>

ሌላ ድል በሌላ ግንባር (ታዬ ደንደአ)

የኦሮሚያ ፍትህ ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊው አቶ ታዬ ደንደአ በገለጹልን መሰረት ኮማንድ ፖስቱ በኦሮሚያ ክልል ያለ ሕግ ያሰራቸውን በርካታ ንጹሃን ዜጎቻችንን ጉዳይ ለኦሮሚያ ክልል ማስረከቡንና የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነርና ፍትህ ቢሮ ተወያይተው የወገኖቻችንን ጉዳይ ወደ ማጣራት ገብተዋል። በዚሁ መሰረት ኮማንዱ ፖስቱ ጨርቁን ጠቅልሎ የሚወጣበት መስመር ላይ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል። የኦሮሚያ ተመሳሳይ ተግባር በሌሎቹም ክልሎች በተለይም ከኦሮሚያ ቀጥሎ በርካቶች በኮማንዱ ፖስቱ የታሰሩበት የአማራ ክልልም የወገኖቻችንን ጉዳይ በኣስቸኳይ ወደ መፍታቱ ኣንደሚንቀሳቀስ ይጠበቃል።  ኢትዮጵያዊያን ከዶ/ር አቢይ ጋር መተባበራችንን ያየ ማንኛውም አምባገነን ሃይል የሚያደርጋቸው ትናንሽ ሙከራዎች ሁሉ እንደሚከሽፉ እያየን እንገኛለን። ስለሆነም በዶ/ር አቢይ አመራር ሃገራችን የተለያዩ አመለካከቶችን ማስተናገድ ወደምትችልበትና ተቋማትን ገንብተን የሕግ የበላይነትን የምናስከብርበት ደረጃ እስኪትደርስ ሕዝባዊ ትግላችን መቀጣጠል ይኖርበታል። በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያዊያን ዶክተር አቢይ ቃል የገቡትን በሙሉ ኣንዳች ሳትሸራረፍ መሬት ላይ እንድትወርድ ከጠቅላያችን ጎን ሳንለይ በመተጋገዝና በመረዳዳት በኢትዮጵያዊ ኣንድነት እየታገሉ ይገኛሉ።
በሱዳን እስር ቤቶች ሲማቅቁ የነበሩ ኢትዮጵያዊያን የህሊና እስረኞች በሙሉ እንደሚፈቱም ለማወቅ ችለናል።
ትዕግስት በማጣት የወያኔዎች መጠቀሚያ እንዳንሆን ኣጽኖት ሰጥተን ልናስገነዝብ ኣንወዳለን።
Taye Dendea
Oduu Simbirtuu
Labsii muddamaa keessatti namooti  koomaandpoostiin qabaman jiraatuun ni beekkama. Abbaan alangaa federaalaa dhimmi namoota kanaa naannoo isaaniitti akka furamu murteessee jira. Haaluma kanaan Biiroon Haqaa Oromiyaa  Koomishiinii Poolisii fi Bulchiinsaf Nageenya Oromiyaa waliin dhimma namoota Oromiyaa irraa qabamanii yeroo gabaabaa keessatti laalee furmaata kennuuf hojii eegalee jira.
Horaa bulaa!
Filed in: Amharic