>

ነጻነትን የሚያውቀው ነጻ አውጭ የመፈታቱ ግምት ወደ 100 ፐርሰንት የተጠጋ ይመስላል!???! (ፋሲል የኔአለም)

2015 – “አንዳርጋቸውን በኢቲቪ ባየሁት ቁጥር የነጻነት ትግሉ እያደገ፣ ያምባገነኖች ቀን ደግሞ እያጠረ መሄዱን ያስታውሰኛል… ህወሃቶች ያልገባቸው እኮ አንዳርጋቸው በታሰረባቸው 6 ወራት ውስጥ ብዙ ነገሮች በፍጥነት የተለዋወጡ መሆኑን ነው። ከአየር ሃይል አብራሪዎች መጥፋት ጀምሮ ብዙ ውጫዊና ውስጣዊ ክስተቶች የነጻነት ትግሉን ከፍ ከፍ አድርገውታል። አንዳርጋቸው ስለአሁኑ ቀርቶ ስላለፈውም ቢሆን ምንም የሚሰጣቸው ነገር የለምና ባያደክሙት ይመከራል።”
በ2014- “ይሄ አንበሳ ጅቦቹን ያስበረግጋቸው ጀምሯል… አንበሳን የማሰር ትርፉ ኮሽ ባለቁጥር መበርገግ ነው። ያ ተራሮችን አንቀጠቀጥኩ የሚለው ቡድን በአንድ አንበሳ ሲንቀጠቀጥ ማየት አንበሳ መሆንን ያስመኛል።”
አንዳርጋቸውን ለማሰርም ለመፍታትም የነበረውን ግርግር ስመለከት፣ ሰውዬው የተሸከመው ራይዕ ከኤቨረስት ተራራ የገዘፈ መሆኑን ዘወትር እንዳስታውሰው ያደርገኛል።
ከ4 ዓመት በፊት አንዳርጋቸውን በጅቦች ተከቦ አይቼዋለሁ፣  ዛሬ ደግሞ አንዲን በ ጀግኖች ተከቦ ለማየት ጓጉቻለሁ።
በተለያዩ የማህበራዊ ሚድያዎች ላይ እኒህ ሀሳቦች ሲንሸራሸሩ ተመልክቻለሁ:-
 – አንዳርጋቸው ጽጌ ከቃሊቲ ማረሚያ ወጥቷል
– የቦሌ መንገድ በመኪና ጥሩንባ ጩኽት ደምቃለች!
– አንዲ  ወደቤቱ እየመጣ ነው!
– በኢትዮጵያ የኢንግሊዝ ኤምባሲ ስምንት v8 መኪናዎች በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ገብተው ይዘውት ወጥተዋል የሚለው ግምት ለተአማኒነቱ ቀረብ ያለ ይመስላል።
– የአንዳርጋቸዉ ጽጌ እህት ወ/ሮ ኑኑ ጽጌ ጨምሮ ከተለያየ ቦታ የመጡ የአዲስ በበባ ወጣቶች  ተቀብለውታል::
– የጉዞዉ ሰነድ በማለቁ ዛሬ ወደ ቤተሰቦቹ፤ አገረ እንግሊዝ ይጓዛል ~ ተብሏል
– በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ቤተሰቦች ቤት በርካታ ወጣቶች ተሰብሰበው እየጠበቁት ነው።
– ወላጆቹም፤ እንዲህ ተውበው የልጃቸውን መምጣት እየጠበቁ ናቸው።
እንግሊዙ ስካይ ኒውስ Sky News ዘገባ ከሆነ አቶ አንዳርጋቸው ዛሬ፤ ሰኞ ማታ ለንደን ይገባሉ።
የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ትናንት እሁድ ምሳ ሰዓት አካባቢ ለአቶ አንዳርጋቸው ባለቤት ወይዘሮ የምሥራች ኃ/ማርያም ስልክ በመደወልአንዳርጋቸው በይቅርታ ከእስር ተፈተው በሁለት ቀናት ውስጥ ወደ ለንደን እንደሚደርሱ አረጋግጠውላቸዋል።
ልጆቹም የአባታቸውን አይን ለማየት በከፍተኛ ጉጉት እየጠበቁ ይገኛሉ።
Filed in: Amharic