሌላዉን ወደ ሌላኛዉ አካባቢ በማስፈር የነበረዉን ትስስርና መረዳዳት በጣጠሱት፡፡ መንደር 1 መንደር 2 እያሉ ቁጥር በመስጠት አንድ አካባቢ የነበረዉን ማህበረሰብ በመነጣጠልና ከሌላ አካባቢ የነበረ በማምጣት በማይተዋወቁበት ሁኔታ አሰፈራቸዉ፡፡ አዝመራዉ እራሱ አማራ ነዉ ነገር ግን ከህወሃትኢንቨስተሮችና ከቤንሻንጉል ክልል አመራሮች ጋር በመሆን መሬት በመሸጥ የራሱን ወገን መሬት በመቀማትና ለህወሃት ሰወች በማደል እሱ እራሱን በሃበት አካበተበት፡፡ ህዝቡ ይሄን ሲያይ ከፍተኛ ተቃዉሞ በማሰማቱ አዝመራዉ የያዘዉን የሙስና ገንዘብ ይዞ ባህርዳር ጂ+ ቤትና ሆቶል በመገንባት ኑሮዉን አሁን እዛ ይኖራል፡፡ በጣም የሚያሳዝነዉ አንዷ ትልቋ የአዝመራዉ ልጅ human trafficker (ህጻናትን መሸጥ) ቢዝነስ ላይ በመግባት ብዙ ገንዘብ አካብታለች፡፡ ህጻናቶች የሚመለመሉት ፓዊ አካባቢ ነዉ፡፡ ለጾታዊ ግንኙነት ያልደረሱ እና ልጃገረዶችን በመመልመል ወደ አዲስ አበባ ትወስዳለች፡፡ አዲስ አበባ ካዛንችስ አካባቢ ባለ ሄቴል ለዲያስፖራ ጨረታ ታቀርባቸዋለች፡፡ ነብሱን የማያዉቅ sadist ዲያስፖራ እስከ 10 ሺህ ብር በመክፈል ከእነዚህ የ 14 እና የ15 አመት ልጃገረዶች ጋር ይተኛል፡፡ ለማንኛዉም አዝመራዉ እና ልጆቹ በሚሊየን የሚቆጠር አማራ ላይ እንዲህ ተጫዉተዋል፡፡ እነሱ ግን ተንደላቀዉ እየኖሩ ነዉ፡፡
የፓዊ ዋና ከተማነት መቀየር
አዝመራዉ የተባለ አስተዳዳሪ ሌላ ያደረገዉ ነገር ቢኖር ልዩ ወረዳ/ አስተዳደሩን ከህወሃት ጋር ሁኖ ሙሉ ለሙሉ አፈረሰዉ፡፡ ባካባቢዉ ይሄ ነዉ የሚባል የጉሙዝ ወይም ሽናሻ ማህበረሰብ በሌለበት ሁኔታ ከሌላ ቦታ በማምጣት የፖሊስ፤ የአስተዳደሩና ሌሎች ስልጣኖችን በሙሉ አማራዉን እያባረሩ በክልሉ መንግስት ድጋፍ ያዙት፡፡ ይሄም ሆኖ ፓዊ ከተማ በጣም ትልቅ የንግድ እንቅስቃሴ የነበረበትና ብዙ አማራ እራሱን ሰርቶ የለወጠበት ከ99 በመቶ በላይ የከተማዉ ነዋሪ አማራ በመሆኑ ከተማዉ በክልሉ መንግስት አልተወደደም፡፡ ከተማዉ ወደ ሌላ መቀየር አለበት ተባለ፡፡ ብዙ አማራ የሌለበት በጣም ሞቃታማና ለኑሮ የማይመች ትንሽየ ከተማ ግልገል በለስ ተመረጠች፡፡ግልገል በለስ የተወሰኑ ጉሙዞች የሚኖሩበት አካባቢ ነዉ፡፡ ለዚህም ነበር የመተከል ዞንን ከተማነት ከፓዊ ወደ ግልገል በለስ ያዞሩት፡፡ ዛሬ አማራዉ እዚህ አካባቢ ኢንቨስት አያደርግም ምክንያቱም ደህንነት የለዉም፡፡ ፓዊ ግን ሙሉ ለሙሉ አማራ ስለሆነ የዚህ ችግር አልነበረም፡፡ ከዛም ባለፈ ፓዊ ከላይ ከቋራ ጋር እንዲሁም ከጎን ከጃዊ ጋር በአጭር እርቀት የሚገናኝ ስለሆነ ሙሉ ለሙሉ አማራ ነዉ፡፡ ለባህርዳር እራሱ በጃዊ በኩል በጣም ቅርብ ነዉ፡፡ ሆን ተብሎ ግን መንገድ አልተሰራለትም፡፡
