ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከእስር ቤት ከተፈታ በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ በትላንትናው ዕለት ግንቦት 2/2010 ዓ.ም በጎንደር ከተማ ያደረገው ንግግር)
ወልቃይትን እንደ ካሽሚር

በትግሉ ተዎፆም የሴቶች ተሳትፎ አናሳ በሆነበት አውድ የእነዚህ አናቶች እና ለዕድሜ አቻዎቿ ዓርአያ መሆን የቻለችው ንግስት ይርጋ ጀግንነትም ከፍ ያላ ዋጋ እንዳለው አይካድም።
ጎንደር ከመካከለኛው ዘመን የስልጣኔ እምብርትነት በዘለለ፣ የ21ኛው ክፍለ-ዘመን የፀረ-ጭቆና ብርሃን ፈልቃቂ ከተማ የመሆኗን ጉዳይ። ባለፉት ሁለት ዓመት ያየነው ሃቅ ይመሰክራል።
በዚህ አጀንዳ ላይ ያለኝን አጭር አስታየት ከማቅረቤ በፊት ከወልቃይት የማንነት ጥያቄ ጋር ተያይዞ በለፉት አርባ አመታት በግፈኛው ስርዓት ህይወታቸው ለለፈ ወገኖቻችን የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት እንድናደርግ በትህትና እጠይቃለሁ። …አመሰግናለሁ።
…የሆነ ሆኖ በሽፍታ-መራሹ ስብስብ የተጫረው “ወያኔያዊ አብዮት” ሁለት ግቦችን በአእምድነት የተሸከመ ሲሆን፤ በመጀመርያው ምዕራፍ ግዛት ማስፋፋትን ታሳቢ አድርጎ ባካሄደው ስር-ነቀል አብዮት የትግራይን ወሰን ተሻግሮ በጠብ-መንጃ ወርሮ በያዛቸው ግዛቶች ነባሩን ማሕበራዊ መዋቅር አፈራርሶ አዲስ ተክሏል ፤ የማሕበረ-ሰቡን ርዕዮተ-ዓለማዊ ምልከታንም በአይነቱ አዲስ በሆነ ገዥ-ሃሳብ ቀይሯል። ሌሎች ስር-ነቀል እርምጃዎችንም ወስዷል። እነሆም በዚህ መልኩ ወደ መሬት ያወረደውን ደም-ጠገብ ፖሊሲን ነው የ”ታሪክ ማስረጃ” እያለ ረብ-የለሽ ሙግት አንስቶ የሚያነታርከን።…
…ይህንን ጥያቄ ወደ አደባባይ ማምጣቱ የማሕበረሰብን ህልውና ያናጋል የሚለው ሙግትም ጊዜ ያለፈበት መድሀኒት ነው፤ የሚገድል እንጂ የማያሽር።…
(ሙሉውን ንግግር ነገ በምትወጣው ግዮን መፅሔት ላይ ያገኙታል)
ግንቦት 3/2010 ዓም