
በእርግጥ ሁለቱም ላመኑለት አላማ የመጨረሻ የሚባለውን ምርጫ በመምረጣቸው ያመሳስላቸዋል።እየታሰሩ ሳይሆን ገሎ መሞትን ,በህወሃት ህግ ሳይሆን በራሳቸው ህግ ና በራሳቸው መንገድ ኖረው አሳይተውናል።
ልዩነቱ ግን አንዳቸው ካሉበት በሚስጥር ተጠርተው በክብር ተደራድረው ከቦሌ የአበባ ጉንጉን ተይዞ ሲጠብቃቸው ሌላኛው ደግሞ በረቀቀ መንገድ የገቡበት ተገብቶ ታፍነው ተወስደዋል።ትልቋን ኢትዮጵያን ካሰብክ ዋጋው ብዙ ነው።አንዳርጋቸው ይህን ዋጋ እየከፈለ ይገኛል።
ዶክተር አብይ በአፉ ኢትዮያን አሳምሮ እንደሚነግረን ሁሉ አንዳርጋቸውን ቤተመንግስት ጋብዞ እንደነ ሌንጮ ማነጋገር ባይችል እንኳን ይልቀቅልንና በስደት ካሉት ቤተሰቦቹና ከኛ ከምንወደው ኢትዮጵይያውያን ጋር ይቀላቀል።