>

ግንቦት ''20'' የፋሽስታዉያን የስኬት ቀን፦ (አዲሱ መኮንን)

ዘመነኞቹ እና ቢሊነረቹ በጭቁኑ ህዝባችን ላይ አፋና ፣ግድያ ፣ቶርቸር ፣ወፌ ይላላ ግርፋት ፣ዘርን መሠረት ያደረገ ዘር ማጥፋትና ዘር ማፅዳት /Genocide and Cleansing/ የመፈፀሚያ ቀን ፣
ግንቦት ”20” የዘመነኞቹ የመሪነት ዝቅጠት መገለጫ ፣ስርቆት እንደ ስራ የተቆጠረበት ቀን ፣ብሄራዊ ዉርደት እንደ ክብር የታየበት ፣የእብሪትና ከእኔ በላይ ለአሳር የተፀባረቀበት ፣ዉንብድና ማፍያነት እንደ ጀግንነት የታየበት ፣የሞራል መላሸቅእና ሀገራዊ ዉድቀት እንደ ስኬት የተቆጠረበት ፣ኢትዮጵያዊ ክብር በአጋዚያን እይታ የከሰረበት ፣የህዝባችን የእርስ በእረስ ግጭት የድርጅቱ ግብ የተደረገበት ፣ጥርጣሬና በህዝብ ዘንድ ያለመተማመን ኩራት የተመዘገበበት ያ ግንቦት 20 ።
ግንቦት”20” የህወሃት የዱር ህግና የከሰረ ሪዮት ዓለም በእናት ኢተዮጵያ ጎልቶ የታየበት ፣የሪዮት ዓለም ክስረት አንዴ ከምስራቁ ዓለም በሌላ ጊዜ ከምዕራቡ ዓለም ውሃ ቅዳ ዉሃ መልስ የዋጀቀበት እንዲሁም ጊዜ ካለፈበት አልባኒያ ተቀድቶ ከሩቅ ምስራቅ ከአብዮታዊነት ወደ ልማታዊነት በመርሽ ቀያሪዎች ማረፊያ ያገኘበት በኢትዮጵያችን ሀያልነት ላይ  የዉርደት ካባ ያከነባበት ፣ ትልቋ እናት ሀገራችን ትልቅ እንዳልነበረች የሪዮት ዓለም ክሽፈት ለይ የወደቀችበት ፣እናት ሀገራችን መርህ ፥ሀገራዊ ዕሴቶች እና ባህሎችን ራዕይ አልባ በሆኑ መሪዎቿ ከሀገር ቁመና ዉጪ የሆነችበት ።
ግንቦት ”20” ለሀገር ክብርና ለህዝብ ነፃነት የተደራጁ ድርጂቶች በጠላትነት የተፈረጁበት ፣ተፎካካሪ ፓርቲ መሪዎችና አባላት ፣ጋዜጤኞች እና ሰብአዊ መብት ተሞጋቾች እንደ ወንጀለኛ ተቆጥረዉ በምድር በላይ ሰቆቃ ያዮበት ፣ስነቶች የሚወዷትን ሀገር ጥለዉ ሲሰደዱ የአዉሬ የበረሃ እና የዉቅያኖስ ሰለባ የሆኑበት ቀን ።
ግንቦት ”20” በከሸፋ የመንግስት ፖሊሲ ዉጤት ስንቱ ጀግና ዘርን መሠረት በማድረግ እንደ ወጣ የቀረበት በዘመነኞቹ እንደ ጀብድ የተቆጠረበት ፣ አንድን ህዝብ በሌላው ክልል የሚኖረዉን ማፈናቀል እንደ ጀግንነት የታየበት ፣ ሀገርንና ህዝብን መዉድ እንደ ሀጢያት የተቆጠረበት ፣ኢትዮጵያዊነት ስሜት ከበረዶ በታች የቀዘቀዘበት ፣የጀግና ልጅ ተሰዶ የባንዳ ልጅ የነገሠበት ፣ የህዝብ ሀብት የተዘረፈበት ፣ ስራዓጥነት እና ፍፁም ድህነት ብሄራዊ መገለጫ የሆነበት ቀን ።
  ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!
                ግንቦት 19/2010 ዓ /ም
Filed in: Amharic