>
5:13 pm - Monday April 20, 3998

የአማራ ነፍስ ዋጋው ስንት ነው?!! (ኢ/ር ይልቃል ጌትነት)

ዳንጉቴ የተባለው የውጭ ሀገር የንግድ ድርጅት ስራ አስኪያጅ ባልታወቁ ሰወች ተገደለ ተብሎ የኢትዮጵያ ቴለቭዥን በሚባለው የአገዛዙ የፕሮፓጋንዳ ማሰራጫ ጣቢያ ኮማንድ ፖስቱ ገዳዮችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ጥብቅ ትዛዝ ማስተላለፉን ሰማሁ። እጅግ ልብ የሚሰብረውና እኛም መልመድ ያቃተን ነገር ቢኖር የዳንጎቴው ስራ አስኪያጅ ግድያ ያሳሰበው ኮማንድ ፖስትና ቴሌቪዥኑ ሰሞኑን በመተከል በታዳጊው ህፃን አበጥር ወርቁ ላይ የተፈፀመውን አረመኔያዊ ድርጊት በተመለከተ ምንም ለማለት አልፈለገም። ምክንያቱ ደግሞ በጣም ግልፅ ነው። አበጥር ወርቁ “የቅኝ ገዥወች የልጅ ልጅ ስለሆነና የገደሉትም በአማራ ሲበደሉ የነበሩና በዚህ አገዛዝ ነፃ የወጡ ጉምዞች በመሆናቸው ነው”። በመሆኑም “ቅኝ ገዥ የነበረው አማራ” ነፍስና የዳንጎቴው ስራስካጅ ነፋስ ለአሁኑዋ ኢትዮጵያ ገዥወች ዋጋቸው በጣም የተለያየ ነው። ለውድድር ማቅረቤም የኔን አላዋቂነትና ቂልነት የሚያሳይ ሳይሆን አይቀርም።
እግዚአብሔር ሆይ የተበደሉና በጥልቅ ሃዘን ውስጥ ያሉ ሰዎችን ጩኸት ስማ!!!
በተያያዘ

በአማራ ብሔር ላይ ያነጣጠር ጥቃት ቀጥሏል!?!

ሀንድ ቱ ሀንድ ኢትዮጵያ
በቤንሻንጉል ዘር ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ሳይቆም  በጂማ ሊሙ ሦስት አማሮች ሌሊት ላይ በገጀራ ታርደው መገደላቸውን ምንጮቻቸውን ጠቅሰው የአማራ አክቲቪስቶች ይፋ አድርገዋል።
በጂማ ሊሙ ዛሬ የሚከበረውን የክርስቶስ እርገት ለማክበር በማታ ወደ ጨንጊ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በመጓዝ ላይ የነበሩ  ሦስት የአማራ ብሔር  ተወላጆ በገጀራ ታርደው ሕይወታቸው ሲያልፍ አንድ ሌላ በጽኑ ቆስሎ ሆስፒታል ገብቱዋል።
 ሲሆን አንድ ሰው በከባድ ጉዳት ሕክምና ገብቷል፡፡ ይህን መሰሉ ጥቃት አዲስ አለመሆኑን ያስታወሱት አክቲቪስቶች  በ1999 ዓም በርካታ አማሮች በሻሻ አቦ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በገጀራና በእሳት መገደላቸውን በምሳሌ ጠቅሰዋል።
ትናንት በተፈጸመባቸው የጭካኔ እርምጃ ሕይወታቸው ያለፈው ሶስት ሰዎችን በስም ጠቅሰው ይፋ አድርገዋል። እነዚህም  አስማማው አማረ ፣መርሻ መኮንን እና   መኳንንት  የተባሉ መሆናቸውን ጠቅሰው የቆሰለው ብርሀኑ ጌቱ ደግሞ በከፍተኛ ሁኔታ ጉዳት ደርሶበታል ትብሉዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በቤንሻንጉል ክልል ትልልንት በአሰቃቂ ሁኔታ በስለት ተወጋግቶና ተሰልቦ ጉዳት የደረሰበት የ14 ዓመቱ አቸፈር ላይ ከተወሰደው በተጨማሪ ዛሬም በአማራ ተወላጆች ላይ ድብቅ ጥቃት ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን በቀስት እየተወጉ የሞቱና ዐይናቸው የፈሰሰ መኖራቸውን የመረጃ ምንጮቻቸውን ጠቅሰው ጽፈዋል።
ዶ/ር አብይ አህመድ ሁኔታው በአስቸኩዋይ እንዲጣራና ውሳኔ እንዲሰጡ የሚጠይቁም አሉ።
Filed in: Amharic