>

ኢህአዴግ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ብአዴንና ሌሎችም (ሚኪ አምሀራ)

ኢህአዴግ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ብአዴንና ሌሎችም (non-partisan political analysis)

ኢህአዴግ
ኢህአዴግ እንደ ድርጅት ከበፊቱ የተወሰነ መረጋጋት ቢያሳይም በግለሰብ ደረጃ ግን እስካሁን ድረስ ለመነጋገርና ስልክ ለመደዋወል እንኳን ያልቻሉ የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች አሉ፡፡ ኩርፊያዉ ገና በደንብ አልቀዘቀዘም፡፡ እንደ ድርጅት የወደፊቱን አቅጣጫ እና ምናልባትም በመጣበት ርእዮተ አለም ይቀጥላል ወይስ የተወሰነ እራሱን እያላመደ የመቀየር አላማ አለዉ የሚለዉ በደንብ አለየም፡፡ የኢህአዴግ ጽ/ቤት አላፊ ተደርጋ የተሾመችዉ ሴትዮ ምናልባትም የምትታወቀዉ ሰወችን በመገምገምና ሴራ በመሸረብ ነዉ፡፡ የድርጅቱን ፖሊሲና ርዮተ አለም ግን በሚገባ የመተንተን፤አካዳሚያዊ እና ፖለቲካዊ ቅርጽ የማስያዝ አቅሙ ያላት አይመስልም፡፡ በዚህ ላይ የጠሚ አብይ ንግግሮች ባብዛኛዉ ከኢህአዴግ የፖሊሲ አካሄድ ሊጻረሩ የሚችሉ ናቸዉ፡፡ አሮጌወቹ ከድርጅቱ በደንብ ከተገለሉለት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የድርጅቱን አቅጣጫ በሚፈልገዉ መንገድ የመቅረጽና ድርጅቱን own የማድረግ እድል አለዉ፡፡
ኦህዴድ
ኦህዴድ ከጠቅላይ ሚኒስትር ምርጫ በኋላ እፎይታ የተሰማዉ ቢሆንም ገና ያላለቁ ነገርች እንዳሉና ከፍርሃት ቆፈን ያልወጣ መሆኑን አሁንም ያሳብቅበታል፡፡ ገፍቶ ሄዶ ወታደሩን እንዲያርፍ የማድረግ፤ በክልሉ ወጣቶች ላይ ያለዉ ተጽእኖ እና ህወሃት ጠቅላይ ሚኒስትር እያለ ልክ በኢህአዴግ ላይ የነበረዉን አይነት power  ገና አላገኘም፡፡ ኦህዴድ ፍሬሽ አገረ ገዥ መሆኑ የታየበት ክስተትም ሰሞኑን ነበር፡፡ የክልሉን ፕሬዝደንት፤ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብረዉ ተያይዘዉ ለጉብኝት ወደ ኬንያ መሄዳቸዉ ነዉ፡፡ ክልሉ ላይ ተቃዉሞ እያለ፤ ህወሃት እየዶለተ ባለበት ሁኔታ፤ ወታደሩ ችግር እያደረሰ፤ አብዲ ኤሊም ባላረፈበት ሁኔታ ሶስቱም የኦህዴድ ቁንጮወች ባድማዉን ለአባዱላ አምነዉ ጥሎ መሄድ ፍሬሽነታቸዉን ያሳያል፡፡የለማ ምክትልም አዲስና ወጣት ከመሆኗ አንጻር ያን ያህል ተጽእኖ አይኖራትም፡፡ ኦህዴድ ምናልባትም ነጻነት ተሰምቶት