የጃዊ ስኳርና የፓዊ አካባቢ አማራ መፈናቀል
ጃዊ አካባቢ እየተሰራ ላለዉ የስኳር ልማት መሬቱ ይፈለጋል በመባሉ ፓዊ አካባቢ የሚኖዉን አማራ ሩቅ ቦታ በመዉሰድ ለቤት መስሪያ እና በጣም ትንሽየ የእርሻ መሬት በመስጠት ወደ ድህነት አዘቅት ብዙዉ ሰዉ ገብቷል፡፡ ለምሳሌ 3 ሄክታር ያርስ የነበረ አማራ ከተፈናቀለ በኋላ የተሰጠዉ ግማሽ ሄክታር ነበር፡፡ እሱ ብቻ አይደለም፡፡ እንዲሰፍሩ የተደረጉበት አካባቢ እና ለእርሻ የተሰጣቸዉ አካባቢ ከ 3 እስከ 4 ሰአት የእግር መንገድ ይወስዳል፡፡ ሆን ተብሎ ሄደዉ ማረስ እዳይችሉ እና አካባቢዉን ለቀዉ እነዲወጡ ነበር፡፡ መሬታቸዉ የተሰጠዉ ለትግሬ ባለ ሃብት ነዉ፡፡ በስህተት ከነዚህ የትግሬ ባለሃበት መሬት ከብት ከገባ በአንድ ከብት 100 ብር ገበሬዉን ያስክፍሉ ነበር፡፡
መንደር 127 
ይህች መንደር ትግሬወች መተዉ የሰፈሩባት መንደር ናት፡፡ በጃዊ እርሻ ምክንያት በመቶሸህ የሚቆጠር አማራ ሲፈናቀል የህችን መንደር ጫፏ ሳይነካ እዛዉ እርሻቸዉ ላይ እንዲኖሩ ተደርጓል፡፡ ባካባቢዉ መብራት ለመጀመሪያ ጊዜ የገባላት ይህች መንደር ናት፡፡ ለመንደር 127 መብራት ከገባ ከ 3 አመት በኋላ ነዉ ሌላዉ ሰዉ እኛስ እያለ ሲያማርር የገባላቸዉ፡፡ የተደረገዉ ይሄዉ ነዉ፡፡የህወሃት ተግባርም ይሄዉ ነዉ፡፡ በየሄድንበት በየምንኖርበት እየተከተለ ሰይጣናዊ ስራ መስራት ነዉ፡፡
መፍትሄ 
ለጊዜዉ የነበረዉን የልዩ ወረዳነት አስተዳደር መመለስና ህዝቡ የመረጠዉን አስተዳደር እንዲመሰረት፡፡ ያለ አግባብ ከእርሻቸዉ የተፈናቀሉት ገበሬወች ተገቢዉን ካሳ ተከፍሎ በዛዉም ልክ ተቀያሪ መሬት በሚኖሩበት አካባቢ እንዲሰጥ፡፡ ማንጎ እና ሌሎች ተክሎች የወደመባቸዉ ገበሬወች ተገቢዉን ካሳ  እንዲከፈላቸዉ፡፡ ፓዊ ከተማ የንግድ መአከል ሆና እንድትቀጥል አስፈላጊዉን መሰረተ ልማት መዘርጋት፡፡ ከባህርዳር በጃዊ አድርጎ ፓዊ የሚደርሰዉን መንገድ በአስፓልት እንዲሰራ፡፡ ከፓዊ በቋራ አድርጎ ጎንደር መንገድ እንዲሰራለት፡፡ ጥፋት ያጠፉ አመራሮች አንዲጠየቁ፡፡ አመራሮቹ እነ አዝመራዉና በህገወጥ የሰዉ ንግድ ዉስጥ ያሉ ልጆቹ እዛዉ ብአዴን አፍንጫ ስር ስላሉ ተይዘዉ እንዲጠየቁ፡፡ በመጨረሻም የመተከል ዞንን ወደ አማራ ክልል በመመለስ በዉስጡ ትቂት የጉሙዝ የኦሮሞና ሌሎች ብሄሮች ቋንቋቸዉ፤ባህላቸዉና ማንነታቸዉ ተከብሮ በአማራ ክልል ዉስጥ መኖር እንዲችሉ ማመቻቸት፡፡
CC// ANDM CC office ANRS Communication Affairs Office Bahirdar city Communication
Filed in: Amharic