አገሬ ስለአንድ የዜጋው ነፍስ የሚጨንቅ መሪ አገኘች
እናት ሐሊማና ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶር አቢይ ወግ !
* ለፈጣሪ አምላክ ምስጋና ይድረሰው !
ነቢዩ ሲራክ

በመጨረሻም ” አይዞሽ በልጅሽ ጉዳይከልዑላኑ ጋር ተነጋግረናል ፣ አስፈላጊው ካሳችሁ ተከፍሏችሁ በቅርቡ ወደ ሀገር ትገቡ ዘንድ ስምምነት ላይ ተደርሷል ! ” የሚል የደስታ ብስራት እናት ሐሊማን አበሰሯት 🙂 እናማ እናት ሐሊማን ስቃ ፈንድቃ የደስታ እንባ እያጎረፈች ተሳሳምን !

ጁምአ የፍትህ ዘመቻችን 13 ኛ ሳምንት ስኬት ምክንያቱ ብርቱው የእናት ሐሊማ ጽናትና የእናንተ አጋርነት ነው !
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶር አቢይ አህመድንና ዶር ወርቅነህን ደጋግሜ አመሰግናለሁ !
ለዚህ ደስ የሚል ቀን ላደረሰን ፈጣሪ አምላክ ምስጋና ይድረሰው !
ግንቦት 10 ቀን 2010 ዓም