ያደረገዉ ነገር ቢኖር የክልሉን ካቢኔ ያዋቀረበት ጉዳይ ነዉ፡፡ ወጣት እና የተማሩ ወደ ስልጣን አምጥቷል፡፡ በፌደራል ደረጃ ጥሩ ልምድ ያካበተዉ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ለኮሙኒኬሽንነቱ አያንስም፡፡ ፌደራል ላይ ሰነፍ መስሎ እንዲታይ ያደረገዉ ህወሃቶች ሆን ብለዉ በተደጋጋሚ ሲያሳስቱት ስለነበር ነዉ፡፡ እንዲያዉም በፌደራል ደረጃ ሁኖ ብሎት የማያዉቀዉን ትናንት በሞያሌ በህዝብ ላይ የደረሰዉ ጭፍጨፋ ተቀባይነት የለዉም ብሏል፡፡ ይህ የሚያሳያዉ ህወሃት ከጎንህ ሲኖር ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ነዉ፡፡ ምናልባት በክለሉ ዉስጥ የሚከናወኑ ነገሮችን አዲሱ አረጋ በፍጥነት በሶሻል ሚዲያዉ የሚያደርሰንን ያህል ላያደርሰን ይችላል፡፡ ከዛ ዉጪ ግን ለቦታዉ አያንስም፡፡ አዲሱ አረጋ ወደ ገጠር ፖለቲካ ዘርፍ መዞሩ ኦህዴድ አሁን የያዘዉን የኦሮሞ ፖለቲካ አካሄድ ከከተማ ወደ ገጠሩ ለማስረጥ የፈለገ ይመስላል፡፡ አብዛኛዉ የኦሮሞ ህዝብ በገጠሩ ክፍል እንደመኖሩ መጠን እና ኦነግ ደግሞ ገጠሩ ላይ ለብዙ ጊዚያት ስለቆየ የኦሮሚያ ገበሬ አሁን ባለዉ የፖለቲካ ትርክት እና አደረጃጀት ዉስጥ መካተት ይኖበታል፡፡ ከሁለት አመት ባልበለጠ ጊዜ ለሚካሄደዉ ምርጫም ኦህዴድ ቤዙን ገጠር ለማድረግ የፈለገ ይመስላል፡፡ በከተሞች አካባቢ እነ ኦፌኮ ኦህዴድን በቀላሉ የማሸነፍ እድል አላቸዉ ስለዚህም ኦህዴድ ከአሁኑ ገጠሩን ካላደራጀ በከተሞች አካባቢ ሊኖር የሚችለዉን ፉክክር ባላንስ ማድረግ አይችልም፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ
ጠሚ አብይ ከሞላ ጎደል በጉዞዎቹ እና በተጓዘበት አካባቢ ስለ ህዝቦች የመጨነቅ፤ ለህዝቡ ቅርብ ሆኖ የመታየት እና በቀላሉ ህዝቡ ሊረዳዉ በሚችለዉ ቋንቋ ማዉራቱ በራሱ በሰዉ ላይ የተወሰነ ነጻ የመሆን ሰሜት ፈጥሯል፡፡ 27 አመት ኒዮ-ሊበራሊዘም፤ቦነፓርቲዝም፤ Agricutlrue led industry, አቢዮታዊ ዲሞክራሲያዊ የመሳሰሉ የአካዳሚክስ ቃላቶች ለ85 በመቶ በገጠር ለሚኖርዉ ህዝብ ለከተሜዉም ቢሆን ምን ማለት እንደሆን ብዙዉ ሰዉ ግራ ሲጋባ መኖሩ የአብይ ቀላል ንግግር ለብዙዉ ሰዉ የተመቸዉ ይመስላል፡፡ ባብዛኛዉ አብይ ላይ እየተነሱ ያሉት ነገሮች የአስቸኳይ ጊዜዉን ለምን አያነሳም እና አስረኞችን ለምን አይፈታም ነዉ፡፡ አስቸኳይ ጊዜዉ ባይነሳም እየሰራ አይደለም፡፡ ተነሳም አልተነሳም አሁን ባለዉ ሁኔታ ለዉጥ ያለዉ አይመስለም፡፡ ሁለተኛዉ ህወሃት 27 አመት ተንደላቆ ሁሉንም ነገር እያዘዘ ነዉ የኖዉ፡፡ አሁን ህወሃት ገና ልምምድ ላይ ነዉ፡፡ ሳያዝ የመኖር፤ ለህዝብ የሚነገር ነገር ጽፎ ሳይሰጥ የመኖር፤ የሚካሄዱ ዉሳኔወችን ቀድሞ ሳይወስኑ የመኖር እና የመሳሰሉት በቀላሉ ሊለመዱ የማይችሉ ግን ቀስ በቀስ የሚለመዱ የህይወት መስመር ላይ ነዉ፡፡ ይሄን በአንዴ ከስልጣን ማማ ወርዶ እንደ አናሳ ፓርቲ ሆኖ ለመቀጠል እያሟሟቀ ያለን ፓርቲ ዶ/ር አብይ ሊጋፈጠዉ አልፈለገም፡፡ ቀስ ብሎ ለማለማመድ ነዉ እየሞከረ ያለዉ፡፡ ህወሃት አሁን እንደ ገጠር ሙሽራ አየተሸኮረመመ ነዉ ያለዉ፡፡ የሆነ ነገር ብትለዉ ወይ ያለቅሳል ወይ ጥሎ ይጠፋል፡፡ ስለዚህም አብይ ያን ያህል አንሱልኝ አታንሱልኝ የሚል ጭቅጭቅ ዉስጥ የገባ አይመስልም፡፡ አልሞከረም ማለት ግን አይቻልም፡፡ በዛ ላይ አብይ ወታደሩ ላይ እና ደህንነቱ ላይ ገና ተጽእኖ ማድረስ የሚችልበት ደረጃ ላይ አይደለም፡፡ በእርግጥ እየሞከረ ነዉ፡፡ እነ እስክንድርን እነ ሃጫሉን ደዉሎ አስለቅቋል፡፡ የዋልድባ መነኮሳትን እራሱ እንዳስፈታ ተናግሯል፡፡ እስረኞችንም በሚቀጥሉት ጊዚያቶች የሚያስፈታ ይመስላል፡፡ ሌላ አገር እየዞርኩ እያስፈታሁ አገር ዉስጥ ያሉት የማይፈቱበት ምክንያት የለም የሚል ቀላል መከራከሪያ ያቀርባል፡፡ ብአዴንና ኦህዴድም እንዲፈቱ የሚፈልጓቸዉ እስረኞች ስላሉ ይደግፉታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ዶ/ር አብይ የፈለገዉን ነገር እንዲያደርግ ከፈለገ ኢህአዴግን ሙሉ ለሙሉ እንነደመለስ የኔ ነዉ ብሎ መጠቅለል አለበት፡፡ አምባገነናዊ ሆኖ ሳይሆን ቢያንስ ኢህአዴግን አላማዉን በመቅረጽ፤ አካሄዱን እሱ በሚፈልገዉ መስመር እንዲሆን በማድረግና በድርጅቱ ፓሊሲወችና የፖለቲካ አስተምህሮ expert በመሆን ድርጅቱን own ማድረግ ይችላል፡፡ አጋጣሚዉ ደግሞ ለሱ በጣም ጥሩ ነዉ፡፡ እሱን ሊቀናቀን የሚችል ወጣት የተማረ እና ሃሳቡን በሚገባ የሚገልጽ ከየትኛዉም ድርጅት አሁን የለም፡፡
ህወሃት
ህወሃት ህይወት አልለመዳት ብሎ እየተጨናነቀች ነዉ፡፡ ምን ማድረግ እንዳለባቸዉ ያን የህል የተስማሙ አይመስልም፡፡ ነገር ግን ላለመሸነፍ ያህል በዛም በዚህም የተንኮል ፖለቲካ የእራሱ አጋር ድርጅቶች ላይ እየሰራ እየሄደ ነዉ፡፡ ለምሳሌ ኦህዴድ ላይ ሞያሌ አካባቢ ችግር በመፍጠር እንቅልፍ ለመንሳት እየሞከረ ነዉ፡፡ ከዚህ በፊት ብአዴን ላይ ያን ያህል ተንኮልም ሆነ ግልጽ በሆነ መንገድ ሲቃወም አልታየም ነበር፡፡ ሰሞኑን ግን ብአዴን በአማራ ተቃዋሚዎች (እኔን ጨምሮ) ሲለበለብ ህወሃት ደስተኛ ነበር፡፡ ለምሳሌ ባለፈዉ ሳምንት በክልሉ በኩል በተካሄደዉ የትምህርት ቤት ጎደሎወችን የማጋለጥ ስራ ላይ ህወሃት ደስተኛ የነበረ መሆኑን በብዙ መልኩ ማሳየት ይቻላል፡፡ የህወሃት ደጋፊዎች እራሱ የአማራ ፖለቲከኞችን ከትምህርት ጋር በተያያዘ የወጡ ጹሁፎችን ያጋሩ ነበር፡፡ አብረዉ ብአዴንን ይወቅሱ ነበር፡፡ በትምህርት ቤት ዘመቻዉ ወቅት የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ወደ ትግራይ ሄዶ የቀላሚኖ ትምህርት ቤት ፋሲሊቲ፤ ተማሪዎች እንዴት በሚያምርና በተሟላ ትምህርት ቤት እንደሚማሩ እንዲሁም ትምህርት ቤቱ ለትግራይ ተማሪዎች ብቻ እንደሆነ ተማሪዎቹ እንዲናገሩ በማድረግ ሰፊ ዘገባ ይዞ ወቷል፡፡ ይህ ምናልባት ብአዴንን በደንብ ደብድቡት ብሎ ዱላ ማቀበል ይመስላል፡፡ በጠሚዉ ምርጫ ምክንያት ብአዴን ላይ ህወሀት እንዳኮረፈ ነዉ፡፡ ህወሃት ቀስ በቀስ ብአዴንና ኦህዴድ እንደኖሩት መኖር ትጀምራለች፡፡ የማይለመድ የለም፡፡ በሚቀጥሉት ስድት ወራት ግን ትግራይ ዉስጥ የተቃዉሞ ሰልፍ በርግጠኝነት ይኖራል፡፡ እሰለፋለዉ የሚል ከተገኘ ህወሃት ከኋላ ሁና የምትደግፍ ይሆናል፡፡ መቀሌ ላይ ዉሃ የለንም ወይም የኢትዮ-ኤርትራ ጉዳይ እልባት ያግኝ የምትል የፌደርል መንግስቱን (ኦህዴድን) አቴንሽን የምትስብ ሰልፍ ትኖራለች፡፡
ብአዴን
ከአራቱ የኢህአዴግ ፓርቲዎች ዉስጥ እስካሁን የከፋ ችግር ላይ ያለዉ ብአዴን ነዉ፡፡ በሁለት ቡድን መካከል ያለዉን ልዩነት ለማጥበብ በዚህ ወር ብቻ ለሶስተኛ ጊዜ ሲሰበሰቡ ነዉ፡፡ ግን እየሰፋ እንጅ እየጠበበ አልሄደም፡፡ በዚህ ሁለት ቀን ባደርጉት ስብሰባ ዛሬ ከሰአት ያልቃል ተብሎ ይጠበቃል እርስ በርስ ተገማግመዋል፡፡ በባለፈዉ ስብሰባ የጥረት ጉዳይ አጅግ አጨቃጫቂ የነበረበት ነዉ፡፡ ጥረትን የሚመራዉ ታደሰ ጥንቅሹ የአማራ ክልል አባይ ጸሃየ ማለት ነዉ፡፡ ከ 1ቢሊየን ብር በላይ የት እንዳስገባዉ አይታወቅም፡፡ ለወረቀት ፋብሪካ ተብሎ የፕሮጀክት ጥናት ተብሎ ከ 10 ሚሊየን ብር በላይ የት እንደገባ አይታወቅም፡፡ የአማራ የኮንስትራክሽን ካምፓኒ ተብሎ 600 ሚሊየን ብር ይዞ ካምፓኒዉ የት እንደገባ አይታወቅም፡፡ BDC የቤት ግንባታ፡፡ ጥረት ከያዘዉ ከ 15 በላይ የንግድ ድርጅቶች በትርፍ የሚንቀሳቀሱት ዳሽንና አምባሰል ብቻ ናቸዉ በተወሰነም የሞባይል መገጣጠሚያዉ ይሄም የሆነ ጊዜ ላይ በኪሳራ እየተንቀሳቀሰ ነበር፡፡ ሌሎች ድርጅቶች በዋነኛነት የሚደጎመዉ በሁለቱ ነዉ፡፡ ታደሰ ካሳ/ጥንቅሹ ይሄን ሁሉ ቢሊየን ብር የት እንዳደረሰዉ ሲጠየቅ መልስ የለዉም፡፡ የሱ ምክትል ምትኩ የሚባልም እንዲሁ በሰፊዉ ተገምግሟል፡፡ በመጀመሪያዉ ግምገማ (ከ2 ወይም 3 ሳምንት በፊት) ሳይስማሙ የወጡ ሲሆን አሁን በሁለተኛዉ ግን ሙሉ የኦዲት ሪፖርት ከተሰማ በኋላ ብአዴን ድንጋጤ ዉስጥ የገባ ሲሆን ሁለቱም የድርጅቱ ሃላፊዎች ወርደዉ በህግ እንዲጠየቁ የሚል ሃሳብ አቅርበዉ ነበር፡፡ ታደሰ በህግ መጠየቅ አይደለም ከስልጣኑም ለመዉረድ ብዙ ያንገራገረ ሲሆን የእነ በረከትን ድጋፍ በተወሰነ መንገድ አግኝቷል፡፡ ድጋፉ ግን ኢሚዩኒቲ እንዲያገኝ ነዉ (በህግ እንዳይጠየቅ ነዉ)፡፡ የታደሰ በህግ መጠየቅ ነገሩ ወደ በረከት ይደርሳል፡፡ በረከት እስከባለፈዉ አመት ድረስ የጥረት የቦርድ ሊቀመንበር ስለነበር፡፡ በመሆኑም የጥረትን ችግር ሊፈቱ ይችላሉ ያሏቸዉን ሰወች ከዩኒቨርስቲ አካባቢ በቦርዱ ዉስጥ አካትተዋል፡፡ ከባህርዳር ዩኒቨርስቲ፤ከጎንደር የኒቨረስቲ ፕሮፌሰሮችን አስገብተዋል፡፡በርግጥ ከባለፈዉ አመት ጀምረዉ ነዉ ቦርዱን በአዲስ መልክ የማወቀር ስራ የጀመሩት፡፡
ብአዴን እንደ ኦህዴድ አሮጌዉን ቡድን መንግሎ መጣል አልቻለም፡፡ ክፉኛ ቢገመግሟቸዉም ከድርጅቱ በቀላሉ ይወጣሉ ተብሎ አይታሰብም፡፡ ነገር ግን በዚህ ሰሞን በእነ በረከት እና አለምነዉ ቡድን ተግምግመዉ ከማእከላዊ ኮሚቴ እንዲባረሩ ተወስኖባቸዉ የነበሩ፤ ከስልጣን ገልል የተደረጉ ሰወች አሁን ተመልሰዉ ስልጣን ይዘዋል፡፡ ተደብቀዉ ከነበሩበት ትንንሽ ቢሮወች እየወጡ ወደ ፊት መተዋል፡፡ ለምሳሌ እነ አገኘዉ ተሻገር (ለማባረር ጥረት ተደርጎ ነበር በእነ አለምነዉ)፤ ጌታቸዉ ጀምበሬ (ሰሜን ጎንደር አመራር እያለ ምናልባትም ከ 7 ወይም 8 አመታት በፊት የወልቃይትን ጥያቄ ብአዴን ስብሰባ ላይ አንስቶ ተባሮ የነበር)፤ ዶ/ር አምባቸዉ (ሲያስቸግር ትምህርት ላኩት ከዛም ገምግመዉ የትምህርት አንከፍልም ብለዉ ተቸጋግሮ ትምህርቱን የጨረሰ)፤ እነዚህ እና የመሳሰሉት ተመልሰዋል፡፡ በአንጻሩ ካሳ ተክለብርሃንን፤ አለምነዉ መኮነን፤ ጌታቸዉ አምባየ፤ አሁን ታደስ ጥንቅሹ የሚባሉት ገሸሸ እየተደረጉ ነዉ፡፡ ሌሎች እነ ዝማምና ከበደ ጫኔን የመሳሰሉ እንዲህ በቀላሉ የሚወጡ አይደሉም፡፡
በነገራችን ላይ ዝማም የብአዴን ከፍተኛ አመራር ናት ገነት ገብረእግዛብሄርም እንዲሁ እነዚህ ሰወች ስማቸዉን በእንግሊዘኛ ሲጽፉ እራሱ ቫወልስ አይጠቀሙም፡፡ Zmmm; Gnt gbrgzbhr ብለዉ ነዉ የሚጽፉት፡፡ ከነዚህ ሰወች ጋር 3 ደቂቃ ካወራህ በኋላ የኦህዴዷ ደሚቱ አንስታይን ትሆንብሀለች፡፡ እነዚህ ሰወች የብአዴን ከፍተኛ አመራር የሆኑት በሴት በሚለዉ ነዉ፡፡ ነገር ግን ክልሉ ላይ እሳት የላሱ ሴቶች በመስሪያ ቤቶች፤ በዩኒቨርስቲዎች፤ በሆስፒታሎች ሞልተዋል፡፡ ችግሩ ብአዴን እንዲህ አይነት ነገር አይፈልግም፡፡ ለማንኛዉም በዚህ ስብሰባ ላይ እርስ በእርስ ሁሉም ስለተጨፋጨፉ ማን ምን አለ የሚለዉ በሌላ ጊዜ እመለስበታለዉ፡፡ ጌታቸዉ ጀምበሬና ተሰፋየ ጌታቸዉ ለብአዴን ጽ/ቤት ታጭተዉ ተስፋየን መርጠዋል፡፡ ተስፋየ በቅርብ የተሾመበትን የኢንደስትሪ ቢሮ ምናልባትም ለጌታቸዉ ይሰጡታል ተብሎ የጠበቃል፡፡
ብአዴን ብዙ ጊዜ የመስመር ጥራት ችግር አለብኝ እያለ ይሰበሰባል፡፡ በገሃድ መግለጽ ስላቃተዉ ወይም ደፋር ስለጠፋ ነዉ እንጂ፡፡ ብአዴን የብሄር ችግር ነዉ ያለበት፡፤ ለዛም ነዉ ችግሩን እንደኦህዴድ ወይም እንደ ህወሃት በአንድ እና ሁለት ስብሰባ መፍታት ያቃተዉ፡፡ ብአዴን ዉስጥ ትግሬ አለ፤ ኤርትራዊ አለ፤ ኦሮሞ አለ፤ ከምባታ አለ፤ሸክቾ አለ፤ሲዳማ አለ፤ሽናሻ አለ እንዲሁም ሌሎችም፡፡ በዚህም ምክንያት እንደ ኦህዴድ ወይም ህወሃት አንድ ቡድን በግልጽ አሸንፎ የመዉጣት እድሉ ዜሮ ነዉ፡፡ ለጊዜዉ ብቻ አንዱ አንዱን ገለል የማድረግ ሁኔታ ካልሆነ በቀር፡፡ በዚህ ስብሰባ ላይ የአማራ ብሄርተኝነትን አንዴት handle እናድርገዉ፤ ወልቃይት፡ እነ መላኩ ፈንታ ለምን አይፈቱም የሚሉ ሃሳቦች ተሰንዝረዋል፡፡ ብዙ ግለሳባዊ ትችቶችም ተሰንዝረዋል፡፡ ገነት ገብረእግዛብሄር የምትባል ሴትዮ መላኩ የሚፈታ ከሆነ ገብረዋሀድም አብሮ ይፈታ የሚል ሃሳብ አቅርባለች፡፡ እንግዲህ ብአዴን ዉስጥ ህወሃት ቁጭ ብሎ ይከራከራል ማለት ነዉ፡፡ በርግጥ የገብረዋህድ መታሰር በራሱ  Fair አይደለም፡፡ አባይ ጸሃየ 77 ቢሊየን ብር ጉዝጓዝ አድርጎ ተኝቶበት ገብረዋህድ 1 እና 2 ቢሊየን ብቻ ቢወስድ ነዉ፡፡
እነ በረከት ከቤተመንግስት አካባቢ መራቃቸዉ እና ጠሚዉ እነ ገዱን አይዟችሁ የሚላቸዉ ከሆነ ተጨማሪ ነባር አመራር ማራቅ ይችላሉ፡፡ ዞሮ ዞሮ ገዱ እራሱ ለብአዴን ችግር መልስ አይሆንም፡፡ ብአዴን ዉስጥ እንደ እነ አብይ እና ለማ በህይወቱ ቆርጦ የህወሃትን ደህንነት የፈለጉ ያድርጉኝ ብሎ ጠቅላይ ሁን ሲባል አይ በቃኝ የማይል ሀገር ለመምራት ህልም ያለዉ ወጣት ያስፈልጋል፡፡ የብሄር ዉጭጩ ግን ይሄን እንዲያደርግ የሚፈቅድለት አይመስልም፡፡
Filed in: Amharic